የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w06 7/15 ገጽ 3
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጀመሪያው ኃጢአት ምን ነበር?
    ንቁ!—2006
  • በገነት ውስጥ የነበረው ሕይወት ምን ይመስል ነበር?
    አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • በገነት ውስጥ የመኖር መብት አጡ
    መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
  • ክፋት እስከ ዛሬ ያልተወገደው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
w06 7/15 ገጽ 3

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

በሰው ልጅ ታሪክ መጀመሪያ ላይ አንድ አሳዛኝ ክስተት ተፈጸመ! አንድ መልአክ የፈጣሪውን ሥልጣን ተገዳደረ። ይህ ዓመጸኛ መልአክ የመጀመሪያዋን ሴት ሔዋንን በማታለል ከተከለከለው ፍሬ እንድትበላ አደረጋት። መልአኩ፣ እሷንና ባሏን አዳምን እንዲህ አላቸው:- “መሞት እንኳ አትሞቱም፤ ከፍሬው በበላችሁ ጊዜ ዐይናችሁ እንደሚከፈትና መልካምና ክፉን በማወቅ፣ እንደ እግዚአብሔር እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው።” (ዘፍጥረት 2:16, 17፤ 3:1-5) በዚህ ምክንያት ይህ ዓመጸኛ መልአክ ዲያብሎስና ሰይጣን ተብሎ መጠራት ጀመረ።—ራእይ 12:9

ሔዋን ሰይጣን ለተናገራቸው ቃላት ትኩረት ሰጥታ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይነግረናል:- “ሴቲቱ የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዐይን የሚያስደስትና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ፣ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከእርሷም ጋር ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።” (ዘፍጥረት 3:6) አዎን፣ የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት የሆኑት አዳምና ሔዋን ከሰይጣን ጋር በመተባበር ዓመጹ። በዚህ ምክንያት ከገነት የተባረሩ ሲሆን ዘሮቻቸውም በገነት የመኖር አጋጣሚ አጡ። የአዳምና የሔዋን ልጆች ፍጹም ሆነው የዘላለም ሕይወት ማግኘት ይችሉ የነበረ ቢሆንም ወላጆቻቸው ባለመታዘዛቸው ምክንያት ኃጢአትና ሞትን ወረሱ።—ሮሜ 5:12

የአጽናፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ገዥ የሆነው ይሖዋ አምላክ በዚህ ጊዜ ምን አደረገ? የኃጢአት ይቅርታ ሊያስገኝ የሚችል ዝግጅት አደረገ። (ሮሜ 5:8) ከዚህም በተጨማሪ ይህንን ችግር ለማስተካከል ይሖዋ አምላክ አንድ መንግሥት አቋቋመ። ይህ ዝግጅት “የእግዚአብሔር መንግሥት” ተብሎ ይጠራል። (ሉቃስ 21:31) ይህ መንግሥት በአምላክ አጽናፈ ዓለማዊ አገዛዝ ሥር የተወሰነ ዓላማ ለማስፈጸም የተቋቋመ ነው።

የአምላክ መንግሥት ዓላማው ምንድን ነው? የዚህ መንግሥት አንዳንድ ገጽታዎች ምንድን ናቸው? ይህ መንግሥት ከሰብዓዊ አገዛዝ አንጻር ሲታይ ምን ይመስላል? መንግሥቱ መግዛት የጀመረውስ መቼ ነው? እነዚህ ጥያቄዎች በሚቀጥለው ርዕስ ውስጥ ይብራራሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ