የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 1/15 ገጽ 23
  • “መልካም ለማድረግ አትታክቱ“

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “መልካም ለማድረግ አትታክቱ“
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የክርስቶስ መገለጥና መገኘት
  • በሥርዓት የማይሄዱትን እንዴት መያዝ እንደሚገባ
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • “የማመዛዘን ችሎታችሁ በቶሎ አይናወጥ”!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ለይሖዋ ቀን የተዘጋጃችሁ ሁኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • 1 ተሰሎንቄ የመጽሐፉ ይዘት
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 1/15 ገጽ 23

“መልካም ለማድረግ አትታክቱ”

ከ2 ተሰሎንቄ የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች

ሐዋርያው ጳውሎስ የመቄዶንያ ከተማ በነበረችው በተሰሎንቄ ይኖሩ ለነበሩ ክርስቲያኖች የነበረው አሳቢነት ሁለተኛ መልእክቱን በ51 እዘአ አካባቢ እንዲጽፍ አነሳሳው። በጉባኤው ውስጥ ከነበሩት አንዳንዶቹ ተሳስተው የኢየሱስ ክርስቶስ መገኘት ሊጀምር ነው በማለት ይናገሩ ነበር። ምናልባትም ጳውሎስ ጽፎታል ተብሎ የሚታመንበት ደብዳቤ የይሖዋ ቀን መቅረቡን እንደገለጸ አድርገው በስህተት ተረድተው ሊሆን ይችላል።​—2 ተሰሎንቄ 2:1, 2

ስለዚህ የአንዳንድ የተሰሎንቄ ክርስቲያኖች አስተሳሰብ መስተካከል ነበረበት። ጳውሎስ በሁለተኛ መልእክቱ እያደገ ስለሚሄደው እምነታቸው፣ ስለ ፍቅራቸውና ስለ ታማኝነት ጽናታቸው አመሰገናቸው። ይሁን እንጂ ኢየሱስ ከመገኘቱ በፊት ክህደት እንደሚመጣ ገለጸላቸው። ስለዚህ ከፊታቸው አስቸጋሪ ጊዜ ይጠብቃቸዋል ማለት ነው። ይህ የሐዋርያው መልእክትም “መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ” የሚለውን ምክር ጠብቀው እንዲኖሩ ይረዳቸዋል። (2 ተሰሎንቄ 3:13) የጳውሎስ ቃል እኛንም በተመሳሳይ በዚህ ረገድ ይረዳናል።

የክርስቶስ መገለጥና መገኘት

ጳውሎስ በመጀመሪያ የተናገረው ከመከራ ስለመገላገል ነበር። (1:1-12) ይህም የሚሆነው “ጌታ ኢየሱስ [ከኃያላን] መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ” ነው። በዚህ ጊዜ ምሥራቹን በማይታዘዙ ላይ የዘላለም ጥፋት ይመጣል። አሳዳጆች መከራ በሚያደርሱብን ጊዜ ይህን ማስታወስ በጣም ያጽናናናል።

ቀጥሎም ጳውሎስ ክርስቶስ ከመገለጡ በፊት “የአመጽ ሰው” እንደሚገለጥ አመለከተ። (2:1-17) የተሰሎንቄ ክርስቲያኖች “የይሖዋ ቀን” ጀምሯል በሚል በማንኛውም መልእክት መደናገጥ አልነበረባቸውም። አስቀድሞ ክህደቱ ይመጣና የአመጽ ሰው ይገለጣል። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በመገኘቱ በሚገለጥበት ጊዜ ይህን የአመጽ ሰው ያጠፋዋል። እስከዚያ ድረስ ግን አምላክና ክርስቶስ የተሰሎንቄ ሰዎችን ልብ እንዲያጸኑና “በበጎ ሥራና በቃል ሁሉ” እንዲያጽናኑአቸው ጳውሎስ ጸለየ።

በሥርዓት የማይሄዱትን እንዴት መያዝ እንደሚገባ

ጳውሎስ ቀጥሎ ከጻፋቸው ቃላት መካከል በሥርአት የማይሄዱ ግለሰቦች ምን መደረግ እንደሚገባቸው የሚገልጽ መልእክት ይገኝበታል። (3:1-18) ጌታ የተሰሎንቄ ክርስቲያኖችን እንደሚያበረታና ከክፉው ከሰይጣን ዲያብሎስ እንደሚጠብቃቸው እርግጠኛ መሆኑን ገለጸላቸው። ይሁን እንጂ ለመንፈሣዊ ጥቅማቸው የሚበጅ እርምጃ መውሰድ ነበረባቸው። በማይመለከታቸው ጉዳይ ውስጥ እየገቡና ሥራ ፈቶች እየሆኑ አለሥርአት ከሚሄዱ መራቅ ነበረባቸው። ጳውሎስ “ሊሠራ የማይወድ አይብላ” ሲል አዘዘ። እንደነዚህ ያሉት ሰዎች ምልክት ሊደረግባቸው ይገባ ነበር። በተጨማሪም እንደ ወንድም መመከር ቢኖርባቸውም ከእነርሱ ጋር የወንድማማች ኅብረት ማድረግ አልነበረባቸውም። ታማኞቹ የተሰሎንቄ ክርስቲያኖች መልካም ሥራ ለመሥራት መታከት አይገባቸውም ነበር። በተጨማሪም ጳውሎስ የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከሁሉ ጋር እንዲሆን ተመኘላቸው።

ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች የጻፈው ሁለተኛ መልእክት የይሖዋ ምሥክሮች ክርስቶስና መላእክቱ ምሥራቹን የማይታዘዙትን ሰዎች በሚበቀሉበት ጊዜ ከመከራቸው ሁሉ እንደሚገላገሉ ማረጋገጫ ይሰጣቸዋል። በተጨማሪም “የአመጽ ሰው” እና (የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት ክፍል) መላው የሐሰት ሃይማኖት በቅርብ ጊዜ እንደሚጠፉ ማወቅ በጣም እምነት ያጠነክራል። ይህ እስከሚሆንበት ጊዜ ግን ጳውሎስ መልካም ሥራ ከመሥራት እንዳንታክት የሰጠውን ምክር እየጠበቅን እንኑር።

[በገጽ 23 የሚገኝ ሥዕል/ሣጥን]

የይሖዋ ቃል ፈጥኖ ይጓዛል፦ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ በማለት ጻፈ፣ “ወንድሞች ሆይ፣ [የይሖዋ (አዓት)] ቃል እንዲሮጥ በእናንተ ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር . . . ስለእኛ ጸልዩ።” (2 ተሰሎንቄ 3:1) አንዳንድ ምሁራን ሐዋርያው በሩጫ ቦታ ከሚወዳደሩ ፈጣን ሯጮች ጋር በማመሳሰል መናገሩ እንደነበረ ገልጸዋል። ይህ አባባል ትክክል መሆኑ የሚያጠራጥር ቢሆንም ጳውሎስ እነርሱና የሥራ ባልደረቦቹ የእውነትን ቃል በፍጥነትና አለእንቅፋት ለማሰራጨት እንዲችሉ የተሰሎንቄ ክርስቲያኖች እንዲጸልዩላቸው ጠይቆአል። አምላክ እንደዚህ ያለውን ጸሎት ስለሚሰማ በዚህ በመጨረሻ ዘመን በትልቅ ጥድፊያ በመስበክ ላይ ያለው የምስራች ቃል እየሮጠ ነው። በተጨማሪም የይሖዋ ቃል በተቀበሉት የተሰሎንቄ ሰዎች ዘንድ እንደሆነው ሁሉ ዛሬም በአማኞች ዘንድ ’የአምላክ የማዳን ኃይል’ መሆኑ ታውቆ በመከበር ላይ ነው። (ሮሜ 1:16፤ 1 ተሰሎንቄ 2:13) አምላክ የምሥራቹን ሰባኪዎች ስለሚባርክና የአምላኪዎቹንም ቁጥር በፍጥነት ስለሚያበዛ በጣም ደስተኞች መሆን ይገባናል።​—ኢሳይያስ 60:22

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ