የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • sp ገጽ 30-31
  • ገነቲቷ ምድር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ገነቲቷ ምድር
  • የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የተሻለ ሕይወት እንደሚመጣ ተስፋ ተሰጥቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • የአምላክ ወዳጆች በገነት ውስጥ ይኖራሉ
    የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • እውነተኛው ሃይማኖት ለዘላለም ይጠቅምሃል!
    ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን መንገድ አግኝተኸዋል?
  • ከአርማጌዶን በኋላ ምድር ገነት ትሆናለች
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?
sp ገጽ 30-31

ገነቲቷ ምድር

የተለያየ ዘር ያላቸው ሰዎች በገነት ውስጥ አብረው ሲመገቡ

ይሖዋ ሰይጣን ያደረሰውን ጉዳት በሙሉ ያስወግዳል። ይሖዋ መላዋን ምድር እንዲያስተዳድር ኢየሱስን ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል። በእሱ አገዛዝ ሥር ምድር ወደ ገነትነት ትለወጣለች።—ዳንኤል 7:13, 14፤ ሉቃስ 23:43

ይሖዋ የሚከተሉትን ነገሮች እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል፦

  • የተትረፈረፈ ምግብ፦ “ምድር ፍሬዋን ትሰጣለች፤ አምላክ፣ አዎ፣ አምላካችን ይባርከናል።” “በምድር ላይ እህል ይትረፈረፋል፤ በተራሮችም አናት ላይ በብዛት ይኖራል።”—መዝሙር 67:6፤ 72:16

  • ጦርነት አይኖርም፦ “ኑና የይሖዋን ሥራዎች እዩ፤ በምድርም ላይ አስደናቂ ነገሮችን እንዴት እንዳከናወነ ተመልከቱ። ጦርነትን ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል።”—መዝሙር 46:8, 9

  • ክፉ ሰዎች አይኖሩም፦ “ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፤ . . . ለጥቂት ጊዜ ነው እንጂ ክፉዎች አይኖሩም፤ በቀድሞ ቦታቸው ትፈልጋቸዋለህ፤ እነሱ ግን በዚያ አይገኙም።”—መዝሙር 37:9, 10

  • ሕይወት በገነት ውስጥ

    በሽታ፣ ሐዘን፣ ወይም ሞት አይኖርም፦ “በዚያን ጊዜ የዓይነ ስውራን ዓይን ይገለጣል፤ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ጆሮም ይከፈታል። በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል፤ የዱዳም ምላስ በደስታ እልል ይላል።”—ኢሳይያስ 35:5, 6

    “አምላክ ራሱም ከእነሱ ጋር ይሆናል። እሱም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም። ቀድሞ የነበሩት ነገሮች አልፈዋል።”—ራእይ 21:3, 4

ይሖዋ እንደ ሰይጣንና እንደ አጋንንቱ አይዋሽም። ቃል የገባው ተስፋ በሙሉ ሳይፈጸም አይቀርም። (ሉቃስ 1:36, 37) ይሖዋ ይወድሃል፣ በሚያዘጋጃት ገነት ውስጥ እንድትኖርም ይፈልጋል። በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኙትን አስደናቂ እውነቶች በይበልጥ ለማወቅ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ተገናኝ። እውነትን በሕይወትህ በሥራ ላይ ካዋልክ ለሐሰት፣ ለአጉል እምነትና ለድንቁርና ባሪያ ከመሆን ነፃ ትወጣለህ። ኢየሱስ እንዳለው “እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነፃ ያወጣችኋል።”—ዮሐንስ 8:32

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ