ክፍል 5
ገንዘብ
ደስተኛ እንድትሆን ገንዘብ ምን ያህል አስፈላጊ ነው ትላለህ?
□ አስፈላጊ አይደለም
□ በተወሰነ መጠን ያስፈልጋል
□ የግድ አስፈላጊ ነው
ስለ ገንዘብ ወይም ገንዘብ ሊገዛቸው ስለሚችላቸው ነገሮች ምን ያህል ታወራለህ?
□ ከስንት አንዴ
□ አልፎ አልፎ
□ ብዙ ጊዜ
ገንዘብ ከመሬት እንደማይታፈስ ወላጆችህ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲናገሩ ሰምተህ ይሆናል። ደግሞም እውነታቸውን ነው። ገንዘብን በአግባቡ መያዝ የሚኖርብህም ለዚህ ነው። ገንዘብ ጠቃሚ ነገሮችን የሚያከናውን ቢሆንም ውጥረት ሊፈጥርብህ እንዲሁም ከሰዎችም ሆነ ከአምላክ ጋር ያለህ ግንኙነት እንዲበላሽ ሊያደርግ ይችላል። ለገንዘብ ያለህ አመለካከት ይህ ነው የማይባል ተጽዕኖ ሊያሳድርብህ እንደሚችል አይካድም። ከ18 እስከ 20 ያሉት ምዕራፎች ለገንዘብ ሚዛናዊ አመለካከት ማዳበር የምትችለው እንዴት እንደሆነ ይጠቁማሉ።
[በገጽ 148 እና 149 ላይ የሚገኝ ባለሙሉ ገጽ ሥዕል]