የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 11/1 ገጽ 6
  • ለሕይወት ቅድስና አክብሮት ማሳየት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለሕይወት ቅድስና አክብሮት ማሳየት
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የይሖዋ ምሥክሮችና የሕክምና ባለሙያዎች ተባብረው ይሠራሉ
    ንቁ!—1994
  • የደም ቅድስናን ለማክበር የተደረገ እርዳታ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • የሐኪም ሙያ
    ንቁ!—1993
  • ዓይነ ሥውር ሳለሁ ማየት ቻልኩ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 11/1 ገጽ 6

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

ለሕይወት ቅድስና አክብሮት ማሳየት

ደም በአምላክ ዓይን ክቡር እንደሆነና በደም አላግባብ መጠቀምን አምላክ እንደሚያወግዝ መጽሐፍ ቅዱስ ያሳያል። (ዘሌዋውያን 17:​14፤ ሥራ 15:​19, 20, 28, 29) እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች መሠረት በማድረግ የይሖዋ ምስክሮች ደም አይወስዱም።

ዶክተሮች እና የሆስፒታል ሠራተኞች የይሖዋ ምስክሮች በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸውን ሃይማኖ ታዊ አቋም እንዲረዱና የደም ምትክ የሚሆኑ ሌሎች መድኃኒቶችን የሚወስዱ መሆናቸውን እንዲገነዘቡ ለመርዳት የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር በተለያዩ አገሮች የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴዎችን አደራጅቷል። የእነዚህ ኮሚቴዎች አባላት በሆስፒታሎች እየተዘዋወሩ ከሕክምና ባለሙያዎች ጋር ይነጋገራሉ። በቅርቡ በ12 የፖላንድ ከተሞች በአብዛኛው የክሊኒኮችና የሆስፒታል ክፍሎች ኃላፊዎች ከሆኑ ከ500 የሚበልጡ ዶክተሮች ጋር 200 የሚያክሉ ስብሰባዎች ተደርገዋል። ይህ ኮሚቴ ካደረጋቸው ይህን ከመሰሉት ጉብኝቶች በአንደኛው ከጥሎ ያለው ሁኔታ ተፈጽሟል:-

“በዛብርዜ በሚገኘው የልብ ቀዶ ሕክምና ክሊኒክ ውስጥ የተደረገው ስብሰባ ከፍተኛ ውጤት ያስገኘ ነበር። ከ1986 ጀምሮ በክሊኒኩ የሚገኘው የሕክምና ቡድን ለወንድሞቻችን ያለ ደም ቀዶ ሕክምና ሲያካሂድ ቆይቷል። እስከ አሁን ድረስ ደም ያልተሰጣቸው 40 የሚያክሉ ቀዶ ሕክምናዎች በዚህ ክሊኒክ ተደርገዋል። ክሊኒኩ ከመላው ፖላንድም ሆነ ከውጭ አገሮች በሽተኞችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጁ ነው። ከ50 ደቂቃ ውይይት በኋላ በሆስፒታሉ የአንድ ክፍል ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴውን አባላት ለበሽተኞቹ ካስተዋወቁ በኋላ እንዲህ አሉ:- ‘እነዚህ ሰዎች የይሖዋ ምስክሮች ናቸው። ከክሊኒካችን ጋር ይተባበራሉ፤ እኛንም ይረዱናል። ከሚሰጡት እርዳታ የእምነት ጓደኞቻቸው ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች በሽተኞች ጭምር ይጠቀማሉ። የይሖዋ ምስክሮች ምስጋና ይግባቸውና ከባድ የሆኑ የልብ ቀዶ ሕክምናዎችን ያለ ደም ማከናወን እንደሚቻል እርግጠኞች ሆነናል።

“‘ለምሳሌ ያህል [ወደ አንዷ ታካሚያቸው በመጠቆም] ይህችን ሴት ያለ ደም ቀዶ ሕክምና አድርገንላታል፤ ሰኞ ከሆስፒታል ትወጣለች። ላስገነዝብ የምፈልገው ነገር ቢኖር ደም አደገኛ ነገር ስለሆነ አሁን እንደ በፊቱ አዘውትረን በደም እንደማንጠቀም ነው። ደም ከኤድስ ቫይረስ፣ ከሄፒታይተስ እና ቶሎ ካለማገገም ጋር የተያያዘ ነው።

“‘እኔ ካቶሊክ ነኝ፤ ነገር ግን ቤተሰባችን የሌሎችን አስተሳሰብ ያከብራል። አንድ ቀን ከልጆቼ ጋር በሾሎስኬ ስታዲየም በኩል አልፍ ነበር። ይህ ስታዲየም ፈጽሞ ተጥሎ ነበር። አሁን ግን ልንገምተው ከምንችለው በላይ እንደተለወጠ አስተዋልን። ከሠራተኞቹ አንዱን ስታዲየሙ እንዴት እንደዚህ ሊለወጥ እንደቻለ ጠየቅሁት። አስተዳደሩ ስታዲየሙ ፈጽሞ ሊጠገን አይችልም ብሎ ተስፋ ቆርጦ ነበር። ይሁን እንጂ ለይሖዋ ምስክሮች አከራየው። እንደዚህ አድርገው ያደሱት እነርሱ ናቸው አለን።

“‘ስለዚህ ከእነዚህ ሰዎች ብዙ ልንማር የምንችለው ነገር አለ። በዚህ የሆስፒታል ክፍል የምንገኝ ሁሉ የሌሎችን አመለካከት መቃወም እንደሌለብን ይሰማናል።’ ከዚያም ከጥቂት ቀናት በኋላ ቀዶ ሕክምና የሚደረግላትን ምስክር በማመልከት ‘ይህች ሴት የይሖዋ ምስክር ናት። ደም ሳይሰጣት ቀዶ ሕክምና ይደረግላታል’ አሉ።”

የይሖዋ ምስክሮች የእኛን እምነት ካልያዛችሁ ብለው ሌሎች ሰዎችን አይጫኑም። በበኩላቸው ግን የሐዋርያትን ምሳሌ በመከተል “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር” ይታዘዛሉ። (ሥራ 5:​29) ይህም ለደም አክብሮት ማሳየትን ይጨምራል። በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸውን ጽኑ ሃይማኖታዊ አቋም የሚያከብሩላቸውን ሰዎች የይሖዋ ምስክሮች ያደንቃሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ