የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 73 ገጽ 172-ገጽ 173 አን. 2
  • ዮሐንስ ለመሲሑ መንገድ አዘጋጀ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዮሐንስ ለመሲሑ መንገድ አዘጋጀ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመሲሑ መንገድ ጠራጊ ነበር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • መጥምቁ ዮሐንስ መንገዱን አዘጋጀ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ኢየሱስ መሲሕ ሆነ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ዮሐንስ መንገዱን አዘጋጀ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 73 ገጽ 172-ገጽ 173 አን. 2
መጥምቁ ዮሐንስ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ላይ ሕዝቡን ሲያስተምር

ትምህርት 73

ዮሐንስ ለመሲሑ መንገድ አዘጋጀ

የዘካርያስና የኤልሳቤጥ ልጅ የሆነው ዮሐንስ ካደገ በኋላ ነቢይ ሆነ። ይሖዋ መሲሑ እንደሚመጣ ለሰዎች እንዲናገር ዮሐንስን ላከው። ዮሐንስ ያስተማረው በምኩራቦች ወይም በከተሞች ውስጥ ሳይሆን በምድረ በዳ ነበር። ብዙ ሰዎች ዮሐንስ የሚያስተምረውን ትምህርት ለማዳመጥ ከኢየሩሳሌምና ከመላው ይሁዳ ይመጡ ነበር። አምላክን ማስደሰት ከፈለጉ መጥፎ ነገሮችን መሥራት ማቆም እንዳለባቸው ነገራቸው። አብዛኞቹ ሰዎች ዮሐንስ የሚያስተምረውን ትምህርት ከሰሙ በኋላ ከኃጢአታቸው ንስሐ ገቡ፤ ከዚያም ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ አጠመቃቸው።

ዮሐንስ ሀብት አልነበረውም። ልብሱ ከግመል ፀጉር የተሠራ ሲሆን አንበጣና የጫካ ማር ይበላ ነበር። ሰዎች ስለ ዮሐንስ ማወቅ ይፈልጉ ነበር። ኩራተኛ የሆኑት ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ሳይቀር እሱን ለማየት ይመጡ ነበር። ዮሐንስም እንዲህ አላቸው፦ ‘መጥፎ ሥራችሁን መተውና ንስሐ መግባት አለባችሁ። የአብርሃም ልጆች ነን ስለምትሉ ብቻ ከሌሎች ሰዎች የተሻላችሁ እንደሆናችሁ አድርጋችሁ አታስቡ። እንዲህ ስላላችሁ የአምላክ ልጆች ናችሁ ማለት አይደለም።’

ብዙ ሰዎች ወደ ዮሐንስ መጥተው ‘አምላክን ለማስደሰት ምን ማድረግ አለብን?’ ብለው ጠየቁት። ዮሐንስም አይሁዳውያኑን ‘ሁለት ልብስ ካላችሁ አንዱን ለተቸገረ ሰው ስጡ’ አላቸው። ዮሐንስ እንዲህ ያለው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? አምላክን ማስደሰት ከፈለጉ ሰዎችን መውደድ እንዳለባቸው እንዲገነዘቡ ፈልጎ ስለነበረ ነው።

ዮሐንስ ቀረጥ ሰብሳቢዎቹን ‘ሐቀኞች ሁኑ፤ ሰዎችን አታታሉ’ አላቸው። ወታደሮቹን ደግሞ ‘ጉቦ አትቀበሉ ወይም አትዋሹ’ አላቸው።

ካህናትና ሌዋውያንም ወደ ዮሐንስ መጥተው ‘አንተ ማን ነህ? ሁሉም ሰው ማን እንደሆንክ ማወቅ ይፈልጋል’ በማለት ጠየቁት። ዮሐንስም ‘ኢሳይያስ እንደተናገረው በምድረ በዳ ሰዎችን ስለ ይሖዋ የማስተምር ሰው ነኝ’ አላቸው።

ሕዝቡ ዮሐንስ የሚያስተምረውን ትምህርት ይወዱት ነበር። ብዙ ሰዎች ዮሐንስ መሲሕ መስሏቸው ነበር። እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ ‘ከእኔ የሚበልጥ ይመጣል። እኔ የጫማውን ማሰሪያ እንኳ ለመፍታት አልበቃም። እኔ በውኃ እያጠመቅኩ ነው፤ እሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃል።’

“ይህ ሰው ስለ ብርሃኑ ይመሠክር ዘንድ ምሥክር ሆኖ መጣ፤ ይህን ያደረገው ሁሉም ዓይነት ሰዎች በእሱ በኩል እንዲያምኑ ነው።”—ዮሐንስ 1:7

ጥያቄ፦ ይሖዋ ዮሐንስን ወደ ሕዝቡ የላከው ለምንድን ነው? ሕዝቡ ዮሐንስ የሚያስተምረውን ትምህርት ሲሰሙ ምን አደረጉ?

ማቴዎስ 3:1-11፤ ማርቆስ 1:1-8፤ ሉቃስ 3:1-18፤ ዮሐንስ 1:19-28፤ ኢሳይያስ 40:3

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ