የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 4/15 ገጽ 3-4
  • ሰብአዊ አመራር ከሽፏልን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሰብአዊ አመራር ከሽፏልን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እምነት የሚጣልበት አመራር ከየት ልታገኝ ትችላለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ድህነትን ለማስወገድ የተደረጉ ጥረቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • በሁሉም ነገሮች የአምላክን መመሪያ ፈልጉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 4/15 ገጽ 3-4

ሰብአዊ አመራር ከሽፏልን?

ሁሉን ነገር የፈጠረው ማን ነው? መልስህ “አምላክ ነው” የሚል ከሆነ በመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ማለትም በፈጣሪ ከሚያምኑት በሚልዮን ከሚቆጠሩ ሰዎች ጋር ትስማማለህ ማለት ነው።

ይሁን እንጂ በአምላክ እናምናለን የሚሉ ብዙ ሰዎች የሰው ልጆችን ችግሮች ለመፍታት አምላክ እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆኑን ለመቀበል ይቸገራሉ። አምላክ ለሰው ልጆች እፎይታን የሚያመጣ በመካሄድ ላይ ያለ ፕሮግራም አለው ብሎ ማሰብ ትክክል ነውን? ብዙ ሰዎች እንደዚህ ያለው ፕሮግራም በመካሄድ ላይ መሆኑን የሚያሳምናቸው ምክንያታዊ ማስረጃ አላገኙም።

በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ሰዎች ያለ አምላክ እርዳታ በራሳቸው ዘዴ ብዙ መፍትሔዎችን ለማግኘት ሲሞክሩ ቆይተዋል። ነገር ግን ሰዎች መፍትሔዎችን አግኝተዋልን? ወይስ ችግሮቹ ይበልጥ ሊፈቱ የማይችሉ አስቸጋሪና ከባድ ሆነውባቸዋል? የሰው ልጅ በዓለም ላይ ያሉትን አንገብጋቢ ችግሮች ለመፍታት የሚሞክረው እንዴት ነው?

አንድ ባለሙያ “የኢንዱስትሪው አብዮት ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ ያደጉት አገሮች የዓለምን የተፈጥሮ ሀብት መተኪያ በሌለው የአመራረትና የአጠቃቀም ሂደት በዓለም ከባቢ አየር አማካኝነትና በመልማት ላይ በሚገኙት አገሮች ላይ ጉዳት በማድረስ ከሚገባው በላይ በዝብዘውታል” በማለት ተናግረዋል።

የሰው ልጅ ምድርን ማጥፋቱን ቀጥሏል። በስፓንኛ ቋንቋ የሚታተመው የአርጀቲናውያን ጋዜጣ ክላሪን “በዚህኛው መቶ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ላይ የኢኮኖሚ ስግብግብነት፣ የጥንቃቄ ጉድለትና ቸልተኝነት የሰዎችን ሕይወት ብቻ ሳይሆን ከግምት በላይ በሆነ መንገድ የከባቢው አየር እንዲበከል ላደረጉት ታላላቅ አደጋዎች ተጠያቂ ናቸው” በማለት ተችቷል።

በዘመናዊው ኅብረተሰብ ውስጥ ከፍተኛ ድህነት ቋሚ የሆነ የተለመደ ነገር እየሆነ በመምጣት ላይ ያለ ይመስላል። በዓለም ላይ ሀብታም የሚባሉት አገሮች እንኳ ከድህነት ጫና የተነሣ እየተንገዳገዱ ነው። በካናዳ ቶሮንቶ የሚታተመው ዘ ግሎብ ኤንድ ሜይል በዘገበው መሠረት “አንድ ሦስተኛ የሚያክሉት ካናዳውያን ዕድሜያቸው ለሥራ ከደረሰ በኋላ ለድህነት እንደሚጋለጡ” ተገምቷል። ጋዜጣው በመቀጠል “ለድህነት አንዱ ከፍተኛ ምክንያት የቤተሰብ መፈራረስ ነው። በቅርብ ዓመታት ደግሞ ይህ ሁኔታ በጣም ጨምሯል” በማለት ተናግሯል።

በጣም እየተበላሸ ለሚሄድ ኅብረተሰብ ሌላው ምልክት ደግሞ በዕፅ አላግባብ መጠቀም ነው። የሰው ዘር ይህንን ችግር በተመለከተ ምን ማድረግ ይችላል? በአጠቃላይ ሲታይ ምንም ሊያደርግ እንደማይችል ከሁኔታው መረዳት ይቻላል። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሱስ የሚያስይዙ ዕፆችን አላግባብ በመውሰዳቸው የአካል፣ የአእምሮና የሥነ ምግባር ውድቀት እያጋጠማቸው ነው። ይህ ችግር ደግሞ እንደ ሰደድ እሳት እየተዛመተ ነው።

የሳይንስ ሊቃውንት ከበሽታ ጋር በሚያደርጉት ውጊያ የተሸነፉ ይመስላል። እውነት ነው፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ብዙ ድሎችን ተቀዳጅቷል። ይሁን እንጂ አንዳንድ ሳይንሳዊ ሂደቶች በራሳቸው መድኃኒት የማይበግራቸው አደገኛ የሆኑ በሽታ የሚያመጡ ተዋሕስያን እንዲፈጠሩ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ሰብአዊ መንግሥታት በጣም የተስፋፋውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ሊያቆሙ አልቻሉም። ለምሳሌ ያህል ባርነትን ለማጥፋት የተደረጉ ብዙ ቃለ መሐላዎችና ሕጎች ቢኖሩም በዓለም ዙሪያ ከአንድ መቶ ሚልዮን የሚበልጡ ሰዎች አሠቃቂ በሆነ ባርነት ሥር እንዲሠሩ በሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ የወደቁ መሆናቸው ይገመታል።

ነገር ግን ሰብአዊ አመራር የከሸፈው ለምንድን ነው? የሚከተሉትን ምክንያቶች ተመልከት። ሰብአዊ አመራር የሚመጣው ከሰዎች ነው። ሰዎች ደግሞ ከፍተኛ ጉድለት አለባቸው። የሕይወት ተሞክሯቸው አጭር ከመሆኑም በላይ በአንዳንድ ባሕሎችና አካባቢዎች ብቻ የተወሰነ ነው። እውቀታቸውም ቢሆን ውስን ነው። ምንም ዓይነት አመራር ቢሰጡም ይህንኑ ውስንነታቸውን ያንጸባርቃል። ሐዋርያው ጳውሎስ “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሎአቸዋል” በማለት እንደተናገረው ነው።—ሮሜ 3:23

እንደ እውነቱ ከሆነ አብዛኛው የሰው ዘር የሚያጋጥመው ችግሮችና መከራዎች የሚመጡት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአምላክን አመራር ከመናቅ የተነሣ ነው። ታዲያ እንደዚህ ያለው አመራር ሊገኝ የሚችለው ከየት ነው? አምላክ አመራሩን እንድናገኝ የሚያደርገን እንዴት ነው? የሚቀጥለው ርዕስ ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሆኑትን መልሶች ይዟል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ