የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች
© 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
ከጥር 5-11
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት ኢሳይያስ 17–20
“የዘረፉን ሰዎች ድርሻ”
“መንግሥቴ የዚህ ዓለም ክፍል አይደለም”
16 በእርግጥም እንዲህ ዓይነት ለውጥ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው! መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ዘር፣ ጸጥ ማለት ከማይችል የሚናወጥ ባሕር ጋር ያመሳስለዋል። (ኢሳ. 17:12፤ 57:20, 21፤ ራእይ 13:1) ፖለቲካዊ ጉዳዮች ሰዎች እርምጃ ለመውሰድ እንዲነሳሱ፣ እንዲከፋፈሉ እንዲሁም ዓመፅ እንዲቀሰቅሱ ቢያደርጓቸውም እኛ ግን ሰላማዊ ለመሆንና አንድነታችንን ለመጠበቅ ጥረት እናደርጋለን። ይሖዋ እንዲህ ባለው የተከፋፈለ ዓለም ውስጥ በሕዝቡ መካከል ያለውን አንድነት ሲመለከት ምንኛ ይደሰት ይሆን!—ሶፎንያስ 3:17ን አንብብ።
በተከፋፈለ ዓለም ውስጥ የገለልተኝነት አቋማችሁን ጠብቁ
4 በምንኖርበት አገር ያለው የፖለቲካ ሁኔታ የተረጋጋና ለእውነተኛው አምልኮ አመቺ ይመስል ይሆናል። ያም ሆኖ የሰይጣን ሥርዓት ወደ መጨረሻው እየተቃረበ ሲሄድ የገለልተኝነት አቋምን መጠበቅ ይበልጥ አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል እንጠብቃለን። የምንኖረው “ለመስማማት ፈቃደኞች ያልሆኑ” እንዲሁም ‘ግትር’ የሆኑ ሰዎች በሞሉበት ዓለም ውስጥ በመሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህ ዓለም ይበልጥ እየተከፋፈለ መሄዱ አይቀርም። (2 ጢሞ. 3:3, 4) በአንዳንድ አገሮች ፖለቲካዊ ሁኔታዎች በፍጥነት በመለዋወጣቸው፣ ወንድሞቻችን ከገለልተኝነት ጋር የተያያዙ ያልተጠበቁ ፈተናዎች አጋጥመዋቸዋል። እንግዲያው ገለልተኝነታችንን ለመጠበቅ አሁኑኑ አቋማችንን ማጠናከር እንዳለብን አስተዋላችሁ? ፈታኝ ሁኔታ እስኪፈጠር ድረስ እጃችንን አጣጥፈን የምንጠብቅ ከሆነ አቋማችንን ልናላላና ገለልተኛ ሳንሆን ልንቀር እንችላለን። ታዲያ በዚህ በተከፋፈለ ዓለም ውስጥ ገለልተኝነታችንን ለመጠበቅ መዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው? በዚህ ረገድ የሚረዱን አራት ቁልፍ ነጥቦችን እንመልከት።
ይሖዋ በብሔራት ላይ የመከረው ምክር
20 ውጤቱስ ምን ይሆናል? ኢሳይያስ እንዲህ ይላል፦ “በመሸ ጊዜ፣ እነሆ፣ ድንጋጤ አለ፤ ከማለዳም በፊት አይገኙም። የዘረፉን ሰዎች እድል ፈንታ፣ የበዘበዙንም ዕጣ ይህ ነው።” (ኢሳይያስ 17:14) ብዙዎች የይሖዋን ሕዝብ በማንገላታትና አክብሮት በጎደለው መንገድ በመያዝ በዝብዘዋቸዋል። እውነተኛ ክርስቲያኖች ታላላቅ ከሚባሉት የዓለም ሃይማኖቶች መካከል ስላልሆኑና መሆንም ስለማይፈልጉ አንዳንድ የተሳሳተ ግንዛቤ ያላቸው አክራሪ ተቃዋሚዎች በቀላሉ ለጥቃት የተጋለጡ ሰዎች እንደሆኑ አድርገው ይቆጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ የአምላክ አገልጋዮች የሚደርስባቸው መከራ የሚያበቃበት ‘ማለዳ’ በፍጥነት እየተቃረበ እንዳለ እርግጠኞች ናቸው።—2 ተሰሎንቄ 1:6-9፤ 1 ጴጥሮስ 5:6-11
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
የኢሳይያስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች—ክፍል 1
20:2-5—ኢሳይያስ ለሦስት ዓመት ያህል ዕርቃኑን ሄዷል? ምናልባት ኢሳይያስ ከላይ ያለውን መደረቢያ አውልቆ ‘ከውስጥ በለበሳት ልብስ ብቻ’ ሄዶ ይሆናል።—1 ሳሙኤል 19:24፣ የአዲስ ዓለም ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ
ከጥር 12-18
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት ኢሳይያስ 21-23
ከሸብና ውድቀት የምናገኘው ትምህርት
ተግሣጽ—የአምላክ ፍቅር መግለጫ
7 ተግሣጽ የሚያስገኘውን ጥቅም ለማስተዋል ይሖዋ የገሠጻቸውን ሁለት ሰዎች ምሳሌ እንመልከት፤ አንደኛው በሕዝቅያስ ዘመን የኖረው ሸብና ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በዘመናችን ያለው ወንድም ግሬሃም ነው። ሸብና ‘በቤቱ ላይ [በሕዝቅያስ ቤት ላይ ሳይሆን አይቀርም] የተሾመ መጋቢ’ እንደመሆኑ መጠን ከፍተኛ ሥልጣን ነበረው። (ኢሳ. 22:15) የሚያሳዝነው ግን ኩሩ በመሆን ለራሱ ክብር መፈለግ ጀመረ። ሌላው ቀርቶ ለራሱ እጅግ ውድ የመቃብር ቦታ ያሠራ ከመሆኑም ሌላ ‘ባማሩ ሠረገሎች’ ይሄድ ነበር!—ኢሳ. 22:16-18
8 ሸብና ለራሱ ክብር ማግኘት ስለፈለገ አምላክ ‘ከኃላፊነቱ አባርሮ’ በእሱ ምትክ ኤልያቄምን ሾመው። (ኢሳ. 22:19-21) ይህ ለውጥ የተደረገው የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን ለማጥቃት እያሰበ በነበረበት ወቅት ላይ ነው። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሰናክሬም ሕዝቅያስንም ሆነ አይሁዳውያንን ወኔ እንዲከዳቸውና እጅ እንዲሰጡ ለማድረግ ሲል በብዙ ሠራዊት የታጀቡ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ወደ ኢየሩሳሌም ላከ። (2 ነገ. 18:17-25) እነዚህን ባለሥልጣናት እንዲያነጋግር የተላከው ኤልያቄም ነበር፤ ሆኖም ብቻውን አልነበረም። ሌሎች ሁለት ሰዎች አብረውት የነበሩ ሲሆን ከሁለቱ አንዱ ሸብና ነበር፤ ሸብና በዚህ ወቅት በጸሐፊነት እያገለገለ ነበር። ይህ ሁኔታ ሸብና በተወሰደበት እርምጃ ከመከፋትና ቅር ከመሰኘት ይልቅ የተሰጠውን ከቀድሞው ዝቅ ያለ ኃላፊነት በትሕትና እንደተቀበለ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። ታዲያ እኛ ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን? እስቲ ሦስት ነጥቦችን እንመልከት።
9 በመጀመሪያ ደረጃ፣ ሸብና የነበረውን ኃላፊነት አጥቷል። በእሱ ላይ የደረሰው ነገር “ኩራት ጥፋትን፣ የትዕቢት መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል” የሚለውን ማስጠንቀቂያ እንድናስታውስ ያደርገናል። (ምሳሌ 16:18) እኛም በጉባኤ ውስጥ አንዳንድ ኃላፊነቶች ይኖሩን ይሆናል፤ ምናልባትም አንዳንዶች በዚህ የተነሳ ከፍ ያለ ቦታ ሊሰጡን ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ትሑቶች በመሆን ለራሳችን ሚዛናዊ አመለካከት ለመያዝ ጥረት እናደርጋለን? ላሉን ተሰጥኦዎችም ሆነ ላከናወንናቸው ነገሮች ሁሉ ሊመሰገን የሚገባው ይሖዋ እንደሆነ አምነን እንቀበላለን? (1 ቆሮ. 4:7) ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “እያንዳንዱ ሰው ከሚገባው በላይ ስለ ራሱ በማሰብ ራሱን ከፍ አድርጎ አይመልከት፤ ከዚህ ይልቅ . . . ጤናማ አስተሳሰብ እንዳለው በሚያሳይ መንገድ እንዲያስብ፣ በመካከላችሁ ያለውን እያንዳንዱን ሰው . . . እመክራለሁ።”—ሮም 12:3
ተግሣጽ—የአምላክ ፍቅር መግለጫ
10 በሁለተኛ ደረጃ፣ ይሖዋ ለሸብና ጠንከር ያለ ተግሣጽ መስጠቱ ሸብናን ‘ፈጽሞ ሊለወጥ አይችልም’ ብሎ ተስፋ እንዳልቆረጠበት የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። (ምሳሌ 3:11, 12) ይህ በአምላክ ጉባኤ ውስጥ ያላቸውን የአገልግሎት መብት ላጡ በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች እንዴት ያለ ግሩም ትምህርት ነው! በሁኔታው ከመበሳጨት ወይም ቅር ከመሰኘት ይልቅ የተሰጣቸውን ተግሣጽ የአምላክ ፍቅር መግለጫ እንደሆነ አድርገው ሊመለከቱትና አሁን ያሉበት ሁኔታ በፈቀደላቸው መጠን ምርጣቸውን በመስጠት አምላክን ማገልገላቸውን ሊቀጥሉ ይችላሉ። አባታችን ራሳችንን በፊቱ ዝቅ እስካደረግን ድረስ ፈጽሞ ተስፋ እንደማይቆርጥብን እናስታውስ። (1 ጴጥሮስ 5:6, 7ን አንብብ።) ፍቅር የሚንጸባረቅበት ተግሣጽ፣ አምላክ እኛን የሚቀርጽበት አንዱ መንገድ ስለሆነ በእሱ እጅ በቀላሉ ለመቀረጽ ፈቃደኞች እንሁን።
ተግሣጽ—የአምላክ ፍቅር መግለጫ
11 በሦስተኛ ደረጃ፣ ይሖዋ ሸብናን የያዘበት መንገድ ተግሣጽ የመስጠት ኃላፊነት ለተሰጣቸው ሁሉ ለምሳሌ ለወላጆችና ለክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች ትልቅ ትምህርት ይሰጣል። ትምህርቱ ምንድን ነው? ይሖዋ የሚሰጠው ተግሣጽ ለኃጢአት ያለውን ጥላቻ ብቻ ሳይሆን ኃጢአት ለሠራው ግለሰብ ያለውን አሳቢነትም ያሳያል። አንተም ወላጅ ወይም የበላይ ተመልካች ከሆንክ ተግሣጽ መስጠት የሚያስፈልግህ ጊዜ ሊኖር ይችላል፤ ታዲያ በዚህ ጊዜ መጥፎ የሆነውን ነገር እንደምትጠላ በማሳየት ብቻ ሳይሆን የእምነት ባልንጀራህ ባለው መልካም ባሕርይ ላይ በማተኮርም ይሖዋን ለመምሰል ጥረት ታደርጋለህ?—ይሁዳ 22, 23
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
የኢሳይያስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች—ክፍል 1
21:1—‘በባሕሩ ዳር ያለው ምድረ በዳ’ የተባለው አካባቢ የትኛው ነው? ምንም እንኳ በባቢሎን አካባቢ ቃል በቃል ባሕር ባይኖርም ይህች አገር በዚህ መልኩ ተገልጻለች። ይህም የሆነበት ምክንያት የኤፍራጥስና የጤግሮስ ወንዞች በየዓመቱ እየሞሉ አካባቢውን በማጥለቅለቅ ረግረጋማ ‘ባሕር’ ይፈጥሩ ስለነበረ ነው።
ከጥር 19-25
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት ኢሳይያስ 24-27
“አምላካችን ይህ ነው!”
“እነሆ፣ አምላካችን ይህ ነው!”
አንድ ትንሽ ልጅ አባቱን ለጓደኞቹ እያሳየ ከልብ በመነጨ የደስታና የኩራት ስሜት “አባቴን አያችሁት?” ሲል ሰምተህ ታውቃለህ? የአምላክ አገልጋዮችም ይሖዋን በተመለከተ እንዲህ እንዲሰማቸው የሚያደርግ በቂ ምክንያት አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ታማኝ የሆኑ ሰዎች “እነሆ፣ አምላካችን ይህ ነው!” ብለው በደስታ ስሜት የሚናገሩበት ጊዜ እንደሚመጣ ይገልጻል። (ኢሳይያስ 25:8, 9) ስለ ይሖዋ ባሕርያት ይበልጥ ባወቅህ መጠን ይሖዋ ከሁሉ የላቀ ጥሩ አባት እንደሆነ እየተሰማህ ይሄዳል።
ከዳቦው ተአምር ምን እንማራለን?
14 ኢየሱስ “የዕለቱን ምግባችንን ዛሬ ስጠን” ብለን እንድንጸልይ ባስተማረበት ወቅት የአምላክ ፈቃድ “በሰማይ እየተፈጸመ እንዳለ ሁሉ በምድርም ላይ ይፈጸም” ብለን እንድንጸልይ ነግሮናል። (ማቴ. 6:9-11) በዚያ ጊዜ ዓለማችን ምን ትመስል ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ፈቃድ በምድር ላይ ሲፈጸም ጥሩ ምግብ እንደምናገኝ ይነግረናል። በኢሳይያስ 25:6-8 መሠረት በይሖዋ መንግሥት አገዛዝ ሥር የተትረፈረፈ ምርጥ ምግብ ይኖራል። መዝሙር 72:16 “በምድር ላይ እህል ይትረፈረፋል፤ በተራሮችም አናት ላይ በብዛት ይኖራል” ይላል። በዚያ ጊዜ የሚኖረውን እህል ተጠቅመህ የምትወደውን ዓይነት ዳቦ ስትጋግር ወይም ሌላ ዓይነት ምግብ ስትሠራ ይታይሃል? ወይን ተክለህ ከዚያ የሚገኘውን የወይን ጠጅ ማጣጣምም ትችላለህ። (ኢሳ. 65:21, 22) ደግሞም በምድር ላይ የሚኖር ሰው ሁሉ በእነዚህ ነገሮች ይደሰታል።
የይሖዋ ፍቅር የትኞቹን በረከቶች አስገኝቶልናል?
11 በገነት ውስጥ የሚኖርህ ሕይወት ምን እንደሚመስል ለማሰብ ሞክር። ብታመምስ ወይም ብሞትስ የሚል ስጋት አያድርብህም። (ኢሳ. 25:8፤ 33:24) ይሖዋ ተገቢ የሆኑ ምኞቶችህን በሙሉ ያረካልሃል። ያኔ ምን መማር ትፈልጋለህ? ፊዚክስ? ኬሚስትሪ? ሙዚቃ? ሥዕል? ያኔ የሥነ ሕንፃ፣ የግንባታና የግብርና ባለሙያዎች እንደሚያስፈልጉ ምንም ጥያቄ የለውም። ምግብ የሚያዘጋጁ፣ የተለያዩ መሣሪያዎችን የሚሠሩ እንዲሁም ውቡን መልክዓ ምድር የሚንከባከቡ ሰዎችም ያስፈልጋሉ። (ኢሳ. 35:1፤ 65:21) ለዘላለም ስለምትኖር የፈለግከውን ክህሎት ሁሉ የምታዳብርበት ጊዜ አለህ።
12 ከሞት የተነሱ ሰዎችን መቀበል ምን ያህል አስደሳች ሊሆን እንደሚችል ለማሰብ ሞክር። (ሥራ 24:15) ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የፍጥረት ሥራዎች በመመርመር ስለ ይሖዋ ምን ያህል ትምህርት ልታገኝ እንደምትችልም አስብ። (መዝ. 104:24፤ ኢሳ. 11:9) ከሁሉ በላይ ግን፣ ከበደለኝነት ስሜት ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆኖ ይሖዋን ማምለክ እንዴት ደስ ይላል! ‘በኃጢአት ለሚገኝ ጊዜያዊ ደስታ’ ብለህ እነዚህን በረከቶች ማጣት ትፈልጋለህ? (ዕብ. 11:25) በጭራሽ! ከእነዚህ በረከቶች አንጻር በአሁኑ ጊዜ የትኛውንም መሥዋዕት ብንከፍል አያስቆጭም። ደግሞም ገነት በሆነች ምድር ውስጥ መኖር ተስፋ ሆኖ እንደማይቀር ልብ በል። እውን ይሆናል። ይሖዋ በፍቅር ተነሳስቶ ልጁን ባይሰጠን ኖሮ ይህን ሁሉ በረከት ልናገኝ አንችልም ነበር።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
በ2013 ተሻሽሎ የወጣው እንግሊዝኛው አዲስ ዓለም ትርጉም
ተጨማሪ ምዕራፎች በግጥም መልክ የተቀመጡት ለምንድን ነው? በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መጀመሪያ የተጻፉት በግጥም መልክ ነው። በአሁኑ ጊዜ ባሉ አብዛኞቹ ቋንቋዎች አንድን ጽሑፍ ግጥም የሚያሰኘው ቤት መምታቱ ነው፤ በዕብራይስጥ ቋንቋ ግን ዋናው የግጥም መለያ፣ ተመሳሳይ ወይም ተቃራኒ የሆኑ ነገሮችን በንጽጽር ማስቀመጥ ነው። በዕብራይስጥ ቋንቋ አንድ ግጥም ቤት መታ የሚባለው የስንኙ አጨራረስ ተመሳሳይ በመሆኑ ሳይሆን ሐሳቡ ትርጉም በሚሰጥ ቅደም ተከተል በመቀመጡ ነው።
ቀደም ሲል በተዘጋጁት የአዲስ ዓለም ትርጉም እትሞች ላይ የኢዮብና የመዝሙር መጻሕፍት የተቀመጡት በግጥም መልክ ነው፤ ይህ የሆነበት ምክንያት ሐሳቦቹ መጀመሪያውኑም ቢሆን የተዘጋጁት እንዲዘመሩ ወይም በቃል እንዲደገሙ ታስቦ እንደሆነ ለማሳየት ነው። ይህ ዓይነቱ አቀማመጥ ስንኞቹን አጉልቶ የሚያወጣ ከመሆኑም ሌላ መልእክቱን ለማስታወስ ይረዳል። በ2013 በወጣው እትም ላይ ምሳሌና መኃልየ መኃልይ እንዲሁም በነቢያት መጻሕፍት ውስጥ ያሉ በርካታ ምዕራፎችም በግጥም መልክ እንዲቀመጡ ተደርገዋል፤ ይህም እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መጀመሪያ በግጥም መልክ እንደተጻፉ ብሎም ተመሳሳይ ወይም ተቃራኒ የሆኑ ስንኞችን እንደያዙ ለማጉላት ያስችላል። ለምሳሌ ያህል ኢሳይያስ 24:2 ላይ እያንዳንዱ መስመር በንጽጽር ተቀምጧል። ይህ ጥቅስ የተጻፈው አንዱ ሐሳብ ወደ ሌላው እንዲመራ ተደርጎ ሲሆን ከአምላክ ፍርድ የሚያመልጥ ማንም እንደሌለ ጎላ አድርጎ ይገልጻል። እንዲህ ያሉ ዘገባዎች በግጥም መልክ መጻፋቸው፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊው አንድን ሐሳብ እየደጋገመ ሳይሆን የአምላክን መልዕክት ጎላ አድርጎ ለመግለጽ የግጥም የአጻጻፍ ስልት እየተጠቀመ እንደሆነ ያሳያል።
በዕብራይስጥ ቋንቋ የተዘጋጀ ስድ ንባብንና ግጥምን ሁልጊዜ በቀላሉ መለየት ስለማይቻል አንዳንዶቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በግጥም መልክ ያስቀመጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሌሎቹ በስድ ንባብ መልክ ያስቀምጡታል። በግጥም መልክ መጻፍ ያለባቸው የትኞቹ ክፍሎች እንደሆኑ የሚወስኑት ተርጓሚዎቹ ናቸው። አንዳንዶቹ ዘገባዎች በስድ ንባብ መልክ ቢቀመጡም ሐሳቡን ለማጉላት ሥዕላዊና ቅኔያዊ አገላለጾችን እንዲሁም ንጽጽሮችን ስለሚጠቀሙ የግጥም ይዘት አላቸው።
ከጥር 26–የካቲት 1
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት ኢሳይያስ 28-29
ይሖዋን በከንፈራችሁ እና በልባችሁ አክብሩ
ኢሳይያስ ይሖዋ ስለሚያከናውነው ‘እንግዳ ሥራ’ ይተነብያል
23 የይሁዳ ሃይማኖታዊ መሪዎች በመንፈሳዊ ልባሞች እንደሆኑ ይናገሩ እንጂ ይሖዋን ትተዋል። ይልቁንም ትክክለኛና ስህተት ስለሆነው ነገር የራሳቸውን የተዛባ አመለካከት ያስተምራሉ። እምነት የለሽ ተግባራቸውንና የብልግና ድርጊቶቻቸውን እንዲሁም ሕዝቡ የአምላክን ሞገስ እንዲያጣ በተሳሳተ ጎዳና መምራታቸውን ደህና ነገር አስመስለው ያቀርባሉ። ይሖዋ አንድ “ድንቅ ነገር” ማለትም ‘እንግዳ ሥራ’ በማከናወን ላሳዩት ግብዝነት የእጃቸውን ይሰጣቸዋል። እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፣ በከንፈሮቹም ያከብረኛልና፣ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፣ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛልና ስለዚህ፣ እነሆ፣ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል፣ ድንቅ ነገርን ተአምራትንም፣ እንደ ገና አደርጋለሁ፤ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፣ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።” (ኢሳይያስ 29:13, 14) ይሖዋ የዓለም ኃይል በሆነችው በባቢሎን አማካኝነት ክህደት የተሞላው የይሁዳ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ተጠራርጎ የሚጠፋበትን መንገድ ሲያመቻች ይሁዳ ያፈለቀችው ጥበብና ማስተዋል ሁሉ ይጠፋል። በራሳቸው ዓይን ጠቢብ የሆኑት የአይሁድ መሪዎች ብሔሩ እንዲባዝን ባደረጉበት የመጀመሪያው መቶ ዘመንም ተመሳሳይ ነገር ተከስቷል። በዘመናችንም በሕዝበ ክርስትና ላይ የሚደርሰው ነገር ከዚህ የተለየ አይሆንም።—ማቴዎስ 15:8, 9፤ ሮሜ 11:8
ጻድቃንን ሊያሰናክላቸው የሚችል ምንም ነገር የለም
7 ኢየሱስ በዘመኑ የነበሩትን ግብዝነት የሚንጸባረቅባቸው ሃይማኖታዊ ልማዶች በድፍረት አውግዟል። ለምሳሌ ፈሪሳውያን፣ ወላጆቻቸውን ከሚንከባከቡበት መንገድ ይልቅ እጃቸውን የሚታጠቡበት መንገድ ያሳስባቸው ነበር፤ ኢየሱስም የእነሱን ግብዝነት አጋልጧል። (ማቴ. 15:1-11) የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እሱ በተናገረው ነገር ተገርመው መሆን አለበት። እንዲያውም “ፈሪሳውያን በተናገርከው ነገር ቅር እንደተሰኙ [እንደተሰናከሉ] አውቀሃል?” ብለው ጠይቀውታል። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል። ተዉአቸው፤ እነሱ ዕውር መሪዎች ናቸው። ስለዚህ ዕውር ዕውርን ቢመራ ሁለቱም ጉድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ።” (ማቴ. 15:12-14) ኢየሱስ በዘመኑ የነበሩ ሃይማኖታዊ መሪዎች መበሳጨታቸው እውነቱን ከመናገር እንዲያግደው አልፈቀደም።
ለዘላለም የይሖዋ እንግዶች ሆናችሁ ኑሩ!
8 ‘በልባቸው እውነትን የሚናገሩ’ ሰዎች በድብቅ የአምላክን ሕግጋት እየጣሱ በሰዎች ፊት ታዛዥ ለመምሰል አይሞክሩም። (ኢሳ. 29:13) ከማታለል ይቆጠባሉ። አታላይ ሰው አንዳንድ የይሖዋ መመሪያዎች ጥበብ ያዘሉ መሆናቸውን መጠራጠር ሊጀምር ይችላል። (ያዕ. 1:5-8) ያን ያህል አስፈላጊ እንዳልሆኑ በሚሰሙት ጉዳዮች ይሖዋን ላይታዘዝ ይችላል። አለመታዘዙ ምንም መዘዝ እንዳላስከተለበት ከተሰማው ደግሞ የይሖዋን ሕግጋት የባሰ ለመጣስ ሊደፋፈር ይችላል፤ አምልኮቱም የግብዝነት ይሆንበታል። (መክ. 8:11) እኛ ግን በሁሉም ነገር ሐቀኞች መሆን እንፈልጋለን።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
ኢሳይያስ ይሖዋ ስለሚያከናውነው ‘እንግዳ ሥራ’ ይተነብያል
19 ይሁንና ይሖዋ ቀጥሎ የሚናገረው ስለ ምንድን ነው? “ዳዊት ለሰፈረባት ከተማ ለአርኤል ወዮላት! ዓመት በዓመት ላይ ጨምሩ፣ በዓላትም ይመለሱ። አርኤልንም አስጨንቃለሁ፣ ልቅሶና ዋይታም ይሆንባታል፤ እንደ አርኤልም [“የአምላክ መሠዊያም፣” NW] ትሆንልኛለች።” (ኢሳይያስ 29:1, 2) “አርኤል” ማለት “የአምላክ መሠዊያ” ማለት ሊሆን ይችላል። እዚህ ላይ ደግሞ የሚያመለክተው ኢየሩሳሌምን መሆኑን ከሁኔታው ለመረዳት ይቻላል። መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያና ቤተ መቅደሱ የሚገኙት በኢየሩሳሌም ነበር። አይሁዳውያኑ በዚህ ቦታ በዓላት ማክበራቸውንና መሥዋዕት ማቅረባቸውን እንደ ልማድ ቀጥለውበት የነበረ ቢሆንም ይሖዋ በአምልኮአቸው አልተደሰተም። (ሆሴዕ 6:6) ከዚህ ይልቅ ከተማዋ ራሷ “መሠዊያ” እንደምትሆን ተናግሯል። ልክ እንደ መሠዊያ ደም ሊፈስስባትና እሳት ሊነድድባት ነው። ይሖዋ ይህ እንዴት እንደሚሆን ሳይቀር ይናገራል፦ “በዙሪያሽም እሰፍራለሁ፣ በቅጥርም ከብቤ አስጨንቅሻለሁ፣ አምባም በላይሽ አቆማለሁ። ትዋረጂማለሽ፣ በመሬትም ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፣ ቃልሽም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፤ ድምፅሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምፅ ይሆናል፣ ቃልሽም ከአፈር ወጥቶ ይጮኻል።” (ኢሳይያስ 29:3, 4) ይህ ትንቢት በ607 ከዘአበ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ፍጻሜውን ያገኘው ባቢሎናውያን ከተማዋን ባጠፉና ቤተ መቅደስዋንም በእሳት ባቃጠሉ ጊዜ ነው። ኢየሩሳሌም ከተገነባችበት አፈር ጋር ተቀላቅላለች።
ከየካቲት 2-8
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት ኢሳይያስ 30-32
በይሖዋ ክንፎች ሥር ተሸሸጉ
ይሖዋ መሸሸጊያችን ነው
7 ይሖዋ መሸሸጊያችን ስለሆነ ከሚከተሉት ቃላት ማጽናኛ እናገኛለን፦ “በላባዎቹ ይጋርድሃል፤ በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ ታማኝነቱ [“እውነተኝነቱ፣” NW ] ጋሻና መከታ ይሆንሃል።” (መዝሙር 91:4 አ.መ.ት) አምላክ ጫጩቶቿን ለመጠበቅ በላያቸው ላይ እንደምታንዣብብ ወፍ ይጠብቀናል። (ኢሳይያስ 31:5) ‘በላባዎቹ ይጋርደናል።’ ብዙውን ጊዜ ‘ላባ’ የሚለው ቃል የወፎችን ክንፍ ያመለክታል። አንዲት ወፍ ጫጩቶቿን ከአዳኝ አውሬ ለመጠበቅ በክንፎቿ ትከልላቸዋለች። እኛም እውነተኛውን የክርስትና ድርጅት እንደ መሸሸጊያ አድርገን በመጠጋት እንደ አንዲት የወፍ ጫጩት ምሳሌያዊ በሆነው በይሖዋ ላባ ሥር ተከልለን እንኖራለን።—ሩት 2:12፤ መዝሙር 5:1, 11
በመከራ ወቅት ይሖዋ ይረዳሃል
13 ማድረግ ያለብን ነገር። ራስህን ላለማግለል ጥረት አድርግ። ራሳችንን ስናገል እይታችን ስለሚጠብ ስለ ራሳችንና ስላጋጠመን ችግር ብቻ ማሰብ ልንጀምር እንችላለን። እንዲህ ያለው አስተሳሰብ በምናደርጋቸው ውሳኔዎችም ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። (ምሳሌ 18:1) እርግጥ ነው፣ ሁላችንም በተለይ ከባድ መከራ ሲያጋጥመን ብቻችንን መሆን የሚያስፈልገን ጊዜ ይኖራል። ይሁንና ለረጅም ጊዜ ራሳችንን አግልለን ከቆየን ይሖዋ እኛን ለመደገፍ የሚጠቀምበትን መንገድ ልንዘጋ እንችላለን። እንግዲያው በመከራ ውስጥ ስትሆን ከባድ ቢሆንም እንኳ የቤተሰቦችህን፣ የጓደኞችህንና የሽማግሌዎችን እርዳታ ተቀበል። ይሖዋ የሚደግፍህ እነሱን ተጠቅሞ እንደሆነ አስታውስ።—ምሳሌ 17:17፤ ኢሳ. 32:1, 2
“ያጠነክራችኋል”—እንዴት?
19 ተስፋህን ማጠናከር የምትችለው እንዴት ነው? ለምሳሌ ተስፋህ በምድር ላይ ለዘላለም መኖር ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገነት የሚሰጠውን መግለጫ አንብበህ አሰላስልበት። (ኢሳ. 25:8፤ 32:16-18) በአዲሱ ዓለም ውስጥ ሕይወት ምን እንደሚመስል በዓይነ ሕሊናህ ሣል። በዚያ ስትኖር ይታይህ። በአካባቢህ ማን አለ? ምን ዓይነት ድምፆች አሉ? አንተስ ምን ይሰማሃል? ተስፋህ ሕያው ሆኖ እንዲታይህ በጽሑፎቻችን ላይ የወጡ ገነትን የሚያሳዩ ሥዕሎችን ወይም የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ተመልከት። ከእነዚህ የሙዚቃ ቪዲዮዎች መካከል ያ አዲስ ዘመን፣ ሩቅ አይደለም ያ ጊዜ እና ያ ቀን ይታይህ የሚሉት መዝሙሮች ይገኙበታል። አዲስ ዓለም እንደሚመጣ ባለን ተስፋ ላይ ካተኮርን አሁን ያሉብን ችግሮች “ጊዜያዊና ቀላል” ይሆኑልናል። (2 ቆሮ. 4:17) ይሖዋ በተስፋው አማካኝነት ጥንካሬ ይሰጥሃል።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
ይሖዋን በመተማመን ተጠባበቁ
17 ኢሳይያስ ንግግሩን በመቀጠል አድማጮቹን መከራ እንደሚመጣ ያስታውሳቸዋል። ሕዝቡ “የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ” ይቀበላሉ። (ኢሳይያስ 30:20ሀ) በከበባው ወቅት የሚደርስባቸው መከራና ጭቆና የእንጀራና የውኃ ያህል የተለመደ ነገር ይሆናል። ያም ሆኖ ግን ይሖዋ ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች ለመታደግ ዝግጁ ነው። “[“ታላቅ፣” NW] አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፤ ዓይኖችህ ግን [“ታላቅ፣” NW] አስተማሪህን ያያሉ፣ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ፦ መንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ።”—ኢሳይያስ 30:20ለ, 21
ከየካቲት 9-15
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት ኢሳይያስ 33-35
“እሱ የዘመንህ መተማመኛ ነው”
በመከራ ወቅት ይሖዋ ይረዳሃል
7 ተፈታታኙ ነገር። ከባድ መከራ ሲያጋጥመን ስሜታችን፣ አስተሳሰባችን እንዲሁም ለተለያዩ ነገሮች የምንሰጠው ምላሽ እንደ ቀድሞው ሚዛኑን የጠበቀ ላይሆን ይችላል። በስሜት ማዕበል እንደምንናወጥ ሆኖ ሊሰማን ይችላል። ቀደም ሲል የተጠቀሰችው አና፣ ሉዊስ ከሞተ በኋላ የተለያዩ ዓይነት ስሜቶች ይፈራረቁባት እንደነበር ተናግራለች። እንዲህ ብላለች፦ “የባዶነት ስሜት ሲሰማኝ ለራሴ ማዘን እጀምራለሁ። በተጨማሪም እሱ በመሞቱ እናደዳለሁ።” ከዚህም ሌላ አና ብቸኝነት ይሰማት ነበር፤ እንዲሁም ሉዊስ ጥሩ አድርጎ ይወጣቸው የነበሩት ኃላፊነቶች እሷ ላይ በመውደቃቸው ትበሳጭ ነበር። አንዳንድ ጊዜ፣ በማዕበል በሚናወጥ ባሕር ውስጥ እንዳለች ሆኖ ይሰማት ነበር። እንዲህ ያሉ ስሜቶች ሲያናውጡን ይሖዋ የሚረዳን እንዴት ነው?
8 ይሖዋ የሚያደርግልን ነገር። ይሖዋ አጽንቶ እንደሚያቆመን ቃል ገብቶልናል። (1 ጴጥሮስ 5:10ን አንብብ።) አንድ መርከብ ማዕበል ሲያጋጥመው በኃይል ሊወዛወዝ ይችላል። ብዙ መርከቦች እንዲህ ያለውን ነውጥ ለመቀነስ የሚያስችል በሁለቱም ወገን ወደ ውኃው ውስጥ የሚገባ ክንፍ አላቸው። ይህ የመርከቡ ክፍል መርከቡ በኃይል እንዳይናወጥ ያደርገዋል፤ ይህም ተሳፋሪዎቹ ጉዳት እንዳይደርስባቸውና ተመችቷቸው እንዲጓዙ ያስችላል። ይሁንና እነዚህ ክንፎች ይበልጥ ውጤታማ የሚሆኑት መርከቡ ወደፊት እየተጓዘ ከሆነ ነው። በተመሳሳይም በመከራ ወቅት በታማኝነት ወደፊት መጓዛችንን ስንቀጥል ይሖዋ አጽንቶ ያቆመናል።
ፈተናዎች እየደረሱባችሁም ደስታችሁን ጠብቃችሁ መኖር የምትችሉት እንዴት ነው?
10 መፍትሔው፦ ይሖዋ ጥበብ እንዲሰጠን መለመን። የሚደርስብንን ፈተና በደስታ ለመቋቋም በመጀመሪያ ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ የሚያስችል ጥበብ እንዲሰጠን ይሖዋን በጸሎት መለመን ይኖርብናል። (ያዕቆብ 1:5ን አንብብ።) ይሖዋ ለጸሎታችን ወዲያውኑ ምላሽ እንዳልሰጠን ቢሰማን ምን ማድረግ ይኖርብናል? ያዕቆብ ‘አምላክን ያለማሰለስ መለመን’ እንዳለብን ተናግሯል። ይሖዋ፣ ጥበብ እንዲሰጠን በተደጋጋሚ ስንለምነው እንደጨቀጨቅነው አይሰማውም። እንዲህ በማድረጋችን አይነቅፈንም። የሰማዩ አባታችንን የገጠሙንን ፈተናዎች መቋቋም የሚያስችል ጥበብ እንዲሰጠን ስንለምነው ‘በልግስና ይሰጠናል።’ (መዝ. 25:12, 13) ያሉብንን ፈተናዎች ያያል፣ ያዝንልናል እንዲሁም ሊረዳን ይፈልጋል። በእርግጥም ይህ ለደስታችን ምክንያት የሚሆን ነገር ነው! ይሁንና ይሖዋ ጥበብ የሚሰጠን እንዴት ነው?
11 ይሖዋ በቃሉ አማካኝነት ጥበብ ይሰጠናል። (ምሳሌ 2:6) ይህን ጥበብ ለማግኘት የአምላክን ቃልና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን ማጥናት አለብን። ሆኖም እውቀት ከማከማቸት የበለጠ ነገር ማድረግ ይጠበቅብናል። አምላክ የሚሰጠንን ምክር ተግባራዊ በማድረግ የአምላክ ጥበብ በሕይወታችን ውስጥ እንዲሠራ ማድረግ አለብን። ያዕቆብ “ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ . . . ሰሚዎች ብቻ አትሁኑ” በማለት ጽፏል። (ያዕ. 1:22) የአምላክን ምክር ተግባራዊ ስናደርግ ይበልጥ ሰላማዊ፣ ምክንያታዊና መሐሪ እንሆናለን። (ያዕ. 3:17) እነዚህ ባሕርያት ምንም ዓይነት ፈተና ቢደርስብን ደስታችንን ጠብቀን እንድንኖር ይረዱናል።
‘በዚያም የሚቀመጥ ታምሜአለሁ አይልም’
21 ይሁንና የኢሳይያስ ትንቢት በዘመናችንም ተፈጻሚነት ይኖረዋል። ዛሬ ያለው የይሖዋ ሕዝብም መንፈሳዊ ፈውስ አግኝቷል። ነፍስ አትሞትም፣ ሥላሴ እና የሲኦል እሳት የሚሉትን ከመሳሰሉት የሐሰት ትምህርቶች ነፃ ወጥተዋል። ከሥነ ምግባር ብልግና እንዲላቀቁና ጥሩ ውሳኔዎችን እንዲያደርጉ የሚረዳቸውን የግብረገብ መመሪያ ያገኛሉ። እንዲሁም ለኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት ምሥጋና ይግባውና በአምላክ ፊት ንጹሕ አቋም ኖሯቸው ንጹህ ሕሊና ለማግኘት በቅተዋል። (ቆላስይስ 1:13, 14፤ 1 ጴጥሮስ 2:24፤ 1 ዮሐንስ 4:10) ይህ መንፈሳዊ ፈውስ አካላዊ ጥቅምም አለው። ለምሳሌ ያህል ክርስቲያኖች ከፆታ ብልግናና ከትንባሆ ውጤቶች በመራቃቸው በፆታ ግንኙነት ከሚተላለፉ በሽታዎችና ከአንዳንድ የካንሰር ዓይነቶች ተጠብቀዋል።—1 ቆሮንቶስ 6:18፤ 2 ቆሮንቶስ 7:1
22 ከዚህም በተጨማሪ በኢሳይያስ 33:24 ላይ የሚገኙት ቃላት ከአርማጌዶን በኋላ በሚኖረው የአምላክ አዲስ ዓለም ውስጥም ታላቅ ፍጻሜ ይኖራቸዋል። የሰው ልጅ በመሲሐዊው መንግሥት አገዛዝ ሥር ከሚያገኘው መንፈሳዊ ፈውስ በተጨማሪ ታላቅ አካላዊ ፈውስ ያገኛል። (ራእይ 21:3, 4) የሰይጣን ክፉ የነገሮች ሥርዓት ከጠፋ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ኢየሱስ ምድር ሳለ ያከናወናቸውን ዓይነት ተዓምራት በምድር ዙሪያ እንደሚከናወኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ዕውራን ያያሉ፣ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፣ አንካሳውም በእግሮቹ ይራመዳል! (ኢሳይያስ 35:5, 6) ይህም ከታላቁ መከራ በሕይወት የተረፉት ሰዎች በሙሉ ምድርን ወደ ገነትነት በመለወጡ ታላቅ ሥራ መካፈል የሚችሉበትን አጋጣሚ ይከፍታል።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
‘በቅድስና ጎዳና’ ላይ መጓዛችሁን ቀጥሉ
8 አንዳንዶች እንዲህ ብለው ያስቡ ይሆናል፦ ‘የሚገርም ታሪክ ነው። ይሁንና በሺዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት አይሁዳውያን ምን እንዳጋጠማቸው ማወቃችን የሚጠቅመን ነገር አለ?’ አዎ፣ አለ። ምክንያቱም እኛም በምሳሌያዊ ሁኔታ ‘በቅድስና ጎዳና’ ላይ እየተጓዝን ነው። ቅቡዓንም ሆንን “ሌሎች በጎች” በቅድስና ጎዳና ላይ መጓዛችንን መቀጠል ይኖርብናል። ምክንያቱም ይህ መንገድ በመንፈሳዊው ገነት በኩል አድርጎ ወደፊት መንግሥቱ ወደሚያመጣቸው በረከቶች ይወስደናል። (ዮሐ. 10:16) ከ1919 ዓ.ም. አንስቶ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች ከታላቂቱ ባቢሎን ማለትም ከሐሰት ሃይማኖት ወጥተው በዚህ ምሳሌያዊ መንገድ ላይ መጓዝ ጀምረዋል። አንተም ከእነሱ መካከል እንደምትገኝ ጥያቄ የለውም። ይህ መንገድ የተከፈተው ከመቶ ዓመት ገደማ በፊት ቢሆንም አውራ ጎዳናውን የማዘጋጀቱ ሥራ ከዚያ በፊት ባሉት በርካታ መቶ ዘመናት ሲከናወን ቆይቷል።
ከየካቲት 16-22
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት ኢሳይያስ 36-37
“የተናገሩትን ቃል በመስማትህ አትፍራ”
it “ሕዝቅያስ” ቁ. 1 አን. 14
ሕዝቅያስ
ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን ለመያዝ ያደረገው ሙከራ ከሸፈ። ሕዝቅያስ እንደጠበቀው ሰናክሬም በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ወሰነ። ሰናክሬም በቅጥር የታጠረችውን የለኪሶ ከተማ ከሠራዊቱ ጋር ከቦ በነበረበት ወቅት የሠራዊቱን የተወሰነ ክፍል ከአንዳንድ የጦር አመራሮች ጋር በመላክ ኢየሩሳሌም እጅ እንድትሰጥ እንዲጠይቁ አደረገ። ቡድኑን ወክሎ ይናገር የነበረው ዕብራይስጥ አቀላጥፎ መናገር የሚችለው ራብሻቅ (ይህ የሰውየው ስም ሳይሆን ወታደራዊ ማዕረጉ ነው) ነበር። እሱም ድምፁን ከፍ አድርጎ በሕዝቅያስ ላይ አፌዘ፤ እንዲሁም የሌሎች ብሔራት አማልክት ምድራቸውን ከአሦር ንጉሥ ማስጣል እንዳልቻሉ ሁሉ ይሖዋም ኢየሩሳሌምን ሊታደጋት እንደማይችል በመግለጽ ይሖዋን ተገዳደረ።—2ነገ 18:13-35፤ 2ዜና 32:9-15፤ ኢሳ 36:2-20
ንጉሡ ያሳየው እምነት ተካሰ
10 ቀጥሎ ደግሞ ራፋስቂስ አይሁዳውያኑን በወታደራዊ ኃይሉ እጅግ እንደሚበልጣቸውም አሳሰባቸው። “የሚቀመጡባቸውንም ሰዎች ማግኘት ቢቻልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረሶች እሰጥሃለሁ” በማለት በትዕቢት ተገዳደራቸው። (ኢሳይያስ 36:8) እንደ እውነቱ ከሆነ ግን የይሁዳ የሰለጠኑ ፈረሰኞች ብዙ ወይም ጥቂት መሆናቸው የሚያመጣው ለውጥ ነበርን? የይሁዳ መዳን የተመካው በወታደራዊ ጥንካሬዋ ላይ ባለመሆኑ ይህ የሚያመጣው ለውጥ አልነበረም። ምሳሌ 21:31 ይህንን ጉዳይ ሲገልጽ “ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ ድል [“መዳን፣” NW] ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” ይላል። ከዚያም ራፋስቂስ የይሖዋ በረከት ያለው ከአይሁዳውያን ጋር ሳይሆን ከአሦራውያን ጋር እንደሆነ ሊያስረዳ ሞከረ። ይህ ባይሆንማ ኖሮ አሦራውያን ይህንን ያህል ወደ ይሁዳ ክልል ዘልቀው መግባት ባልቻሉ ነበር ሲል ተከራክሯል።—ኢሳይያስ 36:9, 10
ንጉሡ ያሳየው እምነት ተካሰ
13 ራፋስቂስ ከነገር ኮሮጆው ውስጥ ሌላ የቃላት መርዙን ይመዝዛል። ሕዝቅያስ “እግዚአብሔር ያድነናል” ቢላቸው እንኳ እንዳያምኑት አይሁዳውያኑን አስጠነቀቀ። ራፋስቂስ የሰማርያ አማልክት አሥሩን ነገድ በአሦር እጅ ከመውደቅ ሊያስጥሉ እንዳልቻሉ አሳሰባቸው። አሦር ስላሸነፋቸው ሌሎች የአሕዛብ አማልክትስ ምን ለማለት ይቻላል? “የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ?” ሲል ጠየቀ። “የሴፈርዋይም አማልክት ወዴት አሉ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን?”—ኢሳይያስ 36:18-20
14 እርግጥ የሐሰት አማልክትን የሚያገለግለው ራፋስቂስ አንድ ያልተረዳው ነገር ቢኖር በከሃዲዋ ሰማርያና በሕዝቅያስ ትተዳደር በነበረችው ኢየሩሳሌም መካከል ትልቅ ልዩነት መኖሩን ነው። የሰማርያ የሐሰት አማልክት የአሥሩን ነገድ መንግሥት የሚያስጥሉበት ምንም ኃይል አልነበራቸውም። (2 ነገሥት 17:7, 17, 18) በሌላ በኩል ግን በሕዝቅያስ የምትመራው ኢየሩሳሌም ለሐሰት አምልኮ ጀርባዋን ሰጥታ ይሖዋን ወደ ማገልገል ዘወር ብላ ነበር። ይሁን እንጂ ሦስቱ የአይሁዳውያኑ ወኪሎች ይህን ጉዳይ ለራፋስቂስ ለማስረዳት አልሞከሩም። “እነርሱም ዝም አሉ፣ አንዳችም አልመለሱለትም፤ ንጉሡ እንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና።” (ኢሳይያስ 36:21) ኤልያቄም፣ ሳምናስ እና ዮአስ ወደ ሕዝቅያስ ተመልሰው ስለ ራፋስቂስ ቃል ኦፊሴላዊ ሪፖርት አቀረቡ።—ኢሳይያስ 36:22
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
it “ልጓም” አን. 4
ልጓም
ይሖዋ ለአሦር ንጉሥ ለሰናክሬም “ስናጌን በአፍንጫህ፣ ልጓሜንም በአፍህ አስገባለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስ አደርግሃለሁ” ብሎታል። (2ነገ 19:28፤ ኢሳ 37:29) ሰናክሬም በውዴታ ሳይሆን በይሖዋ እጅ ተገዶ፣ ኢየሩሳሌምን ለመክበብ የነበረውን ዕቅድ ትቶ ወደ ነነዌ ተመለሰ፤ ከዚያም የገዛ ልጆቹ ገደሉት። (2ነገ 19:32-37፤ ኢሳ 37:33-38) ይሖዋ በጠላት ብሔራት መንጋጋ ውስጥ ልጓም ያስገባል ሲባል በልጓም አማካኝነት እንስሳትን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ማድረግ እንደሚቻለው ሁሉ ይሖዋም እነዚህን ብሔራት እንደሚቆጣጠር ያመለክታል።—ኢሳ 30:28
ከየካቲት 23–መጋቢት 1
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት ኢሳይያስ 38-40
“መንጋውን እንደ እረኛ ይንከባከባል”
መጽሐፍ ቅዱስ ስላጻፈው አካል ምን ይነግረናል?
3 ኢሳይያስ 40:8ን አንብብ። የአምላክ ቃል ታማኝ ለሆኑ ወንዶችና ሴቶች በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ጥበብ ያዘለ መመሪያ ሲሰጥ ቆይቷል። ይህ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? ይህን ጥያቄ ማንሳታችን ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም ቅዱሳን መጻሕፍት የተጻፉት ከረጅም ጊዜ በፊት ነው። የተጻፉባቸው ነገሮችም ሊበላሹ የሚችሉ ስለሆኑ ከበኩረ ጽሑፉ መካከል እስከ ዘመናችን የዘለቀ አንድም ቅጂ የለም። ሆኖም ይሖዋ ቅዱስ ጽሑፉ በእጅ እንዲገለበጥ አድርጓል። ገልባጮቹ ፍጹማን ባይሆኑም ሥራቸውን ያከናወኑት በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ አንድ ምሁር የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍትን አስመልክተው እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፦ “መልእክቱ ይህን ያህል ተጠብቆ የቆየ አንድም ጥንታዊ መጽሐፍ የለም ብንል ማጋነን አይሆንም።” ስለዚህ ቅዱሳን መጻሕፍት ከተጻፉ ረጅም ጊዜ ቢያልፍም፣ የተጻፉበት ነገር ሊበላሽ የሚችል ቢሆንም እንዲሁም ገልባጮቹ ፍጹማን ባይሆኑም በዛሬው ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ የምናነብባቸው ቃላት ያጻፈውን አካል ማለትም የይሖዋን ሐሳብ በትክክል እንደሚያስተላልፉ መተማመን እንችላለን።
4 ይሖዋ ‘የመልካም ስጦታ ሁሉና የፍጹም ገጸ በረከት ሁሉ’ ምንጭ ነው። (ያዕ. 1:17) ይሖዋ ከሰጠን ግሩም ስጦታዎች መካከል አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። አንድ ስጦታ ሰጪው ስለ እኛም ሆነ ስለሚያስፈልገን ነገር ምን ያህል እንደሚያውቅ ይነግረናል። መጽሐፍ ቅዱስን ከሰጠን አካል ጋር በተያያዘም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። ይህን ስጦታ ስንመረምር ስለ ይሖዋ ብዙ እንማራለን። እኛንም ሆነ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ምን ያህል እንደሚያውቅ እንረዳለን። በዚህ ርዕስ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚከተሉት ሦስት የይሖዋ ባሕርያት ምን እንደሚያስገነዝበን እንመረምራለን፦ ስለ ጥበቡ፣ ስለ ፍትሑና ስለ ፍቅሩ። በቅድሚያ መጽሐፍ ቅዱስ የይሖዋን ጥበብ የሚያንጸባርቀው እንዴት እንደሆነ እንመልከት።
‘መጠጊያችን የሆነው አምላክ’—ለመጠበቅ የሚጠቀምበት ኃይል
7 ይሖዋም ልክ እንደ አንድ እረኛ እንደሚጠብቀን ቃል ገብቶልናል። (ሕዝቅኤል 34:11-16) በዚህ መጽሐፍ ሁለተኛ ምዕራፍ ላይ የተብራራውን ኢሳይያስ 40:11ን መለስ ብለህ አስታውስ። ይህ ጥቅስ ይሖዋን እንዲህ በማለት ይገልጸዋል፦ “መንጋውን እንደ እረኛ ይንከባከባል። ግልገሎቹን በክንዱ ይሰበስባል፤ በእቅፉም ይሸከማቸዋል።” ግልገሏ እረኛው ‘እንዲያቅፋት’ የምታደርገው እንዴት ነው? ወደ እረኛው ተጠግታ እግሩን ትታከከዋለች። ሆኖም ጎንበስ ብሎ በማንሳት እቅፍ የሚያደርጋት እረኛው ነው። ታላቁ እረኛ እኛን ለመጠበቅና ለመንከባከብ ፈቃደኛ መሆኑን የሚያሳይ እንዴት ያለ ግሩም መግለጫ ነው!
‘ለደከመው ኃይል ይሰጣል’
4 ኢሳይያስ 40:26ን አንብብ። በአጽናፈ ዓለም ውስጥ የሚገኙትን ከዋክብት በሙሉ መቁጠር የቻለ ሰው የለም። የሳይንስ ሊቃውንት፣ ፍኖተ ሐሊብ በተባለው በእኛ ጋላክሲ ውስጥ ብቻ እስከ 400 ቢሊዮን የሚደርሱ ከዋክብት ሊገኙ እንደሚችሉ ይናገራሉ። የሚገርመው ይሖዋ ለእያንዳንዱ ኮከብ ስም ሰጥቶታል። ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን? ይሖዋ፣ ሕይወት የሌለውን እያንዳንዱን ፍጥረቱን በሚገባ የሚያውቀው ከሆነ በፍቅር ተነሳስተው ለሚያገለግሉት ሕዝቦቹማ የበለጠ ትኩረት እንደሚሰጥ መገመት አያዳግትም! (መዝ. 19:1, 3, 14) አባታችን የእኛን ማንነት በሚገባ ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ “የራሳችሁ ፀጉር እንኳ አንድ ሳይቀር ተቆጥሯል” ይላል። (ማቴ. 10:30) መዝሙራዊውም “ይሖዋ ነቀፋ የሌለባቸውን ሰዎች የሕይወት ጎዳና ያውቃል” የሚል ማረጋገጫ ሰጥቶናል። (መዝ. 37:18) ይሖዋ በአሁኑ ጊዜ እያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎችን የሚመለከት ከመሆኑም በላይ እያንዳንዱን ፈተና ለመወጣት የሚያስችል ብርታት ይሰጠናል።
5 ኢሳይያስ 40:28ን አንብብ። ይሖዋ ገደብ የሌለው ኃይል ያለው አምላክ ነው። ይህን በምሳሌ ለማስረዳት ፀሐይ ያላትን ኃይል እንመልከት። የሳይንስ ጽሑፍ አዘጋጅ የሆኑት ዴቪድ ቦዳኒስ እንደገለጹት ፀሐይ በእያንዳንዱ ሴኮንድ የምታመነጨው ኃይል፣ በቢሊዮኖች ከሚቆጠሩ የአቶሚክ ቦምቦች ፍንዳታ ጋር የሚመጣጠን ነው። ሌላ ተመራማሪ እንዳሰሉት ደግሞ ፀሐይ በአንድ ሴኮንድ ብቻ የምታመነጨው ኃይል፣ የዓለም ሕዝብ ለ200,000 ዓመታት የሚያስፈልገውን የኃይል መጠን ማሟላት ይችላል! ለፀሐይ ይህን ሁሉ ኃይል የሰጣት አምላክ፣ እኛም የሚያጋጥመንን ማንኛውንም ችግር ለመቋቋም የሚያስችል ብርታት እንደሚሰጠን ምንም ጥርጥር የለውም!
6 ኢሳይያስ 40:29ን አንብብ። ይሖዋን ማገልገል ታላቅ ደስታ ያስገኛል። ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱን “ቀንበሬን ተሸከሙ፤ . . . ለራሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ። ቀንበሬ ልዝብ፣ ሸክሜም ቀላል ነውና” ብሏቸዋል። (ማቴ. 11:28-30) ብዙዎቻችን የዚህን አባባል እውነተኝነት በሕይወታችን ተመልክተናል! አንዳንድ ጊዜ ወደ ጉባኤ ስብሰባ ለመሄድ ወይም በመስክ አገልግሎት ለመካፈል ከቤታችን ስንወጣ በጣም ዝለን ሊሆን ይችላል። ወደ ቤታችን የምንመለሰው ግን መንፈሳችን ታድሶ እንዲሁም የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለመቋቋም የሚያስችል ኃይል አግኝተን ነው። በእርግጥም የኢየሱስ ቀንበር ልዝብ ነው!
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
“ሕዝቤን አጽናኑ”
7 የዚህ ትንቢት ፍጻሜ በስድስተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ የተከናወነው መልሶ ማቋቋም ብቻ ነው ማለት አይደለም። በአንደኛው መቶ ዘመንም ትንቢቱ ተፈጻሚነት ነበረው። መጥምቁ ዮሐንስ በኢሳይያስ 40:3 ፍጻሜ መሠረት “በምድረ በዳ የሚጮኽ” ሰው ድምፅ ሆኖ ብቅ ብሏል። (ሉቃስ 3:1-6) ዮሐንስ የኢሳይያስ ቃላት ለእርሱ እንደሚሠሩ በመንፈስ አነሳሽነት ተናግሯል። (ዮሐንስ 1:19-23) ከ29 እዘአ አንስቶ ዮሐንስ ለኢየሱስ ክርስቶስ መንገዱን አዘጋጅቷል። ዮሐንስ አስቀድሞ ያሰማው የነበረው አዋጅ ሕዝቡ ቃል የተገባለትን መሲህ ይሰሙና ይከተሉ ዘንድ በጉጉት እንዲጠባበቁ አነሳስቷቸዋል። (ሉቃስ 1:13-17, 76) ይሖዋ ንስሐ የሚገቡትን ሰዎች በኢየሱስ አማካኝነት በአምላክ መንግሥት ሥር ብቻ ሊገኝ ወደሚችለው ነፃነት ይኸውም ከኃጢአትና ከሞት ነፃ ወደ መሆን ይመራቸዋል። (ዮሐንስ 1:29፤ 8:32) በ1919 የመንፈሳዊ እስራኤል ቀሪዎች ከታላቂቱ ባቢሎን ነፃ ወጥተው ወደ ንጹሕ አምልኮ ሲመለሱ የኢሳይያስ ቃላት ታላቅ ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል።