ከሰኔ 30–ሐምሌ 6
ምሳሌ 20
መዝሙር 131 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. በተሳካ ሁኔታ ለመጠናናት የሚረዱ ቁልፎች
(10 ደቂቃ)
ይሖዋ ስለ መጠናናት ያለውን አመለካከት አትዘንጉ (ምሳሌ 20:24, 25፤ w24.05 26-27 አን. 3-4)
መጠናናት ከመጀመራችሁ በፊት ግለሰቡን ከርቀት ተመልከቱት (ምሳሌ 20:18፤ w24.05 22 አን. 8)
በምትጠናኑበት ወቅት በደንብ ለመተዋወቅ ጥረት አድርጉ (ምሳሌ 20:5፤ w24.05 28 አን. 7-8)
አስታውሱ፦ መጠናናት ተሳካ የሚባለው ወደ ትዳር ሲያመራ ብቻ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ ሲረዳችሁ ነው።
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
ምሳሌ 20:27—“የሰው እስትንፋስ የይሖዋ መብራት ነው” ሲባል ምን ማለት ነው? (it-2 196 አን. 7)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ምሳሌ 20:1-15 (th ጥናት 5)
4. ውይይት መጀመር
(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ በቅርቡ ከመኖሪያው ተፈናቅሎ እንደመጣ ይነግርሃል። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 3)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። ለግለሰቡ ስለ JW ላይብረሪ አፕሊኬሽን ንገረው፤ እንዲሁም አፕሊኬሽኑን በኤሌክትሮኒክ መሣሪያው ላይ እንዲያወርድ እርዳው። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 5)
6. እምነታችንን ማብራራት
(4 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። ijwbq ርዕስ 159—ጭብጥ፦ እንስሳት ወደ ሰማይ ይሄዳሉ? (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 4)
መዝሙር 78
7. ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሳችንን እንዲሞክሩት አበረታቱ
(5 ደቂቃ) ውይይት።
ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ መጋበዝ የአገልግሎታችን ወሳኝ ክፍል ነው። ደግሞም ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ ካላስጠናን ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ ልንረዳቸው አንችልም። (ሮም 10:13-15) ከቤት ወደ ቤት ስታገለግሉ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ አልፎ አልፎ በቀጥታ ለመጋበዝ ግብ ማውጣት ትችላላችሁ። በመጀመሪያ የቤቱን ባለቤት ትኩረት የሚስበው ርዕሰ ጉዳይ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ጥረት አድርጉ። ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱ ለጥያቄዎቹ መልስ ለማግኘትና ሌሎች ጥቅሞችን ለማግኘት የሚረዳው እንዴት እንደሆነ አሳዩት።
jw.org ላይ ያለው “የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሳችንን ሞክረው” የሚለው ሊንክ የምታገኟቸውን ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ ለመጋበዝ ይረዳችኋል።
“የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሳችንን ሞክረው” የሚለውን ሊንክ ተጠቅማችሁ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ ግብዣ ማቅረብ የምትችሉት እንዴት ነው?
በምትኖሩበት አካባቢ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ውጤታማ ሆኖ ያገኛችሁት ዘዴ የትኛው ነው?
8. ለሰኔ ወር የተዘጋጀው ድርጅቱ ያከናወናቸው ነገሮች
(10 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውት።
9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 28 አን. 8-15