የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ll ክፍል 5 ገጽ 12-13
  • ታላቁ የጥፋት ውኃ—አምላክን የሰሙት እነማን ነበሩ? ያልሰሙትስ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታላቁ የጥፋት ውኃ—አምላክን የሰሙት እነማን ነበሩ? ያልሰሙትስ?
  • አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የኖኅ መርከብ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ክፍል 5
    አምላክን ስማ
  • ኖኅ መርከብ ሠራ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • “ከእውነተኛው አምላክ ጋር ይሄድ ነበር”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
ለተጨማሪ መረጃ
አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
ll ክፍል 5 ገጽ 12-13

ክፍል 5

ታላቁ የጥፋት ውኃ—አምላክን የሰሙት እነማን ነበሩ? ያልሰሙትስ?

በኖኅ ዘመን ይኖሩ የነበሩት አብዛኞቹ ሰዎች ክፉ ድርጊት ይፈጽሙ ነበር። ዘፍጥረት 6:5

ሥጋ የለበሱ ክፉ መላእክት ከሴቶች ጋር ሆነው

አዳምና ሔዋን ልጆች ወለዱ፣ ሰዎችም በምድር ላይ እየበዙ ሄዱ። ከጊዜ በኋላ የተወሰኑ መላእክት ዓምፀው ከሰይጣን ጎን ተሰለፉ።

እነዚህ መላእክት የሰው አካል ለብሰው ወደ ምድር በመምጣት የሰውን ሴቶች ልጆች አገቡ። ሴቶቹም ከሰው የላቀ ኃይል ያላቸውን ጨካኝና ብርቱ የሆኑ ልጆች ወለዱ።

ልጅ የያዘችን ሴት አንድ ልጅ ሲመታት፤ የክፉዎቹ መላእክት ልጆች የሆኑት ኔፍሊም የዓመፅ ድርጊት ሲፈጽሙ

ዓለም ክፉ ድርጊት በሚፈጽሙ ሰዎች ተሞላች። መጽሐፍ ቅዱስ “የሰው ልጅ ክፋት በምድር ላይ እንደበዛና የልቡም ሐሳብ ሁሉ ምንጊዜም ወደ መጥፎ ብቻ ያዘነበለ” እንደነበር ይገልጻል።

ኖኅ አምላክ ያዘዘውን በመስማት መርከብ ሠርቷል። ዘፍጥረት 6:13, 14, 18, 19, 22

ኖኅ አምላክን ሰምቷል

ኖኅ ጥሩ ሰው ነበር። ይሖዋ ታላቅ የጥፋት ውኃ በማምጣት ክፉ ሰዎችን ሊያጠፋ እንደሆነ ለኖኅ ነገረው።

ኖኅና ቤተሰቡ መርከቡን ሲሠሩ

በተጨማሪም አምላክ ትልቅ መርከብ እንዲሠራ እንዲሁም ቤተሰቡንና ሁሉንም ዓይነት እንስሳት ወደ መርከቡ እንዲያስገባ ነገረው።

ኖኅ የጥፋት ውኃ እንደሚመጣ ሕዝቡን ሲያስጠነቅቅ፤ ሕዝቡ ግን እየሳቁበት ነው

ኖኅ የጥፋት ውኃ ሊመጣ እንደሆነ በመናገር ሰዎችን ቢያስጠነቅቅም እነሱ ግን አልሰሙትም። እንዲያውም አንዳንዶቹ ሳቁበት፤ ሌሎቹ ደግሞ ጠሉት።

ኖኅና ቤተሰቡ እንስሳቱን ወደ መርከቡ ለማስገባት ሲሰበስቡ

ኖኅ መርከቡን ሠርቶ ሲያጠናቅቅ እንስሳቱን ወደ ውስጥ አስገባቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ