የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 5/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በፍርድ ቀን ምን ነገሮች ይከናወናሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • የፍርድ ቀንና ከዚያ በኋላ ያለው ጊዜ
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • የፍርድ ቀን ምንድን ነው?
    ንቁ!—2010
  • የፍርድ ቀን ምንድን ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 5/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የፍርድ ቀን ምንድን ነው?

በሺው ዓመት ግዛት ወቅት በትንሣኤ አማካኝነት ዳግመኛ በመገናኘቱ የተደሰተ ቤተሰብ

የፍርድ ቀን አስደሳች ጊዜ የሚሆነው ለምንድን ነው?

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን አምላክ መሳፍንትን በማስነሳት ሕዝቡን ከሚደርስባቸው ፍትሕ የጎደለው ድርጊት ያድን ነበር። (መሳፍንት 2:18) መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱ የፍርድ ቀን የምድር ሁሉ ፈራጅ የሆነው ይሖዋ የሰው ዘርን ከፍትሕ መጓደል የሚያድንበት አስደሳች ጊዜ እንደሚሆን ይናገራል።—መዝሙር 96:12, 13⁠ን እና ኢሳይያስ 26:9⁠ን አንብብ።

አምላክ ፈራጅ አድርጎ የሾመው ኢየሱስ ሕያዋንም ሆኑ ሙታን ፍትሕ እንዲያገኙ ያደርጋል። (የሐዋርያት ሥራ 10:42፤ 17:31) ብዙ ሰዎች አምላክን ሳያውቁ ሞተዋል። በፍርድ ቀን ኢየሱስ እንዲህ ያሉትን ሰዎች ዳግመኛ ሕይወት እንዲያገኙ በማድረግ እውነተኛውን አምላክ ማወቅና መውደድ የሚችሉበት አጋጣሚ ይሰጣቸዋል።—የሐዋርያት ሥራ 24:15⁠ን አንብብ።

የፍርድ ቀን ለአንድ ሺህ ዓመት የሚዘልቀው ለምንድን ነው?

ሙታን በሺው ዓመት ግዛት ውስጥ ይነሳሉ። (ራእይ 20:4, 12) የአምላክን መንገዶች አውቀው እሱን ለመታዘዝ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ፍርድ የሚሰጣቸው ከትንሣኤ በኋላ በሚያደርጓቸው ነገሮች እንደሆነ ይነግረናል፤ ይህ ደግሞ ብዙዎች ካላቸው አመለካከት የተለየ ነው።—ሮም 6:7⁠ን አንብብ።

መጽሐፍ ቅዱስ ሺው ዓመት ከመጀመሩ በፊት በድንገት የሚከሰት የፍርድ ቀን እንዳለም ይነግረናል። በዚህ መጽሔት መግቢያ ላይ ያሉት ርዕሶች ይህ ቀን መጨረሻው ተብሎም እንደሚጠራ ይናገራሉ። በዚያን ቀን ይሖዋ ፈሪሃ አምላክ የሌላቸውን ክፉ ሰዎች በሙሉ ያጠፋል። (2 ጴጥሮስ 3:7) በመሆኑም ለአምላክ ያለንን ፍቅር በተግባር ለማሳየት ጥረት እናድርግ።—2 ጴጥሮስ 3:9, 13⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን መጽሐፍ ገጽ 213 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ