የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb25 መስከረም ገጽ 8-9
  • ከመስከረም 29–ጥቅምት 5

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከመስከረም 29–ጥቅምት 5
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
mwb25 መስከረም ገጽ 8-9

ከመስከረም 29–ጥቅምት 5

መክብብ 3–4

መዝሙር 93 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

አንድ ባልና ሚስት አብረው በደስታ መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነቡ።

እርስ በርሳችሁም ሆነ ከይሖዋ ጋር ጊዜ አሳልፉ

1. በሦስት የተገመደውን ገመድ አጠናክሩ

(10 ደቂቃ)

ትርጉም ባለው መንገድ ለማውራት ጊዜ መድቡ (መክ 3:1፤ ijwhf ርዕስ 10 አን. 2-8)

አብራችሁ ሥሩ (መክ 4:9፤ w23.05 23-24 አን. 12-14)

ከይሖዋ ጋር ጠንካራ ወዳጅነት መሥርቱ (መክ 4:12፤ w23.05 21 አን. 3)


ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በሥራ፣ በመዝናኛም ሆነ በሌላ ምክንያት ከትዳር ጓደኛዬ ርቄ ረዘም ላለ ጊዜ መቆየቴ በትዳራችን ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መክ 3:8—‘ለመውደድ ጊዜው’ ያልሆነው መቼ ነው? (it “ፍቅር” አን. 39)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መክ 4:1-16 (th ጥናት 2)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 1 2025⁠ን ተጠቅመህ ውይይት ጀምር። ግለሰቡ ስለ ሌላ ጉዳይ መወያየት እንደሚፈልግ ስታስተውል አቀራረብህን አስተካክል። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 1 2025 የተበረከተለትን ሰው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 4)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 12—ጭብጥ፦ አምላክ ፍትሐዊ ነው፤ ፈጽሞ አያዳላም። (th ጥናት 19)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 131

7. በትዳራችሁ ውስጥ ችግር ሲያጋጥማችሁ ይሖዋን ከግምት አስገቡ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ይሖዋ ለክርስቲያን ባለትዳሮች አስደሳችና የሰመረ ትዳር ለመመሥረት የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ሰጥቷቸዋል። ያም ቢሆን ባለትዳሮች አልፎ አልፎ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። (1ቆሮ 7:28) እነዚህ ችግሮች ካልተፈቱ ለብዙ የስሜት ሥቃይ ሊዳርጉና እየተባባሱ ሊሄዱ ይችላሉ። እናንተስ በትዳራችሁ ውስጥ እንዲህ ያሉ ችግሮች ካጋጠሟችሁ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

እውነተኛ ፍቅር ምንድን ነው? የተባለው ድራማ ከባድ ችግር ያጋጠማቸውን ወጣት ባለትዳሮች ያሳያል። ሚስትየው ይሖዋን ከግምት ያላስገባ ውሳኔ ልታደርግ ስትል አባቷ ምን ምክር እንደሰጣት ታስታውሳላችሁ?

እውነተኛ ፍቅር ምንድን ነው?—ተቀንጭቦ የተወሰደ የተባለውን አጭር ድራማ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • በትዳራችን ውስጥ ችግሮች ሲያጋጥሙን የይሖዋን መመሪያ መከተል ያለብን ለምንድን ነው?—ኢሳ 48:17፤ ማቴ 19:6

በትዳራችሁ ውስጥ ከባድ ችግር ካጋጠማችሁ ጥሩ መንፈሳዊ ልማድ ይዛችሁ በመቀጠል ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ዝምድና ጠብቁ። የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ተጠቅማችሁ ችግሩን ለመፍታት ተግታችሁ ሥሩ፤ እንዲሁም ያላችሁበትን ሁኔታ ከይሖዋ አመለካከት አንጻር ለማየት የሚረዷችሁን ሐሳቦች ከጽሑፎቻችን ላይ ፈልጉ። እንዲህ ካደረጋችሁ የይሖዋን ድጋፍና በረከት እንደምትፈልጉ ታሳያላችሁ።—ምሳሌ 10:22፤ ኢሳ 41:10

“አሳሳች በሆነ ሰላም አትታለሉ!—ዴረል እና ዴብራ ፍሬዚንገር” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ዴብራ በወጣትነቷ ፎቶግራፍ ስትመለከት የሚያሳይ ትወና።

አሳሳች በሆነ ሰላም አትታለሉ!—ዴረል እና ዴብራ ፍሬዚንገር የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • በትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙ ከባድ ችግሮችን ከመፍታት ጋር በተያያዘ ከወንድም ፍሬዚንገርና ከባለቤቱ ተሞክሮ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 22፣ የክፍል 5 ማስተዋወቂያ እና ትምህርት 23

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 51 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ