ከጥር 5-11
ኢሳይያስ 17–20
መዝሙር 153 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. “የዘረፉን ሰዎች ድርሻ”
(10 ደቂቃ)
መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ዘር ከሚናወጥ ባሕር ጋር ያመሳስለዋል (ኢሳ 17:12፤ w18.06 7 አን. 16)
በገለልተኝነት አቋማችን የተነሳ ከዓለም ፈተና እንደሚደርስብን እንጠብቃለን (ዮሐ 15:18, 19፤ w16.04 28 አን. 4)
በቅርቡ ይሖዋ ‘ከሚዘርፉን ሰዎች’ ይታደገናል (ኢሳ 17:13, 14፤ ip-1 198 አን. 20)
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
ኢሳ 20:2—በእርግጥ ኢሳይያስ ለሦስት ዓመታት ሙሉ በሙሉ ራቁቱን ተመላልሷል? (w06 12/1 11 አን. 1)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ኢሳ 19:1-12 (th ጥናት 11)
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ባለትዳር ለሆነ ግለሰብ ሰዎችን ውደዱ በተባለው ብሮሹር ተጨማሪ መረጃ ሀ ላይ የሚገኝ አንድ እውነት አካፍል። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 3)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 4)
6. ንግግር
(5 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 14—ጭብጥ፦ አምላክ ወደ እሱ እንድንጸልይ ይፈልጋል። (th ጥናት 8)
መዝሙር 148
7. ‘መሸሸጊያ ዓለታችሁን አስታውሱ’
(10 ደቂቃ) ውይይት።
ይሖዋ መሸሸጊያ ዓለታችን ነው። (ኢሳ 17:10) እሱን መጠለያ የሚያደርጉትን ይታደጋቸዋል። (መዝ 144:1, 2) ይሖዋ ተቃውሞን የሚያስወግድልን ሁልጊዜ ባይሆንም ወዳጆቹ ተቃውሞን በጽናት ለመቋቋም የሚያስፈልጋቸውን ነገር ምንጊዜም ይሰጣቸዋል።—1ቆሮ 10:13
ይሖዋን እንደምናስታውስ የምናሳይበት አንዱ መንገድ እሱን መታዘዝ ነው። ከይሖዋ ወዳጆች ተማሩ—ሃናንያህ፣ ሚሳኤል እና አዛርያስ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም አስቀድመህ የመረጥካቸው ልጆች ወደ መድረኩ እንዲወጡ ካደረግክ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቃቸው፤ ወይም አድማጮችን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
ይሖዋ ወዳጆቹን ያዳናቸው እንዴት ነው?—ዳን 3:24-28
ሃናንያህ፣ ሚሳኤል እና አዛርያስ የይሖዋ ወዳጆች እንደሆኑ ያሳዩት እንዴት ነው?
ይሖዋን መታዘዝ የሚከብዳችሁ መቼ ነው?
ይሖዋን ለመታዘዝ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
8. በየቀኑ ከይሖዋ ወዳጆች ለመማር ጊዜ መድቡ
(5 ደቂቃ) ውይይት።
ከይሖዋ ወዳጆች ተማሩ የተባለው ተከታታይ ቪዲዮ የተዘጋጀው ማንበብ እየተማሩ ላሉ ልጆች ነው። ለልጆቹ ይሖዋን ስለሚወዱ ሰዎች ያስተምራቸዋል። እያንዳንዱ ቪዲዮ፣ ለልጆች “በየቀኑ ከይሖዋ ወዳጆች ለመማር ጊዜ መድቡ” የሚል ማበረታቻ ይሰጣል።
በየቀኑ ስለ ይሖዋና ስለ ወዳጆቹ ለመማር ጊዜ መመደብ የምትችሉት እንዴት ነው?
ስለ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች ይበልጥ መማር ትፈልጋላችሁ? ለምንስ?
9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 50፣ የክፍል 9 ማስተዋወቂያ እና ትምህርት 51