የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 12/12 ገጽ 15-31
  • ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤተሰብ የሚወያይበት
  • ንቁ!—2012
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከአብርሃም ምን እንማራለን?
  • ካርድ በመሰብሰብ መማር
  • ሕዝቦችና አገሮች
  • ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
  • መልስ
  • ሳምሶን ከይሖዋ ባገኘው ብርታት ድል አደረገ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • እንደ ሳምሶን በይሖዋ ታመኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 12/12 ገጽ 15-31

ቤተሰብ የሚወያይበት

ከአብርሃም ምን እንማራለን?

ለሌሎች ደግነት ማሳየት አስፈላጊ ይመስልሃል?

• ሥዕሎቹን ተስማሚ ቀለም ቀባ። • ጥቅሶቹን አንብብና አብራራ፤ ከዚያም የተናገሩትን ነገር በክፍት ቦታው ላይ ጻፍ። • እስቲ የሚከተሉትን ነገሮች ከሥዕሎቹ ውስጥ ፈልገህ ለማግኘት ሞክር። (1) እንሽላሊት እና (2) ቢላዋ

አብርሃም ሰዎቹን በእንግድነት ሲቀበል ምን ደግነት የሚንጸባረቅባቸው ነገሮች አድርጓል?

ፍንጭ፦ ዘፍጥረት 18:2, 4, 5።

ለሌሎች ደግነት ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ ሮም 12:13።

በዘፍጥረት ላይ ከሚገኘው ከዚህ ዘገባ ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለህ?

ምን ይመስልሃል?

ከሁሉ የበለጠ ደግነት ማሳየት ያለብን ለማን ነው?

ፍንጭ፦ ገላትያ 6:10

ካርድ በመሰብሰብ መማር

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 24 ሳምሶን

ጥያቄ

  1. ሀ. የሳምሶን አባት ስም ․․․․․ ነው።

  2. ለ. ሳምሶን በጋዛ ከተማ ውስጥ ምን ከፍተኛ ጥንካሬ የሚጠይቅ ድርጊት ፈጽሟል?

  3. ሐ. ሳምሶንን አሳልፋ የሰጠችው ማን ናት?

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

ለ20 ዓመታት የእስራኤልን ብሔር ከጥቃት የጠበቀ ጀግና መስፍን ነው። (መሳፍንት 15:20) ይሖዋ በሳምሶን ተጠቅሞ እስራኤላውያንን “ከፍልስጥኤማውያን እጅ [ታድጓል]።” (መሳፍንት 13:5) የአምላክ መንፈስ ሳምሶን ከፍተኛ ኃይል እንዲኖረው አድርጓል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ሳምሶን በይሖዋ ላይ ጠንካራ እምነት ነበረው።—ዕብራውያን 11:32-34

መልስ

  1. ሀ. ማኑሄ።—መሳፍንት 13:8, 24

  2. ለ. የከተማይቱን ቅጥር በር ከሁለት መቃኖቹ ጋር መወርወሪያውንና ማያያዣውን ጭምር ተሸክሞ በኬብሮን ፊት ለፊት እስካለው ኮረብታ ጫፍ ድረስ ወጥቷል።—መሳፍንት 16:2, 3

  3. ሐ. ደሊላ።—መሳፍንት 16:4, 5

ሕዝቦችና አገሮች

ሌዝሊ፣ ካትሊን እና አሎንድራ እንባላለን፤ የ10፣ የ8 እና የ7 ዓመት ልጆች ስንሆን የምንኖረው በሜክሲኮ ነው። በሜክሲኮ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 295,400፣ 455,000 ወይስ 724,700?

የምንኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከሜክሲኮ በጣም ይርቃል?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

መልስ

  1. እንሽላሊቷ የምትገኘው በሥዕል 5 ላይ ነው።

  2. ቢላዋው የሚገኘው በሥዕል 2 ላይ ነው።

  3. 724,700

  4. ሀ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ