መዝሙር 39
ከአምላክ ያገኘነው ሰላም
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋን አወድሱ፤ ሰላም ይወዳል።
ጦርነትን ያስቀራል፤ ፍቅርን ያሰፍናል።
የሰላም አለቃ ነው፤ ልጁ ’የሱስም
ፍትሕ በማስፈን ባለም፣ ያመጣል ሰላም።
2. ጠበኝነትንና ቁጣን ትተናል።
የጦር መሣሪያችንም የሰላም ሆኗል።
ይህ ሰላም እንዳይጠፋ ይቅር ባይ ’ንሁን።
የክርስቶስ በጎች ነን፤ ሰላም ይኑረን።
3. የጽድቅ ፍሬ ነው ሰላም፤ እንኮትኩተው።
ከላይ የሆነው ጥበብ መገለጫም ነው።
መንግሥቱ እስኪያመጣ ሰላም ለምድር፣
ሰላማዊ ለመሆን ከልብ እንጣር።
(በተጨማሪም መዝ. 46:9ን፣ ኢሳ. 2:4ን እና ያዕ. 3:17, 18ን ተመልከት።)