የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g94 1/8 ገጽ 24-26
  • ገንዘብ ታዛዡ አገልጋይህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ገንዘብ ታዛዡ አገልጋይህ
  • ንቁ!—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለሕይወት አስፈላጊ በሆኑት ነገሮች መርካት
  • የገንዘብ አያያዝ
  • ሌላው አስፈላጊ ነገር
  • ገንዘብ የክፋት ሁሉ ሥር ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ለገንዘብ ሚዛናዊ አመለካከት ይኑርህ
    ንቁ!—2015
  • ገንዘብ
    ንቁ!—2014
  • የገንዘብ አያያዝ
    ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1994
g94 1/8 ገጽ 24-26

ገንዘብ ታዛዡ አገልጋይህ

“ከ1968 እስከ 1986 ባለው ጊዜ በታላቋ ብሪታንያ የግንባታ ማኅበር ቁጠባ ሂሣብ ያላቸው ሰዎች ብዛት ከ15% ወደ 64% አድጓል” በማለት ግላስጎ ሄራልድ ሪፖርት አድርጓል። ጋዜጣው ሪፖርቱን በመቀጠል “በአንጻሩ ግን የቤተ ክርስቲያን አባላት የሆኑ ሰዎች ብዛት ቀንሷል” ብሏል።

ገንዘብ ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ የአምላክ ተጻራሪ ሆኖ ሲታይ ቆይቷል። ይህም የሆነው ኢየሱስ “ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፣ ወይም አንዱን ይጠላል፣ ሁለተኛውንም ይወዳል። . . . ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም” በማለቱ እንደሆነ አይጠረጠርም። —​ማቴዎስ 6:​24

ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ “ገንዘብ ራስ መጠበቂያ ነው” ይላል። (መክብብ 7:​12 አዓት) ወይም አንድ ዘመናዊ ሰው እንደተናገረው “ገንዘብ ሁሉም ሕዝቦች በሚገባቸው ቋንቋ ይናገራል።”

ይሁን እንጂ ገንዘብ በእኛ ላይ ከመሠልጠን ይልቅ እንዲጠቅመን ለማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ለሕይወት አስፈላጊ በሆኑት ነገሮች መርካት

ምግብ

ልብስ

መጠለያ

ከላይ የተዘረዘሩት በሕይወት ለመኖር የግድ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ናቸው። ደስተኛ ለመሆን የሚያስፈልጉ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው “ምግብና ልብስ ከኖረን ግን እርሱ ይበቃናል።” ከእነዚህ ነገሮች ሌላ የግድ የሚያስፈልገን ነገር የለም። “ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም።”—​1 ጢሞቴዎስ 6:​7, 8

የምታገኘው ገንዘብ የግድ አስፈላጊ ናቸው የምትላቸውን ነገሮች ለማስገኘት የማይበቃህ ቢሆንስ? የሚያስፈልጉህን ነገሮች ሊያስገኝልህ የሚችል ደመወዝ ልታገኝ ወደምትችልበት አካባቢ ለመሄድ ታስብ ይሆናል። ይሁን እንጂ ከመሄድህ በፊት ያለህበትን ሁኔታ በሐቀኝነትና በጥንቃቄ ማመዛዘን ይኖርብሃል። ምክንያቱም የአምላክ ቃል “ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ” በማለት ያስጠነቅቃል። —​1 ጢሞቴዎስ 6:​9

ይህንን ማስጠንቀቂያ ልብ በል! ሐዋርያው ጳውሎስ “አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለመውደድ ይሁን” በማለት የሰጠውን ምክር አዳምጥ። (ዕብራውያን 13:​5) ራስህን ‘ለመኖር በሚያስፈልጉኝ ነገሮች ብቻ እረካለሁ ወይስ የቅንጦት ዕቃዎችን ለማግኘት እጎመጃለሁ?’ ብለህ ጠይቅ።

እውነት ነው፣ ገንዘብ ደስታ የሚጨምሩ ነገሮችን ሊገዛ ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ “እንጀራን ለሳቅ የወይን ጠጅንም ለሕይወት ደስታ ያደርጉታል። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ ያለ ገንዘብ አይገኝም” ይላል። (የ1980 ትርጉም ) ሆኖም ገንዘብ የሚገዛቸው ትርፍ ነገሮች ለእውነተኛ ደስታ የግድ የሚያስፈልጉ ነገሮች አይደሉም። —​መክብብ 10:​19

የገንዘብ አያያዝ

ታዲያ ገንዘብ የአገልጋይነት ቦታውን ሳይለቅ እንዲኖር ምን ለማድረግ ትችላለህ? በአቅም መኖር በጣም አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ ያህል ቀደም ሲል የተጠቀሰችው ሊዝ እንዲህ ትላለች:- “ትንሽ ልጅ ሳለሁ ቤተሰቤ የነበረበት ችግር የገንዘብ አያያዝ ካለማወቅ የመጣ እንደሆነ አሁን ተገንዝቤአለሁ። በዱቤ እንገዛ ስለነበረ ዕዳ ከራሳችን ወርዶ አያውቅም። ይህ ደግሞ በቤተሰቡ ላይ ጭንቀት ያመጣ ነበር።”

ያለህን ገንዘብ በጥንቃቄ መቆጣጠር ይኖርብሃል። ደመወዝህን እንደተቀበልህ በመጀመሪያ አስፈላጊ ለሆኑ ወጪዎች የሚያስፈልገህን ለይ። እንዲህ ስታደርግ ገንዘብህ መክብብ 7:​12 እንደሚለው ራስህን መጠበቂያ ይሆንልሃል።

ወደፊት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሁኔታዎችን ለመመልከት መቻል አንዱ የገንዘብ አያያዝ አስፈላጊ ክፍል ነው። ወደፊት ሊያጋጥሙ ለሚችሉ ወጪዎች የሚሆን ገንዘብ አስቀምጥ። ይሁን እንጂ ከሚገባ በላይ ስለወደፊቱ ጊዜ መጨነቅና የገንዘብ ችግር እንዳያጋጥም መጣር ጉዳት ሊያስከትል የሚችል የፍቅረ ንዋይ ክፍል መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

በተጨማሪም ያለህ ገንዘብ በሙሉ የአንተ ሊሆን እንደማይችል ማስታወስ ይኖርብሃል። ኢየሱስ ግብር ስለመክፈል ተጠይቆ የሰጠውን መልስ ታስታውሳለህን? ሳንቲም እንዲሰጡት ጠየቀና “ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት?” አላቸው።

“የቄሣር ናት” ብለው መለሱለት።

ኢየሱስም መልሶ “የቄሣርን ለቄሣር አስረክቡ አላቸው።”

ስለዚህ ሕጋዊ ሥልጣን ያላቸው መንግሥታት ለሚሰጡት የጤና፣ የትምህርትና የመጓጓዣ አገልግሎት የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ በግብር መልክ እንድንከፍል መጠየቃቸው ተገቢ ነው። እንግዲያው የአምላክን ሞገስ ለማግኘት ከፈለግህ የምትጠየቀውን ግብር የመክፈል ግዴታ አለብህ። —​ማርቆስ 12:​13–17

ሌላው አስፈላጊ ነገር

ከምግብ፣ ከልብስና ከመጠለያ ሌላ የግድ የሚያስፈልገን ነገር አለ። ይህን አስፈላጊ ነገር ችላ ብንል በራሳችን ላይ ከባድ ችግር ማስከተላችን አይቀርም። ይህ አስፈላጊ ነገር ምን እንደሆነ ከሚከተሉት የኢየሱስ ቃላት መገንዘብ ትችላለህን? “የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ።” —​ሉቃስ 16:​9

ገንዘብ ያልቃል። ብዙዎቻችን የዕቃዎች ዋጋ እየናረ በመሄዱ ምክንያት የገንዘባችን የመግዛት ኃይል እየተሟጠጠ ሲሄድ ስለተመለከትን ገንዘብ ጠፊ መሆኑን ተገንዝበናል። ስለዚህ በሕይወት እስከኖርን ድረስ ገንዘባችንን ‘በዘላለም ቤቶች ሊቀበሉን ከሚችሉ ጋር’ ሊያወዳጀን በሚችል መንገድ ለመጠቀም እንፈልጋለን። እነዚህ ወደፊት የሚቀበሉን ወዳጆቻችን እነማን ናቸው?

ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነተኛ አምላክ የሆንህ አንተን፣ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት” ብሎ በጸለየ ጊዜ መልሱን ራሱ ሰጥቷል። (ዮሐንስ 17:⁠3) አዎን፣ ሕይወታችን በዚህ በመከራ የተሞላ አጭር ኑሮ ተወስኖ እንዳይቀር ከፈለግን ፈጣሪያችን ከሆነው ከይሖዋ አምላክና ከልጁ ከኢየሱስ ጋር መወዳጀት የግድ ያስፈልገናል።

ይሁን እንጂ እንዴት ከእነርሱ ጋር መወዳጀት እችላለሁ? ምንስ ወጪ ይጠይቅብኛል? ይህስ እውነተኛ ደስታ ያስገኝልኛልን? ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።

[በገጽ 26 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

“የቄሣርን ለቄሣር አስረክቡ” የሚለው የኢየሱስ ትምህርት ዛሬ በምንኖረው ሰዎች ላይ ኃላፊነት ያስከትላል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ