መዝሙር 69
መንገድህን አሳውቀኝ
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ በፊትህ ተሰብስበናል፤
ግብዣህንም ተቀብለናል።
ቃልህ ብርሃን ነው፤ መንገድ ያሳየናል።
ያንተን ትም’ርት ይገልጽልናል።
(አዝማች)
አስተምረኝ መንገድህን ላስተውል፤
ጆሮዬ ወደ ሕግህ ያዘንብል።
በ’ውነተኛው ጎዳና ላይ ምራኝ፤
ት’ዛዞችህ ደስታ ያስገኙልኝ።
2. አምላካችን ሆይ፣ ጥበብህ ጥልቅ ነው፤
ሥርዓትህ የሚያረጋጋ ነው።
በድንቅ ነገሮች ተሞልቷል ያንተ ቃል፤
ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
(አዝማች)
አስተምረኝ መንገድህን ላስተውል፤
ጆሮዬ ወደ ሕግህ ያዘንብል።
በ’ውነተኛው ጎዳና ላይ ምራኝ፤
ት’ዛዞችህ ደስታ ያስገኙልኝ።