የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • be ጥናት 51 ገጽ 263-ገጽ 264 አን. 4
  • ሰዓት መጠበቅና ጊዜን ማመጣጠን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሰዓት መጠበቅና ጊዜን ማመጣጠን
  • በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትክክለኛ መደምደሚያና የጊዜ አመዳደብ
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ለጉባኤ የሚቀርቡ ንግግሮችን መዘጋጀት
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • አስተዋጽኦ ማዘጋጀት
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
ለተጨማሪ መረጃ
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
be ጥናት 51 ገጽ 263-ገጽ 264 አን. 4

ጥናት 51

ሰዓት መጠበቅና ጊዜን ማመጣጠን

ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

ንግግርህን በተመደበልህ ሰዓት አጠናቅቅ፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ የንግግርህ ክፍል የምታጠፋው ጊዜ የተመጣጠነ ይሁን።

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ለእያንዳንዱ የትምህርቱ ዋና ነጥብ በቂ ጊዜ መመደብ ያስፈልጋል። ስብሰባው በሰዓቱ መጠናቀቅ ይኖርበታል።

አጽንዖት ሊሰጠው የሚገባው ነገር ትምህርቱን በጥሩ ሁኔታ የማቅረቡ ጉዳይ ቢሆንም የተመደበልህን ሰዓት መጠበቅህም ትኩረት የሚያሻው ነገር ነው። ስብሰባዎቻችን የሚጀምሩበትም ሆነ የሚያበቁበት የተወሰነ ሰዓት አላቸው። ስብሰባዎቹ በሰዓታቸው ሊጠናቀቁ የሚችሉት ክፍል ያላቸው ሁሉ በዚህ ረገድ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ነው።

ዛሬ በብዙ አገሮች የሚገኙ ሰዎች ስለ ሕይወት ያላቸው አመለካከት በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ከነበራቸው አመለካከት በእጅጉ የተለየ ነው። በዚያ ዘመን ሰዎች ጊዜን የሚገልጹት ‘ሦስት ሰዓት ገደማ’ ወይም “ዐሥር ሰዓት ገደማ” በማለት ነበር። (ማቴ. 20:​3-6 የ1980 ትርጉም ፤ ዮሐ. 1:​39 የ1980 ትርጉም ) በዕለት ተዕለት የሕይወት እንቅስቃሴያቸው ስለ ጊዜ ብዙም አይጨነቁም። ዛሬም ቢሆን በአንዳንድ አገሮች ሰዎች ስለ ጊዜ ያላቸው አመለካከት ከዚህ ጋር የሚመሳሰል ነው።

ይሁን እንጂ ሰዎች ከአካባቢያቸው ባሕል ወይም ከግል ባሕርያቸው የተነሣ ስለ ጊዜ ግዴለሽ ቢሆኑም እኛ ትክክለኛውን አመለካከት ማዳበራችን ይጠቅመናል። የተለያዩ ወንድሞች ተከታታይ ክፍሎች እንዲያቀርቡ በሚመደቡበት ጊዜ ለየክፍሉ የተመደበውን ጊዜ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። “ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን” የሚለው መሠረታዊ ሥርዓት በስብሰባዎች ላይ የሚቀርቡትን ክፍሎች ሰዓት በመጠበቅ ረገድም ይሠራል።​—⁠1 ቆሮ. 14:​40

በሰዓቱ መጨረስ። በሰዓቱ ለመጨረስ ዝግጅት ወሳኝ ነው። ብዙውን ጊዜ ሰዓታቸውን ለማክበር የሚቸገሩት ጥሩ ዝግጅት ያላደረጉ ተናጋሪዎች ናቸው። ከልክ በላይ በራሳቸው ይተማመኑ ይሆናል። ወይም ደግሞ ክፍላቸውን የሚዘጋጁት ባለቀ ሰዓት ሊሆን ይችላል። ለተሰጠህ ክፍል አድናቆት ካለህና ጥሩ ዝግጅት ለማድረግ ጥረት የምታደርግ ከሆነ ሰዓትህን መጠበቅ አትቸገርም።

ክፍልህ በንባብ የሚቀርብ ነውን? በመጀመሪያ ስለ ቅልጥፍና፣ ቆም እያሉ ስለመናገር፣ ስለ ማጥበቅና ዋና ዋና ነጥቦችን በአጽንዖት ስለማንበብ የሚናገሩትን ከጥናት 4 እስከ 7 ያሉትን ምዕራፎች ከልስ። ከዚያም ድምፅህን ከፍ አድርገህ በምታነብበት ጊዜ ምክሮቹን ሥራ ላይ ለማዋል ሞክር። ሰዓት ይዘህ ተለማመድ። በተመደበልህ ጊዜ ውስጥ ለመጨረስ ፈጠን ማለት ያስፈልግህ ይሆን? በንግግርህ ውስጥ ብዙም ጉልህ ስፍራ የሌላቸው ነጥቦች ላይ ስትደርስ ፈጠን ብለህ አንብብ። ሆኖም ቁልፍ የሆኑ ነጥቦችን ማጉላት በምትፈልግባቸው ቦታዎች ላይ ቆም ማለትና ዝግ ብለህ ማንበብ ይኖርብሃል። ደግመህ ደጋግመህ ተለማመድ። ቅልጥፍናህ እየተሻሻለ ሲሄድ በተመደበልህ ጊዜ ውስጥ ለመጨረስ አትቸገርም።

ንግግርህን የምታቀርበው ከማስታወሻ ከሆነስ? ሰዓት ለመጠበቅ ስትል በንባብ እንደሚቀርብ ንግግር እያንዳንዱን የክፍልህን ነጥብ በዝርዝር መጻፍ አያስፈልግህም። በጥናት 25 ላይ የተሻለው ዘዴ ምን እንደሆነ ተምረሃል። የሚከተሉትን አምስት ነጥቦች አትርሳ:- (1) ጥሩ ነጥቦችን መዘጋጀትህ አስፈላጊ ቢሆንም መብዛት የለባቸውም። (2) ዋና ዋና ነጥቦቹን በአእምሮህ መቅረጽ ቢኖርብህም እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር ለመሸምደድ አትሞክር። (3) ለእያንዳንዱ የንግግርህ ክፍል ምን ያህል ጊዜ እንደምታጠፋ ወይም በምን ያህል ጊዜ ውስጥ የትኛው ነጥብ ላይ መድረስ እንደሚኖርብህ አስተዋጽኦህ ላይ ምልክት አድርግ። (4) ንግግሩን በምታቀርብበት ወቅት ጊዜ እንደማይበቃህ ከተሰማህ ልታስቀራቸው የምትችላቸውን ነጥቦች አስቀድመህ በመምረጥ ምልክት አድርግባቸው። (5) የንግግርህን አቀራረብ ተለማመድ።

ንግግርህን መለማመድ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህን ስታደርግ ለእያንዳንዱ የንግግሩ ክፍል የተመደበውን ጊዜ መጠበቅ አለመጠበቅህን ተከታተል። ንግግርህን በተመደበልህ ሰዓት መጨረስ እስክትችል ድረስ ደግመህ ደጋግመህ ተለማመድ። ሰዓትህን አጣብበህ ብዙ ነጥብ ለመጨመር አትሞክር። ብቻህን ስትለማመድ ከምትወስደው ጊዜ ይልቅ ንግግሩን ለአድማጮች ስታቀርብ የበለጠ ጊዜ ልትፈጅ ስለምትችል የተወሰነ የጊዜ ክፍተት ልትተው ይገባል።

ጊዜን ማመጣጠን። ንግግሩን በሰዓቱ መጨረስና ለእያንዳንዱ የንግግሩ ክፍል ጊዜን ማመጣጠን ተነጣጥለው የማይታዩ ነገሮች ናቸው። የትምህርቱ አንኳር ነጥቦች የሚገኙት በንግግሩ አካል ውስጥ ስለሆነ ከተመደበልህ ጊዜ አብዛኛውን ልትጠቀምበት የሚገባው ለዚህ የንግግሩ ክፍል ነው። የመግቢያው ርዝማኔ በጥናት 38 ውስጥ የተገለጹትን ሦስት ዓላማዎች ማሳካት ካስቻለ በቂ ነው። በጥናት 39 ላይ በተገለጸው መሠረት ግቡን የሚመታ መደምደሚያ ተጠቅመን ንግግሩን ለመቋጨት በቂ ጊዜ እንድናገኝ የንግግሩ አካል አለቅጥ መርዘም የለበትም።

ክፍልህን በሰዓቱ ለመጨረስ የምታደርገው ጥረት ንግግርህ የተሳካ እንዲሆን ከማድረጉም በላይ ክፍል ላላቸው ሌሎች ወንድሞችም ሆነ ለጠቅላላው ጉባኤ ያለህን አክብሮት የሚያሳይ ይሆናል።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ቀደም ብለህ በመጀመር ጥሩ ዝግጅት አድርግ።

  • ለእያንዳንዱ የንግግርህ ክፍል ጊዜህን አመጣጥነህ በመመደብ በዚያ መሠረት ለማቅረብ ጥረት አድርግ።

  • የንግግርህን አቀራረብ ተለማመድ።

መልመጃ:- አንተም ሆንክ ቤተሰቦችህ ወደ ጉባኤ ለመሄድ የምታደርጉትን ዝግጅት ለመጨረስ የሚያስፈልጋችሁን ጊዜ በመመደብ ስብሰባዎቹ ከመጀመራቸው ከ15 ወይም ከ20 ደቂቃ በፊት ለመድረስ ዕቅድ አውጣ። እዚያ ለመድረስ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድባችሁ እንዲሁም ሊያዘገዩአችሁ የሚችሉትን የተለመዱ ችግሮች እንዴት መወጣት እንደምትችሉ አስብ። እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ እያደረግህ ይህን ግብህን በተደጋጋሚ ጊዜ ለማሳካት ሞክር። ንግግር በምትሰጥበትም ጊዜ እነዚህ መሠረታዊ ሥርዓቶች ይጠቅሙሃል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ