ከጥቅምት 6-12
መክብብ 5–6
መዝሙር 42 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
አንድ ካህን ሕጉን ሲያብራራ የተወሰኑ እስራኤላውያን በጥሞና ሲያዳምጡት
1. ታላቁን አምላካችንን በጥልቅ እንደምናከብር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
(10 ደቂቃ)
በስብሰባዎች ላይ በጥሞና በማዳመጥ እንዲሁም ለአለባበሳችንና ለአጋጌጣችን ትኩረት በመስጠት አክብሮት እናሳያለን (መክ 5:1፤ w08 8/15 15-16 አን. 17-18)
በሕዝብ ፊት የምናቀርበው ጸሎት ቃላት የበዛበት ሳይሆን በሚገባ የታሰበበትና አክብሮት የሚንጸባረቅበት እንዲሆን እናደርጋለን (መክ 5:2፤ w09 11/15 11 አን. 21)
ራሳችንን ስንወስን የገባነውን ቃል እንጠብቃለን (መክ 5:4-6፤ w17.04 6 አን. 12)
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
መክ 5:8—ኢፍትሐዊ ድርጊት ሲፈጸምብን ይህ ጥቅስ የሚያጽናናን እንዴት ነው? (w20.09 31 አን. 3-5)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
4. ውይይት መጀመር
(1 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ መከራከር ጀመረ። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 5)
5. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ላይ ከሚገኙት “ለማስተማር የምንጓጓቸው እውነቶች” መካከል አንዱን አካፍል። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 3)
6. ተመላልሶ መጠየቅ
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ የሚገኝ አንድ ቪዲዮ ተጠቀም። (lmd ምዕራፍ 7 ነጥብ 3)
7. ደቀ መዛሙርት ማድረግ
መዝሙር 160
8. “ለማስተማር የምንጓጓቸው እውነቶች” የተባለውን ክፍል እየተጠቀማችሁበት ነው?
(15 ደቂቃ) ውይይት።
ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ የተባለው ብሮሹር ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ውይይት የማድረግ ችሎታችንን እንድናሻሽል እየረዳን ነው። ተጨማሪ መረጃ ሀ የተዘጋጀው ከሰዎች ጋር ውይይት ስናደርግ መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ለማስተዋወቅ እንዲረዳን ታስቦ ነው። (ዕብ 4:12) “ለማስተማር የምንጓጓቸው እውነቶች” በሚለው ሥር ያሉትን ዘጠኝ ርዕሰ ጉዳዮች በደንብ ታውቋቸዋላችሁ?
ከሰዎች ጋር ስንወያይ ተስማሚ ጊዜ መርጠን አንድን መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ማስተዋወቅ የምንችለው እንዴት ነው?—lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ
በክልላችሁ ውስጥ ይበልጥ ውጤታማ ሆነው ያገኛችኋቸው ርዕሰ ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው?
በተጨማሪ መረጃ ሀ ውስጥ ካሉት ጥቅሶች ጋር በደንብ ለመተዋወቅ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
እነዚህን ጥቅሶች በአገልግሎት ላይ በተጠቀምንባቸው መጠን ይበልጥ እየለመድናቸው እንሄዳለን። ይሁንና እነዚህን ጥቅሶች አዘውትረን መጠቀም እንድንችል በመጀመሪያ በክልላችን ውስጥ ያሉትን ሰዎች ማግኘት አለብን።
‘ብረት ብረትን ይስላል’—ለብዙ ሰዎች መመሥከር የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
በክልላችን ውስጥ ብዙ ሰዎችን ለማግኘት ምን ሊረዳን ይችላል?
9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 24-25