የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 5/1 ገጽ 3
  • በአሸባሪ ዓለም ውስጥ ያለው ወንጀል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በአሸባሪ ዓለም ውስጥ ያለው ወንጀል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በአሸባሪ ዓለም ውስጥ የወንጀልን ጥቃት መቋቋም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • የፖሊስ ጥበቃ—የማያስፈልግበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?
    ንቁ!—2002
  • ወንጀልን ማስቀረት ይቻል ይሆን?
    ንቁ!—2008
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 5/1 ገጽ 3

በአሸባሪ ዓለም ውስጥ ያለው ወንጀል

ወንጀል ዘመናዊ ክስተት አይደለም። የመጀመሪያው ግድያ የተፈጸመው በሺህ ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ቃየን ወንድሙን አቤልን በገደለ ጊዜ ነው። በጾታ መደፈርና ሰዶማዊነት በጥንታዊ የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ተጠቅሰዋል። (ዘፍጥረት 4:8፤ 19:4, 5፤ 34:1-4) የደጉ ሰማሪያዊ ምሳሌ እንደሚያሳየው በመጀመሪያው መቶ ዘመን እዘአ ሰዎች ይዘረፉ ነበር። (ሉቃስ 10:29-37) ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ ያለው ሁኔታ ለየት ያለ ነው።

በኒው ዮርክም ሆነ በለንደን፣ በካልካታ ወይም በጐታ በታላላቅ የዓለም ከተሞች የሚኖሩ ሕዝቦች ከምን ጊዜውም የበለጠ ወንጀል መስፋፋቱና ይበልጥ አስጊ እየሆነ መሄዱ ይሰማቸዋል። “የሥርዓተ አልበኝነት አምልኰ” የሚል ርዕስ አንቀጽ ይዞ የወጣው ኢንዲያ ቱደይ የተሰኘ ጽሑፍ እንደሚከተለው አስፍሯል፦ “አገሪቱን አንድ ላይ የሚያስተሳስረውን ደካማ የሥነ ምግባርና ማህበራዊ ድር ለመበጣጠስ እያሰጋ ያለው አሳሳቢ ጉዳይ የዓመጽ መጨመር፣ ዕብሪት ያለበት ሥርዓተ ቢስነትና አምልኰ ወደመሆን ያደገው ሕገወጥነት ነው።” ፖሊሶች ወንጀልን ለመዋጋት በሚያደርጉት ተጋድሎ አንዳንድ ጊዜ የሕግን ድንበር ለመጣስና ራሳቸውም ወንጀል የተሞላባቸው ዘዴዎችን ለመጠቀም ይገፋፋሉ። ቀደም ሲል የተጠቀሰው የሕንድ ሪፖርት “በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ያሉ ሰዎች መሞት አሁንም በየጊዜው የሚሰማ ዜና ነው” ይላል። ይህ ሁኔታ በሌሎች አገሮችም ያው ነው።

ወንጀል በግለሰቡ ላይ ያለመድረሱ ሁኔታ እየጠበበ ሄዷል። ከዩናይትድ ስቴትስ የመጣ አንድ ዘገባ እንደሚለው “በ1988ቱ ዓመት ውስጥ ከአራት የአሜሪካ ቤተሰቦች ውስጥ አንዱ ወንጀል ወይም ስርቆት ደርሶበታል።” ከዚህም በላይ በአሁኑ ጊዜ ሰዎች ገና በለጋነት ዕድሜ አስከፊ ወንጀሎችን እየፈጸሙ ነው። ቪዥን የተባለ የላቲን አሜሪካን መጽሔት “ከ10 ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ውስጥ ዘጠኙ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ናቸው። ከትውልድ አንጻር ሲታዩ በጣም ልጆች ናቸው፤ ሕጉም ይከላከልላቸዋል” ይላል። እንደገናም ይህ ለአቅመ አዳም ባልደረሱ ልጆች ወንጀል መፈጸሙ ዓለም አቀፍ አዝማሚያ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ከ2,000 ዓመት በፊት እንዲህ በማለት ተንብዮአል፦ “ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፤ ገንዘብን የሚወዱ . . . [ታማኝ ያልሆኑ፤ ተፈጥሮአዊ ፍቅር የሌላቸው (አዓት)] ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣ ከዳተኞች፣ ችኩሎች፣ በትዕቢት የተነፉ፣ . . . ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች እያሳቱና እየሳቱ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።”​—2 ጢሞቴዎስ 3:1-4, 13

ከ1914 ወዲህ በእነዚያ አስጨናቂ የመጨረሻ ቀኖች እየኖርን ለመሆኑ ማስረጃ ሞልቷል። ሁለት የዓለም ጦርነቶችንና ሌሎች አበይት ውጊያዎችን ያሳለፈው ይህ ዓለም በብዙ መንገድ የማይገዛና ቅጥ ያጣ ሆኖአል። ወንጀል ተዛምቷል። በብዙ ከተሞች ወንጀለኞች የሕግ አክባሪ ብዙሃንን አኗኗር እስከመለወጥ ድረስ የበላይነቱን ይዘዋል። አንድ የዩናይትድ ስቴትስ እውቅ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል “እስከ ዛሬ የማያስፈሩን የነበሩ በአሁኑ ጊዜ ብዙ የምንጨነቅባቸው ነገሮች አሉ። እሥር ቤት ውስጥ ሊቆለፍባቸው የሚገቡት ሰዎች በነፃነት ወዲያ ወዲህ ማለት ሲችሉ እኛ ግን አንዳንድ ጊዜ በጣም ከመፍራታችን የተነሣ እሥረኞች ሆነናል” ሲሉ እንደተናገሩት ነው።

በዚህም ምክንያት ሰዎች ከዛሬ ሃያ ወይም ሰላሳ ዓመታት በፊት የማያስፈልጉ የነበሩ ብዙ ጥንቃቄዎችን አሁን እያደረጉ ነው። መዝጊያዎች ሁለትና ሦስት መቀርቀሪያዎች አላቸው። እንደገናም በአረብ ብረት ይታሸጋሉ። በብዙ ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች ማጅራት መቺዎች ሲፈትሹ ምንም ሲያጡባቸው እንዳይደበድቧቸው ይረዳል ብለው ተስፋ በማድረግ በቂ ገንዘብ ይዘው ይሄዳሉ። ብዙ ጐዳናዎች ጸሐይ ከገባች በኋላ ጭር ይላሉ። የሚዘወተሩት በቂሎች፣ በአጉል ጀብደኞችና በከተማው ለሚንቀዋለሉት አዳኞች ቀላል ዒላማ የሆኑ ሁኔታዎች ተገደው በጐዳና ላይ በሚኖሩ ብቻ ሆኗል።

በዚህ አሸባሪ በሆነና ቅጥ ባጣው ዓለም ውስጥ በወንጀል እንዳንጠቃ ምን ለማድረግ እንችላለን? እንዴትስ ልንቋቋመው እንችላለን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ