የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 38
  • አምላክ ለእኔ ያለው ፈቃድ ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ለእኔ ያለው ፈቃድ ምንድን ነው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • ስለ እውነተኛው አምላክ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የሕይወት ትርጉሙ ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት አጠናክር
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 38

አምላክ ለእኔ ያለው ፈቃድ ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አምላክ እሱን እንድታውቀው፣ እንድትቀርበው እንዲሁም እንድትወድደውና በሙሉ ልብህ እንድታገለግለው ይፈልጋል። (ማቴዎስ 22:37, 38፤ ያዕቆብ 4:8) የኢየሱስን ሕይወትና ያስተማረውን ትምህርት በመመርመር የአምላክን ፈቃድ ማድረግ የምትችለው እንዴት እንደሆነ ማወቅ ትችላለህ። (ዮሐንስ 7:16, 17) ኢየሱስ ስለ አምላክ ፈቃድ በማስተማር ብቻ ሳይወሰን ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ኖሯል። እንዲያው ኢየሱስ በሕይወቱ ውስጥ ትልቁን ቦታ የያዘውን ነገር አስመልክቶ ሲናገር “የመጣሁት የእኔን ፈቃድ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ነው” ብሏል።​—ዮሐንስ 6:38

አምላክ ለእኔ ያለውን ፈቃድ በራእይ ወይም ለየት ባለ ምልክት ያሳውቀኛል ብዬ መጠበቅ ይኖርብኛል?

በፍጹም፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ለሰው ልጆች የሰጠውን መልእክት ይዟል። ‘ለማንኛውም መልካም ሥራ በሚገባ እንድንታጠቅ’ የሚያስችሉ ነገሮችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን። (2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17) አምላክ፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ‘የማሰብ ችሎታህን’ ተጠቅመህ ለአንተ ያለውን ፈቃድ እንድታውቅ ይፈልጋል።​—ሮም 12:1, 2፤ ኤፌሶን 5:17

በእርግጥ የአምላክን ፈቃድ መፈጸም እችላለሁ?

እንዴታ! ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ‘የአምላክ ትእዛዛት ከባዶች አይደሉም’ ይላል። (1 ዮሐንስ 5:3) እንዲህ ሲባል ግን የአምላክን ትእዛዛት መፈጸም ሁልጊዜ ቀላል ነው ማለት አይደለም። ይሁን እንጂ ይህን ማድረግህ ከሚያስገኝልህ ጥቅም አንጻር ማንኛውንም መሥዋዕት ብትከፍል የሚያስቆጭ አይሆንም። ኢየሱስ “ደስተኞችስ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው!” በማለት ተናግሯል።​—ሉቃስ 11:28

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ