የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g93 4/8 ገጽ 29
  • ለእማማና ለአባባ የተጻፈ ደብዳቤ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለእማማና ለአባባ የተጻፈ ደብዳቤ
  • ንቁ!—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ወላጆቼን ይበልጥ ላውቃቸው የምችለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2009
  • ብርቅ የሆነ ክርስቲያናዊ ውርስ
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ልጆች ሐዘን ሲደርስባቸው
    ንቁ!—2017
  • ከአምላክና ከእናቴ ጋር ሰላም መፍጠር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1993
g93 4/8 ገጽ 29

ለእማማና ለአባባ የተጻፈ ደብዳቤ

ጥሩ ወላጆች ምን ያህል ጠቃሚ ናቸው? አንድ ትልቅ ልጅ ለእናትና ለአባቱ የጻፈው የሚከተለው ደብዳቤ የእነርሱን ዋጋማነት ያሳያል።

“የተወደዳችሁ እማዬና አባዬ:-

“ከቤት ከወጣሁ ከ16 ዓመታት በላይ ስለሆነኝ አሁን ከእኔ እንደዚህ ዓይነቱ ደብዳቤ ሲደርሳቸሁ እንግዳ ነገር ይሆንባችሁ ይሆናል። ነገር ግን ብዙ ካሰብኩበት በኋላ ይህንን ደብዳቤ መጻፉን አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ከብዙ ዓመታት በፊት ከቤታችሁ ስወጣ ከእናንተ ፈቃድ ሳልጠይቅ የወሰድኳቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ። ምናልባትም እነዚህን ነገሮች እንደወስድኳቸውም እንኳን አላወቃችሁ ይሆናል። ስወስዳቸው ምንም በማያስታውቅ መንገድ ስለነበር እስከተወሰነ ዓመት ድረስ ከእኔ ጋር እንዳሉ እንኳን አላውቅም ነበር። እነርሱንም እንደሚከተለው ዘርዝሬያቸዋለሁ:-

“ትክክል የሆነውን ነገር መውደድ:- ይህ እንዴት ዓይነት ጥበቃ ሆኖልኛል!

“ሰዎችን መውደድ:- ቁመና፣ ቅርጽና ቀለም የማይለውጠው። ውስጣዊ ማንነታቸውን ብቻ ግምት ውስጥ የሚያስገባ።

“ሐቀኝነት:- የኔ የሆነው ነገር የኔ ነው፤ ለሌሎች ባካፍላቸው ይመረጣል። የሌላውን ሰው ንብረት ግን ለእርሱ መተው።

“ቁርጠኝነት:- ከባድ ችግር በገጠመኝ ጊዜ ሁሉ ይህ እጄን ይዞ አውጥቶኛል።

“ትዕግሥት:- እናንተ ለእኔ ደግ፣ አፍቃሪና በትዕግሥት የምትንከባከቡኝ ነበራችሁ። እኔን ለመርዳት ተስፋ ቆርጣችሁ አታውቁም።

“ተግሣጽ:- በጣምም አልተጫናችሁኝም፤ ልቅም አልሰደዳችሁኝም። ይህንን ግን በጊዜው አልተረዳሁትም ነበር። ይቅርታ ታደርጉልኝ ይሆን?

“ነፃነት:- ሌሎች ብዙ ልጆች ካደጉበት ስቃይ ይኸውም በአካል፣ በአእምሮና በስሜት ልጆቻቸውን የሚያጎሳቁሉ ወላጆች ከሚያደርሱባቸው ሥቃይ ነፃ ነበርሁ። ለእኔ የተሻለውን ነገር ከማሰብ በቀር ሌላ ምንም ነገር በአእምሯችሁ አልነበረም፤ ከጉዳት ጠብቃችሁኛል። ለእኔ ያደረጋችሁልኝን ፈጽሞ አልረሳውም።

“ቀላል የሆኑ ነገሮችን መውደድ:- ተራራዎች፣ ወንዞች፣ ጥርት ያለው ሰማይ፣ የእግር ጉዞው፣ ራቅ ያሉ ቦታዎች ሄደን በድንኳን ውስጥ የምናድርባቸው ጊዜያት። ሕይወትን አስደሳች አድርጋችሁልኛል። ሁለት ወላጆች ከዚህ የተሻለ ነገር ሊያደርጉ አይችሉም። ይህንንም አድርጋችሁ ቅር አትሰኙም ነበር።

“ጥንቃቄ:- የሰማኸውን ሁሉ ለማመን አትቸኩል። ስታምንበት ግን ምንም ይሁን ምን አጥብቀህ ያዘው።

“ከአምላክ ቃል የተገኘው እውነት:- ይህ ከሁሉም የሚበልጥ ነው። የእኔ ውርሻ ይህ ነው። ምንም ያህል ገንዘብ፣ ጀልባዎች ቢሆኑ፣ ቤቶች ወይም ሌላ ንብረት ከዚህ ጋር አይወዳደርም። ከሁሉ የተሻለውን ነገር ይኸውም የዘላለምን ሕይወት ያስገኝልኛል።

“ከላይ የተዘረዘሩትን ነገሮች ዋጋቸው ይህን ያክል ነው ለማለት ያስቸግራል። በዋጋ ሊተመኑ የማይችሉ ናቸው። በጣም ተጠቅሜባቸዋለሁ። ለእናንተ መልሼ መስጠት ከሌለብኝ በእነርሱ መጠቀሜን እቀጥላለሁ። ቅር የማይላችሁ ከሆነም ለትናንሽ ልጆቼ መስጠቴን ለመቀጠል አስቤያለሁ። ለእኔ እንዳገለገሉ ሁሉ ለልጆቼም እንደሚያገለግሉ ተስፋ አደርጋለሁ። ከየት እንዳገኘኋቸው ይኸውም ከአያቶቻቸው እንደተቀበልኳቸው እንዲያውቁ ሁልጊዜ እነግራቸዋለሁ።

“ልጃችሁ”

(ጥያቄውን በማክበር ስሙን አንጠቅስም)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ