የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g96 7/8 ገጽ 26
  • ጠንቃቃ ሾፌር ነህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጠንቃቃ ሾፌር ነህን?
  • ንቁ!—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መኪና ስታሽከረክር ራስህን ከአደጋ ትጠብቃለህ?
    ንቁ!—2002
  • በጎዳና ላይ የሚያጋጥም ግልፍተኝነትን እንዴት መቋቋም ይቻላል?
    ንቁ!—1998
  • ድካም የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ስውር ወጥመድ
    ንቁ!—1998
  • የመኪና አደጋ እንዳይደርስ መከላከል የሚቻለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2011
ንቁ!—1996
g96 7/8 ገጽ 26

ጠንቃቃ ሾፌር ነህን?

መኪና በምታሽከረክርበት ጊዜ የምታሳየው ጠባይ በማሽከርከር ችሎታህ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። በእንግሊዝ አውቶሞቢል ማኅበር የተደረገ አንድ ጥናት እንዳሳየው ከ17 እስከ 20 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የእንግሊዝ ወንዶች መካከል 22 በመቶው በየዓመቱ ቢያንስ አንድ የመኪና አደጋ ያጋጥማቸዋል።

በአደገኛ ሁኔታ እንዲያሽከረክሩ የሚያደርጓቸው ዋነኛ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? የአውቶሞቢል ማኅበሩ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ኬንዝ ፋርክሎዝ እንደለገጹት ከመጠጥ፣ ከከፍተኛ የስሜት መለዋወጥና በጣም ከሚጮህ ሙዚቃ በተጨማሪ “ብዙዎቹ በአደገኛ ሁኔታ የሚያሽከረክሩት በእኩዮቻቸው ግፊት ነው።” በዚህ የተነሳ የአውቶሞቢል ማኅበሩ ለተማሪዎች የሚሰጠው ሥልጠና በአሽከርካሪነት ጥበብ ላይ ሳይሆን በአሽከርካሪው ጠባይ ላይ ማተኮር እንዳለበት ሐሳብ ያቀርባል።

ለምሳሌ ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ:- ‘የመጣው ይምጣ ብዬ ግድ የለሽ በመሆን መኪናዬ ውስጥ የተሳፈሩት ሰዎች በችሎታዬ እንዲገረሙ ለማድረግ እጥራለሁን? በማሽከረክርበት ጊዜ በሚኖረኝ ሁኔታ ላይ ስሜቴ ተጽዕኖ ያሳድራልን? በመንገድ ላይ የሚያጋጥሙኝን ሌሎች አሽከርካሪዎች እንደ ተራ መሰናክል አድርጌ በማየት ቀድሜያቸው መሄድ እንዳለብኝ ሆኖ ይሰማኛልን?’ ለእነዚህ ጥያቄዎች የምትሰጣቸው መልሶች ምን ዓይነት አሽከርካሪ እንደሆንክ ያሳያሉ።

ወንዶችም ሆናችሁ ሴቶች፣ ወጣቶችም ሆናችሁ በዕድሜ የገፋችሁ መኪና ስታሽከረክሩ ወዳጃዊ ዝንባሌ ይኑራችሁ። “ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው።” (ማቴዎስ 7:12) እንዲህ ማድረጉ በምታሽከረክሩበት ጊዜ ከአደጋ ይጠብቃችኋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ