መዝሙር 95
“ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም”
በወረቀት የሚታተመው
1. ያገልግሎት መብት ልዩ ነው፤
የስብከት ሥራችን ክቡር።
ጊዜ እንግዛ ምርጡንም እንስጥ፤
ለብዙዎች ለመመሥከር።
(አዝማች)
ቃሉ ጋብዞናል ቀምሰን ’ንድናይ፣
የይሖዋን ጥሩነት።
ለአምላክ ማደር ትርፍ ያስገኛል፤
እናድርግ ትልቅ ጥረት።
2. የሙሉ ጊዜ አገልጋይ
ብዙ በረከት ያገኛል።
ባምላክ ላይ እምነት ስለሚኖረው፣
አይሰጋም፤ ባለው ይረካል።
(አዝማች)
ቃሉ ጋብዞናል ቀምሰን ’ንድናይ፣
የይሖዋን ጥሩነት።
ለአምላክ ማደር ትርፍ ያስገኛል፤
እናድርግ ትልቅ ጥረት።
(በተጨማሪም ማር. 14:8ን፣ ሉቃስ 21:2ን፣ 1 ጢሞ. 1:12፤ 6:6ን ተመልከት።)