መዝሙር 133
ትድኑ ዘንድ አምላክን ፈልጉ
በወረቀት የሚታተመው
1. ብሔራት አበሩ፤
ባምላክ ልጅ ላይ ተነሱ።
የሰው አገዛዝ ያከትማል፤
ይሖዋ ፍርዱን ሰጥቷል።
ገዢዎች በቃቸው፤
ያምላክ መንግሥት ተራ ነው።
’የሱስ ጠላቶቹን ያደቃል፤
ጊዜውም በጣም ቀርቧል።
(አዝማች)
እንድታገኙ መዳንን
በ’ምነት ፈልጉት አምላክን።
ጽድቁን ፈልጉ፤
ታማኞች ሁኑ፤
ልዕልናውን ደግፉ።
ያኔ ክንዱን ታያላችሁ፤
ሲታደጋችሁ።
2. ምሥራቹ ለሰው
እየተሰበከ ነው፤
እኛ ግብዣ ’ናቀርባለን፤
ምርጫው ግን የነሱ ነው።
ፈተናው ቢከብድም
ልንፈራ አይገባም።
ይሖዋ ሕዝቡን ይጠብቃል፤
ስንጮህ ይሰማናል።
(አዝማች)
እንድታገኙ መዳንን
በ’ምነት ፈልጉት አምላክን።
ጽድቁን ፈልጉ፤
ታማኞች ሁኑ፤
ልዕልናውን ደግፉ።
ያኔ ክንዱን ታያላችሁ፤
ሲታደጋችሁ።
(በተጨማሪም 1 ሳሙ. 2:9ን፣ መዝ. 2:2, 3, 9ን፣ ምሳሌ 2:8ን እና ማቴ. 6:33ን ተመልከት።)