መዝሙር 104
ያህን አብረን እናወድስ!
በወረቀት የሚታተመው
1. ያህን አብረን እናወድስ!
ሰጥቶናል ሕይወትና እስትንፋስ።
ስሙን እንባርክ፣ ሌትና ቀን።
ኃያል ቢሆንም ተላብሷል ፍቅርን፤
እንዘምር፣ እናሳውቅ ስሙን።
2. ያህን አብረን እናወድስ!
ጸሎት ሰምቶ ይሰጣልና መልስ።
ክንዱ ብርታት ለደካማው፣
መንፈሱ ለትሑታን ድጋፍ ነው።
ስለ ኃይሉ እናውጅ በሰፊው።
3. ያህን አብረን ’ናወድሰው!
ያጽናናናል፣ የፍትሕ አምላክ ነው።
ልባችንን ይጠግናል፤
በረከቱን ለሁሉም ያፈሳል።
ኑ በደስታ እንበልለት እልል።
(በተጨማሪም መዝ. 94:18, 19፤ 145:21፤ 147:1፤ 150:2ን ተመልከት።)