የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbv ርዕስ 49
  • 2 ቆሮንቶስ 12:9—“ጸጋዬ ይበቃሃል”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 2 ቆሮንቶስ 12:9—“ጸጋዬ ይበቃሃል”
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የ2 ቆሮንቶስ 12:9 ትርጉም
  • የ2 ቆሮንቶስ 12:9 አውድ
  • ከአምላክ ለተቀበልነው ጸጋ አመስጋኝ መሆን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • ማንኛውንም ፈተና መቋቋም እንችላለን!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • የሰው ልጅ ደካማነት የይሖዋን ኃይል አጉልቶ ያሳያል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ስለ አምላክ ጸጋ የሚገልጸውን ምሥራች አውጁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
ijwbv ርዕስ 49

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው

2 ቆሮንቶስ 12:9—“ጸጋዬ ይበቃሃል”

“ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ምክንያቱም ኃይሌ ፍጹም የሚሆነው በምትደክምበት ጊዜ ነው።”—2 ቆሮንቶስ 12:9 አዲስ ዓለም ትርጉም

“ጸጋዬ ይበቃሃል፣ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና።”—2 ቆሮንቶስ 12:9 የ1954 ትርጉም

የ2 ቆሮንቶስ 12:9 ትርጉም

አምላክ፣ ሐዋርያው ጳውሎስ የሚያጋጥሙትን ተፈታታኝ ሁኔታዎችና ያሉበትን የአቅም ገደቦች ለመቋቋም የሚያስፈልገውን ብርታት እንደሚሰጠው ቃል ገብቶለታል።

“ጸጋዬ ይበቃሃል።” ጳውሎስ በተደጋጋሚ ላቀረበው ጸሎት አምላክ የሰጠው ምላሽ “ደግነቴ ይበቃሃል” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። በሌላ አባባል አምላክ ያሳየው አስደናቂ ደግነት፣ ጳውሎስ ያጋጠሙትን ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንዲወጣ ለመርዳት በቂ ነበር። እንዴት? “ይገባናል የማንለው ደግነት” ወይም “ጸጋ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል፣ ተቀባዩ ይገባኛል ብሎ ሊጠይቅ የማይችለውን አምላክ በልግስና ተነሳስቶ በነፃ የሚሰጠውን ስጦታ ያመለክታል። ከጻፋቸው ደብዳቤዎች መረዳት እንደሚቻለው ጳውሎስ ከአምላክ ጸጋ በእጅጉ ተጠቅሟል። ቀደም ሲል ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረ ቢሆንም አምላክ ብርታት ስለሰጠው ባሕርይውን መቀየርና ሌሎች ሰዎች ክርስቲያን እንዲሆኑ መርዳት ችሏል። (1 ቆሮንቶስ 15:9, 10፤ 1 ጢሞቴዎስ 1:12-14) ጳውሎስ ያጋጠመውን ማንኛውንም ችግር ወይም ተፈታታኝ ሁኔታ በአምላክ እርዳታ መወጣት እንደሚችል መተማመን ይችላል።

“ምክንያቱም ኃይሌ ፍጹም የሚሆነው በምትደክምበት ጊዜ ነው።” ይሖዋ፣a ኃይሉ ይበልጥ የሚታየው ደካማና ኃጢአተኛ በሆኑ ሰዎች ላይ እንደሆነ ለጳውሎስ አስታውሶታል። (2 ቆሮንቶስ 4:7፤ 12:8) ክርስቲያኖች ድክመታቸውን አምነው በመቀበል የይሖዋን እርዳታ ለማግኘት ጥረት ሲያደርጉ የአምላክ ኃይል ሙሉ በሙሉ በእነሱ ላይ እንዲሠራ ይፈቅዳሉ። (ኤፌሶን 3:16፤ ፊልጵስዩስ 4:13) ከዚህ አንጻር የአምላክ ኃይል የሚገለጠው በድካም ጊዜ ነው ሊባል ይችላል።

የ2 ቆሮንቶስ 12:9 አውድ

ጳውሎስ በ55 ዓ.ም. ገደማ በቆሮንቶስ ላሉ ክርስቲያኖች በመንፈስ መሪነት ደብዳቤ ጽፎላቸው ነበር። በደብዳቤው የመጨረሻ ክፍል ላይ ሐዋርያ የመሆን ሥልጣን እንዳለው አበክሮ ገልጿል። እንዲህ ለማድረግ የተነሳሳው ራሳቸውን የሾሙ አንዳንድ አስተማሪዎች፣ ምናልባትም በውጫዊ ገጽታው ወይም በንግግር ችሎታው የተነሳ ይተቹት ስለነበር ነው።—2 ቆሮንቶስ 10:7-10፤ 11:5, 6, 13፤ 12:11

ጳውሎስ የመከላከያ ሐሳብ ሲያቀርብ፣ በራሱ ጥንካሬ ቢሆን ኖሮ አገልግሎቱን ማከናወንና የተለያዩ ፈተናዎችን መወጣት እንደማይችል ገልጿል። (2 ቆሮንቶስ 6:4፤ 11:23-27፤ 12:12) ምዕራፍ 12 ላይ “ሥጋዬን የሚወጋ እሾህ” የሚል ምሳሌያዊ አገላለጽ ተጠቅሟል፤ ይህም አካላዊ ወይም ስሜታዊ ሥቃይ ያስከተለበትን ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ችግር የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም። (2 ቆሮንቶስ 12:7) ጳውሎስ ይህ ችግር ምን እንደሆነ ባይገልጽም በአምላክ እርዳታ ችግሩን በጽናት ለመቋቋም ቁርጥ ውሳኔ አድርጎ ነበር።

በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖችም ስደትና ሌሎች ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ። አምላክ የሚሰጣቸው ኃይል፣ የሚያጋጥማቸውን ማንኛውንም ችግር ለመወጣት እንደሚረዳቸው ማወቃቸው ያጽናናቸዋል። እነሱም ልክ እንደ ጳውሎስ በሙሉ ልብ “ስደክም ያን ጊዜ ብርቱ ነኝ” ማለት ይችላሉ።—2 ቆሮንቶስ 12:10

ሁለተኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 12⁠ን በአዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ አንብብ። ለመረዳት ቀላል በሆነ መንገድ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የግርጌ ማስታወሻዎች፣ ማጣቀሻዎች፣ ሥዕላዊ መግለጫዎችና ካርታዎች አሉት።

የ2 ቆሮንቶስ መጽሐፍን አጠቃላይ ይዘት ለማየት ይህን አጭር ቪዲዮ ተመልከት።

a ይሖዋ የአምላክ የግል ስም ነው። (መዝሙር 83:18) “ይሖዋ ማን ነው?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ