የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 12/1 ገጽ 21-24
  • ከጎበዝ ተማሪነት ወደ ውጤታማ ሚስዮናዊነት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከጎበዝ ተማሪነት ወደ ውጤታማ ሚስዮናዊነት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቀናተኛ ተማሪዎች ከአገልግሎት ደስታ ያገኛሉ
  • የረዥም ጊዜ ሚስዮናውያን ስኬታማ የሆኑበትን ምሥጢር ተናገሩ
  • የፈቃደኝነት መንፈስ ለጊልያድ ያበቃል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • በይሖዋ ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ለማገልገል ተነሳሱ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • የአምላክ ቃል ተማሪዎችን ማስመረቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 12/1 ገጽ 21-24

ከጎበዝ ተማሪነት ወደ ውጤታማ ሚስዮናዊነት

“አሁንም እንኳ ሳስበው ይህን መብት ማግኘታችን እውነት እውነት አይመስለኝም!” ዊል ከባለቤቱ ከፓትሲ ጋር በጊልያድ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት የ103ኛው ክፍል ተማሪዎች በመሆን ያገኙትን ሥልጠና ባጠናቀቁበት ወቅት የተሰማውን ሲናገር ከላይ ያለውን ብሏል። ዛሂድና ጄኒ በዚህ ሐሳብ ይስማማሉ። “እዚህ በመገኘታችን ክብር ይሰማናል” ብለዋል። ሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን በትጋት ተከታትለዋል። ሚስዮናውያን በመሆን የሚያከናውኑትን ሥራ ለመጀመር ጓጉተዋል። ከዚያ በፊት ግን መስከረም 6, 1997 በተካሄደው የምረቃ ፕሮግራም ላይ በሚስዮናዊ ምድባቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ፍቅራዊ ምክር ተቀብለዋል።

የፕሮግራሙ ሊቀ መንበር የአስተዳደር አካል አባል የሆነው ቴዎዶር ጃራዝ ነበር። ከቤቴል ቤተሰብና ከ48 የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ቅርንጫፍ ቢሮዎች የመጡ ተወካዮች ጋር ከካናዳ፣ ከአውሮፓ፣ ከፖርቶ ሪኮና ከዩናይትድ ስቴትስ የመጡ ጓደኞችና ዘመዶች ለተማሪዎቹ ድጋፋቸውንና ፍቅራቸውን ለመግለጽ በቦታው መገኘታቸውን ገለጸ። ወንድም ጃራዝ የሕዝበ ክርስትና አብያተ ክርስቲያናት የሚልኳቸው ሚስዮናውያን የሚስዮናዊ ሥራቸውን ትተው በዓለማዊ ትምህርት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ እንደሚጣጣሩ አልፎ ተርፎም በፖለቲካ እንደሚጠላለፉ ገልጿል። ከዚህ በተቃራኒ ግን የጊልያድ ምሩቃን ባገኙት ሥልጠና መሠረት ይሠራሉ። ለሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ያስተምራሉ።

በማኅበሩ የብሩክሊን ቢሮ የሚያገለግለው ሮበርት በትለር “አካሄዳችሁ ስኬታማ ይሁን” በሚል ጭብጥ ንግግር አቀረበ። ሰዎች ስኬታማነታቸውን የሚለኩት ባካበቱት የገንዘብ መጠን ወይም በግል ባገኟቸው ሌሎች ነገሮች ቢሆንም ሊያሳስበን የሚገባው አምላክ ስኬታማነትን የሚለካበት መንገድ ነው። የኢየሱስን አገልግሎት ስኬታማ ያደረገው በርካታ ተከታዮችን ማፍራቱ ሳይሆን ለተሰጠው ሥራ የታመነ ሆኖ መገኘቱ ነበር። ኢየሱስ ለይሖዋ ክብር አምጥቷል፤ እንዲሁም በዓለም አልተበከለም። (ዮሐንስ 16:​33፤ 17:​4) እነዚህ ነገሮች እያንዳንዱ ክርስቲያንም ሊያደርጋቸው የሚችላቸው ነገሮች ናቸው።

ቀደም ሲል በሩቅ ምሥራቅ በሚስዮናዊነት ያገለገለው ሮበርት ፔቪ “ለሰው ሁሉ ባሪያዎች ሁኑ” በማለት ይመክራል። ሐዋርያው ጳውሎስ ውጤታማ ሚስዮናዊ ነበር። ምሥጢሩ ምን ነበር? ራሱን ለሁሉ ባሪያ አድርጎ ነበር። (1 ቆሮንቶስ 9:​19-23) ተናጋሪው እንዲህ ሲል አብራራ:- “ይህን የመሰለ አመለካከት ያለው አንድ የጊልያድ ምሩቅ የሚስዮናዊነት አገልግሎቱን እንደ ሥራ እድገት ማለትም በድርጅቱ ውስጥ ቁልፍ ቦታዎችን ለመያዝ የሚያስችል መወጣጫ አድርጎ አይመለከተውም። አንድ ሚስዮናዊ ወደ ሥራ ምድቡ የሚሄደው ለአንድ ዓላማ ነው። ይኸውም ለማገልገል ነው። ምክንያቱም ባሪያዎችም የሚያደርጉት ይህንኑ ነው።”

የአስተዳደር አካል አባል የሆነው ጌርት ሌሽ ምክሩን በአብዛኛው በ2 ቆሮንቶስ ምዕራፍ 3 እና 4 ላይ በማስመርኮዝ “የይሖዋን ክብር እንደ መስተዋት አንጸባርቁ” ሲል ተማሪዎቹን አጥብቆ አሳስቧቸዋል። የአምላክ እውቀት እንደ ብርሃን ሲሆን አንድ ክርስቲያን ልቡን ክፍት ካደረገ ሊበራለት እንደሚችል አሳስቧቸዋል። ይህን ብርሃን የምናንጸባርቀው ምሥራቹን በመስበክና በመልካም አኗኗር በመመላለስ ነው። “አንዳንድ ጊዜ ብቁ እንዳልሆናችሁ ይሰማችሁ ይሆናል። እንዲህ ዓይነት ስሜት ሲሰማችሁ ‘የኃይሉ ታላቅነት ከአምላክ ይሆን ዘንድ’ በይሖዋ ታመኑ” ሲል ተናግሯል። (2 ቆሮንቶስ 4:​7) ወንድም ሌሽ በ2 ቆሮንቶስ 4:​1 ላይ ተመዝግበው የሚገኙትን የጳውሎስ ቃላት በማስተጋባት “የሚስዮናዊነት ሥራችሁን አታቋርጡ። መስተዋታችሁ ሁልጊዜ የተወለወለ ይሁን!” ሲል ተማሪዎቹን በጥብቅ አሳስቧል።

የጊልያድ ፋካልቲ አባል የሆነው ካርል አዳምስ “ይሖዋ የት ነው?” የሚል ጭብጥ ያለው ትኩረት የሚስብ ንግግር አቀረበ። ጥያቄው የቀረበው አምላክ በአጽናፈ ዓለም ውስጥ የሚገኝበትን ቦታ ለማመልከት ሳይሆን የይሖዋን አመለካከት እንዲሁም አመራሩን የሚጠቁሙ ነገሮችን ግምት ውስጥ የማስገባቱን አስፈላጊነት ለመጠቆም ነበር። “በይሖዋ አገልግሎት በርካታ ዓመታት ያሳለፈ ሰውም እንኳ ቢሆን ውጥረት ውስጥ ሲገባ ይህን ጉዳይ ሊዘነጋ ይችላል” ብሏል። (ኢዮብ 35:​10) ስላለንበት ዘመንስ ምን ለማለት ይቻላል? በ1942 የአምላክ ሕዝቦች መመሪያ ማግኘት አስፈልጓቸው ነበር። የስብከቱ ሥራ ማብቂያ ተቃርቧል ወይስ ገና ብዙ የሚሠራ ሥራ ይኖራል? ይሖዋ ለሕዝቦቹ ያለው ዓላማ ምንድን ነበር? የአምላክን ቃል ባጠኑ ቁጥር መልሱ ግልጽ እየሆነ መጣ። “ዓመቱ ከማብቃቱ በፊት” አለ ወንድም አዳምስ “የጊልያድ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤትን ለማቋቋም እቅድ ተነደፈ።” በእርግጥም ይሖዋ፣ ይህ ትምህርት ቤት የሚልካቸውን ሚስዮናውያን ሥራ ባርኳል።

ቀጥሎ ንግግር ያቀረበው የጊልያድ አስተማሪ ማርክ ኑሜር ነበር። “ምናናችሁን የምትጠቀሙት እንዴት ነው?” የሚል ጭብጥ ባለው ንግግሩ ተማሪዎቹ ከጊልያድ ያገኙትን ሥልጠና በአዲሱ ምድብ ቦታቸው እንደደረሱ ወዲያውኑ በተግባር እንዲተረጉሙት አበረታቷል። “ሌሎችን ለመቅረብ ጥረት አድርጉ። ራሳችሁን ከሁኔታው ጋር አስማምታችሁ ኑሩ። የአገሩን ባሕል፣ ታሪክና ጨዋታ ለመማር ልባዊ ጥረት አድርጉ። ቋንቋውን ወዲያውኑ መማራችሁ ከምድብ ቦታችሁ ጋር ራሳችሁን በቶሎ ለማላመድ ያስችላችኋል” ብሏቸዋል።

ቀናተኛ ተማሪዎች ከአገልግሎት ደስታ ያገኛሉ

ተማሪዎቹ በጊልያድ የሚሰጠውን ትምህርት በትኩረት ከመከታተላቸውም በተጨማሪ በአካባቢው በሚገኙ 11 ጉባኤዎች ውስጥ ተመድበው ነበር። በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በስብከቱ እንቅስቃሴ በቅንዓት ተካፍለዋል። በጊልያድ ፋካልቲ ውስጥ የሚያገለግለው ዋለስ ሊቨረንስ አንዳንድ ተሞክሮዎቻቸውን ለአድማጮቻቸው እንዲያካፍሉ የተወሰኑ ተማሪዎች ጋብዞ ነበር። በትላልቅ የገበያ አዳራሾች፣ በመኪና ማቆሚያዎች፣ በንግድ አካባቢዎች፣ በመንገድ ላይና ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ በሚሰብኩበት ጊዜ ያጋጠማቸውን ተሞክሮ ሲናገሩ ደስታቸው በፊታቸው ላይ ይነበብ ነበር። አንዳንዶቹ በጉባኤያቸው ክልል ውስጥ የሚኖሩና የሚሠሩ የሌላ አገር ቋንቋ ተናጋሪዎችን ለማነጋገር ጥረት አድርገዋል። የ103ኛው ክፍል አባላት አምስት ወራት በፈጀው በዚህ ሥልጠናቸው ወቅት ቢያንስ አሥር የሚያክሉ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን አስጀምረዋል መርተዋልም።

የረዥም ጊዜ ሚስዮናውያን ስኬታማ የሆኑበትን ምሥጢር ተናገሩ

አስደሳች ከሆነው ከዚህ የፕሮግራሙ ክፍል ቀጥሎ ፓትሪክ ላፍራንካ እና ዊልያም ቫን ደ ዎል ሰባት የቅርንጫፍ ኮሚቴ አባላትን በመጋበዝ በሚስዮናዊ ሥራቸው ወቅት ያገኟቸውን ትምህርቶች እንዲናገሩ በማድረግ ለተማሪዎቹ የሚጠቅም ክፍል አቅርበዋል። ተመራቂዎቹ የሚስዮናዊነት ምድባቸውን ከይሖዋ የተገኘ አድርገው እንዲመለከቱና ሥራቸውንም የሙጥኝ ብለው እንዲይዙ አጥብቀው መክረዋቸዋል። በጊልያድ የሠለጠኑ ሚስዮናውያን በሌሎች አገሮች በሚከናወነው ሥራ ላይ የሚያሳድሩትን በጎ ተጽእኖ ጠቅሰዋል።

እነዚህን የቅርንጫፍ ቢሮ ኮሚቴ አባላት ለአሥርተ ዓመታት ደስተኛና ፍሬያማ ሚስዮናውያን ሆነው እንዲቀጥሉ ያስቻላቸው ምንድን ነው? በአካባቢው ከሚገኙ ወንድሞች ጋር ተቀራርበው መሥራታቸውና ከእነርሱም መማራቸው ነው። ምድብ ቦታቸው እንደደረሱ ወዲያውኑ ቋንቋውን ለመማር ጥረት አድርገዋል። እንደ ሁኔታው መለዋወጥንና ከአካባቢው ልማድ ጋር ራስን ማላመድን ተምረዋል። የጊልያድ የመጀመሪያው ክፍል ምሩቅ የሆነውና ለ54 ዓመታት በሚስዮናዊነት ያገለገለው ቻርለስ አይዘናወር ውጤታማ ሚስዮናውያን የተማሯቸውን አምስት “ምሥጢሮች” ዘርዝሯል:- (1) መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትሮ ማጥናት፣ (2) ቋንቋውን ማጥናት፣ (3) በአገልግሎት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ፣ (4) በሚስዮናውያን ቤት ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ መጣርና (5) ወደ ይሖዋ አዘውትሮ መጸለይ ናቸው። ተማሪዎቹ እነዚህ ተሞክሮ ያካበቱ ሚስዮናውያን የሰጧቸው ተግባራዊ ምክር ብቻ ሳይሆን በፊታቸው ላይ ይነበብ የነበረው በይሖዋ አገልግሎት ያገኙት ደስታም ነክቷቸዋል። አርማንዶና ሉፕ “ስለ ሕይወታቸው ሲናገሩ ደስተኞች ናቸው” ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።

ቃለ ምልልሶቹ ካበቁ በኋላ የቀረው አንድ ንግግር ነበር። የአስተዳደር አካል አባል የሆነው አልበርት ሽሮደር ለንግግሩ የመረጠው ጭብጥ “የታመኑ የአምላክ ቃል መጋቢዎች መሆን ውድ የእውነት ፈርጦችን ያሳውቃል” የሚል ነበር። የጊልያድ ትምህርት ቤት ዋነኛው የመማሪያ መጽሐፍ፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደመሆኑ መጠን ተማሪዎቹ የሚለውን ለማዳመጥ ጓጉተው ነበር። ወንድም ሽሮደር ከ50 ዓመት በፊት የአዲሲቱ ዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ኮሚቴ ቅቡዓን አባላት የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉምን ሥራ ሲጀምሩ ዓላማቸው በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘት አልነበረም። ከዚህ ይልቅ መመሪያ ለማግኘት በመንፈስ ቅዱስ እንደታመኑ ገልጿል። (ኤርምያስ 17:​5-8) ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ በመስኩ የተሰማሩ ሰዎች የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ያለውን ከፍተኛ የጥራት ደረጃ አምነው ተቀብለዋል። አንድ ምሁር ለማኅበሩ በላኩት ደብዳቤ ላይ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል:- “ጥራት ያለው የጽሑፍ ሥራ ምን ዓይነት እንደሆነ አውቃለሁ፤ የእናንተ ‘የአዲሲቱ ዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ኮሚቴ’ ድንቅ ሥራ ሰርቷል።”

ንግግሩ እንዳበቃ ተማሪዎቹ ዲፕሎማቸውን የተቀበሉ ሲሆን የተመደቡባቸውም ቦታዎች ለአድማጮች ተገለጸ። ይህ ጊዜ ለክፍሉ አባላት ሆዳቸውን የሚያላውስ ወቅት ነበር። አንድ የክፍሉ ተወካይ የምስጋና ደብዳቤ በሚያነብበት ጊዜ ብዙዎች ሲቃ ይተናነቃቸውና ዓይኖቻቸው እንባ አቅርረው ይታዩ ነበር። አንዳንዶቹ ተማሪዎች ለሚስዮናዊነት ሥራ ለዓመታት ዝግጅት አድርገዋል። የጊልያድ ኮርስ የሚሰጠው በእንግሊዝኛ ቋንቋ መሆኑን በመገንዘብ ጥቂቶች እንግሊዝኛ ተናጋሪ ወደሆኑ ጉባኤዎች በመዛወር ቋንቋውን በደንብ ለማጥናት ጥረት አድርገዋል። ሌሎች በአገራቸው ውስጥም ሆነ ከአገራቸው ውጪ አቅኚዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉባቸው ቦታዎች ተዛውረዋል። ሌሎች ደግሞ ተሞክሮዎችን በማንበብ፣ ምርምር በማድረግ ወይም ማኅበሩ ያዘጋጀውን ቱ ዚ ኢንድስ ኦቭ ዚ ኧርዝ የተባለውን ቪድዮ ካሴት ደጋግመው በመመልከት ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በመግቢያው ላይ የተጠቀሱት ዊልና ፓትሲ ሌሎች ወንድሞች ለተማሪዎቹ ባሳዩት ወዳጃዊ ስሜት እጅግ ተደንቀው ነበር። “የማያውቁን ሰዎች እንኳን ሳይቀር አቅፈው ይስሙንና ፎቶ ግራፍ ያነሱን ነበር። አንድ የአስተዳደር አካል አባል እጃችንን ከጨበጠ በኋላ ‘እንኮራባችኋለን’ ብሎናል!” የ103ኛው ክፍል አባላት ከልብ የሚወደዱ መሆናቸው ምንም አያጠራጥርም። በሚገባ ሠልጥነዋል። በጊልያድ ያገኙት ሥልጠና ከጎበዝ ተማሪነት ወደ ውጤታማ ሚስዮናዊነት ለመሸጋገር ያስችላቸዋል።

[በገጽ 22 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

ስለ ተማሪዎቹ የቀረበ አኃዛዊ መረጃ

ሚስዮናውያኑ የተውጣጡባቸው አገሮች:- 9

የተመደቡባቸው አገሮች ብዛት:- 18

የተማሪዎቹ ብዛት:- 48

ባልና ሚስት የሆኑ:- 24

አማካይ ዕድሜ:- 33

በእውነት ውስጥ የቆዩባቸው ዓመታት በአማካይ:- 16

በሙሉ ጊዜ አገልግሎት የቆዩባቸው ዓመታት በአማካይ:- 12

[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ከጊልያድ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት የተመረቁ የ103ኛው ክፍል ተማሪዎች

ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር ለእያንዳንዱ ረድፍ ተራ ቁጥር የተሰጠው ከፊት ወደ ኋላ ሲሆን ስሞቹ የሰፈሩት ከግራ ወደ ቀኝ ነው።

(1) በን ኤ፣ ዳልስቴድ ኤም፣ ካምፓንያ ዜድ፣ ቦያጁሉ አር፣ ኦጋንዶ ጂ፣ ኒከንቸክ ቲ፣ ሜልቭን ኤስ (2) ሜይ ኤም፣ ማፕላ ኤም፣ ልዊን ጄ፣ ሃይታማ ዲ፣ ሄርናንዴስ ሲ፣ ቦያጁሉ ኤን፣ ስተርም ኤ፣ ሜልቭን ኬ (3) ቶም ጄ፣ ማፕላ ኢ፣ ኖል ኤም፣ ቲዝዴል ፒ፣ ራይት ፒ፣ ፔሬስ ኤል፣ ሼንፌልት ኤም፣ ፓክ ኤች (4) መርፊ ኤም፣ ካምፓንያ ጄ፣ ስቲዋርት ኤስ፣ ቼሬዳ ኤም፣ ሪድ ኤም፣ ፔሬስ ኤ፣ ቲዝዴል ደብልዩ፣ ፓክ ጄ (5) ስቲዋርት ዲ፣ ራይት ኤ፣ ቼሬዳ ፒ፣ ኒከንቸክ ኤፍ፣ ሪድ ጄ፣ ሃይታማ ኬ፣ ኦጋንዶ ሲ፣ ሼንፌልት አር (6) መርፊ ቲ፣ ሄርናንዴስ ጄ፣ ኖል ኤም፣ በን ቢ፣ ቶም አር፣ ዳልስቴድ ቲ፣ ልዊን ዜድ፣ ሜይ አር፣ ስተርም ኤ

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የት ይሆን የምንሄደው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ