የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 6/1 ገጽ 24
  • አምላክ አያዳላም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ አያዳላም
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ከዚህ ዓለም ያልሆነውን’ መንግሥት መጠበቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • በመከራ ውስጥ እያለሁም ይሖዋን የማገልገል መብት በማግኘቴ አመስጋኝ ነኝ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ቆርኔሌዎስ መንፈስ ቅዱስ ተቀበለ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ይሖዋ ‘አያዳላም’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 6/1 ገጽ 24

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

አምላክ አያዳላም

ከ1,900 ዓመታት በፊት ሐዋርያው ጴጥሮስ ቆርኔሌዎስ ለተባለ አንድ መቶ አለቃ ሲመሠክርለት “እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ” ብሎት ነበር። (ሥራ 10:34, 35) ቆርኔሌዎስ ፈሪሃ አምላክ የነበረውና ጽድቅን የሚወድ ሰው ነበር። ጴጥሮስ የሰጠውን ምሥክርነት ተቀብሎ ክርስቲያን ሆነ።

አምላክ አያዳላም የሚለው መሠረታዊ ሥርዓት ዛሬም ይሠራል። በጀርመን ከደረሰ አንድ ተሞክሮ ይህንን ለማየት እንችላለን። ሪፖርቱ እንዲህ ይላል፦

“በጉባኤያችን ክልል ውስጥ አንድ ትልቅ የሩስያ የጦር ሠፈር አለ። በ1989 የበርሊን ግንብ ከፈረሰ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሽማግሌዎች የሩሲያ ቋንቋ መናገር የሚችሉ አስፋፊዎች እንዳሉ ጠየቁ። አንዳንዶቻችን እንችል ስለነበር በዚህ የአገልግሎት ክልል መሥራት ጀመርን፤ ይህም ከፍተኛ ደስታ አምጥቶልናል። ካገኘናቸው ብዙ ተሞክሮዎች አንዱ የሚከተለው ነው፦

“ከአንድ ያልተጠመቀ አስፋፊ ጋር ሆኜ (አሁን ግን ተጠምቋል) አንድ የጦር አዛዥ አነጋገርን። የጦር አዛዡ የምንናገረውን ከሰማ በኋላ ለወታደሮቹም እንድንነግራቸው ጋበዘን። እነሱም ስለ አምላክና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ መስማት አለባቸው አለ። ስለዚህ ተመልሰን ለመምጣት ቀጠሮ ወሰድን።

“የሩሲያ ቋንቋ በደንብ መናገር የምትችል አንዲት እህት አብራን እንድትሄድና አስተርጓሚ እንድትሆንልን ጠየቅናት። በጦር ሰፈሩ ክበብ ውስጥ ጽሑፎቻችንን በአንድ ጠረጴዛ ላይ ደረደርንና 68 ወታደሮችን አነጋገርን። ጥያቄዎቻቸውንም መለስንላቸው። ከዚያ በኋላ 35 መጽሐፎችና ወደ 100 የሚጠጉ መጽሔቶችን በደስታ ወሰዱ። ከክበቡ ስንወጣ ወታደሮቹ በቡድን በቡድን ሆነው በጽሑፎቹ ላይ ሲወያዩ አየናቸው።

“ሐምሌ 4, 1992 ተመልሰን ለመምጣት ተቀጣጠርን። ያን ዕለት ጠዋት በ4:50 ላይ እዚያ ስንደርስ የጦር ሠፈሩ ዘበኛ ወታደሮቹ እየጠበቁን መሆናቸውን ነገረን። አንድ ሻለቃ ወደ ክበቡ ወሰደን። ባለፈው ጊዜ ለጦር ሰፈሩ ቤተ መጻሕፍት ጽሑፍ ወስዳ የነበረች አንዲት ሴት ተመልሰን የምንመጣ መሆናችንን የሚገልጹ ፖስተሮችን በጦር ሰፈሩ ውስጥ በመለጠፍ ማስታወቂያ መንገሯን ሰማን። ሦስት ወንድሞች ስለ ዓለም አቀፉ ሥራችን እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ የምናምነው ለምን እንደሆነ የሚገልጹ አጠር አጠር ያሉ ንግግሮች አቀረቡ። ከዚያም ከአድማጮቻችን ለሚቀርቡልን ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ መልስ ሰጠናቸው። ከጥያቄዎቻቸው መካከል የይሖዋ ምሥክሮች ስለ ውትድርና አገልግሎት ያላቸው አቋም ምንድን ነው? ወታደሮች የሆኑስ አሉ ወይ? የሚሉ ይገኙበታል። ይህም ባለፈው ጊዜ አብሮኝ መጥቶ የነበረው ያልተጠመቀ አስፋፊ ለ25 ዓመት በምሥራቅ ጀርመን በውትድርና እንዳገለገለና፤ በኋለኞቹም ዓመታት የአየር ኃይል ካፒቴን ሆኖ እንደሠራ ለመግለጽ ጥሩ አጋጣሚ ከፈተለት። ከዚያም ስለ አምላክና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ሊማር እንደቻለና አሁን የይሖዋ ምሥክር ለመሆን እንደሚፈልግ ነገራቸው። ወታደሮቹ በሰሙት ነገር በጣም ተገረሙ። ያመጣናቸው ጽሑፎች በሰባት ደቂቃ ውስጥ ወታደሮቹ እጅ ገቡ። ብዙዎቹ መጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት ይፈልጉ ነበር። ከአንድ የመጻሕፍት መደብር ሰባት በሩሲያ ቋንቋ የተጻፉ መጽሐፍ ቅዱሶች አምጥተን ስለነበረ መጽሐፍ ቅዱሶቹን በደስታ ወሰዷቸው። ለእነዚህ በመንፈሳዊ ለተራቡ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ልናካፍላቸው በመቻላችን በጣም ደስ ብሎናል። በሰሙት ነገር ላይ እርምጃ ይወስዳሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።”

እውነትም አምላክ አያዳላም። ልበ ቅን የሆኑ ሰዎች ሁሉ በየትም ቦታ ቢኖሩ በቃሉ አማካኝነት እንዲሳቡ ያደርጋል። ስለ እርሱና ስለ ልጁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲማሩ ይጋብዛቸዋል። ከሁሉም የኑሮ ደረጃዎች የመጡ ብዙ ሰዎች ስለነሱ እየተማሩ ናቸው።—ዮሐንስ 17:3

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ