የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 9/1 ገጽ 16-17
  • በፍርድ ቀን ምን ነገሮች ይከናወናሉ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በፍርድ ቀን ምን ነገሮች ይከናወናሉ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የፍርድ ቀንና ከዚያ በኋላ ያለው ጊዜ
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • የፍርድ ቀን ምንድን ነው?
    ንቁ!—2010
  • የፍርድ ቀን ምንድን ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 9/1 ገጽ 16-17

ከአምላክ ቃል ተማር

በፍርድ ቀን ምን ነገሮች ይከናወናሉ?

ይህ ርዕስ በአእምሮህ ሊመላለሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን በማንሳት መልሶቹን መጽሐፍ ቅዱስህ ውስጥ የት ቦታ ላይ ማግኘት እንደምትችል ይጠቁምሃል። የይሖዋ ምሥክሮች ለጥያቄዎቹ በተሰጡት መልሶች ላይ ከአንተ ጋር ለመወያየት ፈቃደኞች ናቸው።

1. የፍርድ ቀን ምንድን ነው?

[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በቀኝ በኩል ካለው ሥዕል መመልከት እንደሚቻለው ብዙ ሰዎች፣ በፍርድ ቀን በቢሊዮን የሚቆጠሩ ነፍሳት በአምላክ ዙፋን ፊት ቀርበው ከዚያ ቀደም በሠሩት ነገር መሠረት እንደሚፈረድባቸው ያስባሉ፤ በዚህ ወቅት አንዳንዶች በሰማይ ሕይወት እንደሚያገኙ ሌሎች ደግሞ በገሃነመ እሳት እንደሚሠቃዩ ያምናሉ። ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ፣ የፍርድ ቀን የሚመጣው የፍትሕ መጓደልን ለማስወገድ እንደሆነ ይናገራል። (መዝሙር 96:13) አምላክ ፈራጅ አድርጎ የሾመው ኢየሱስ፣ የሰው ልጆች እንደገና ፍትሕ እንዲያገኙ ያደርጋል።—ኢሳይያስ 11:1-5ን እና የሐዋርያት ሥራ 17:31ን አንብብ።

2. የፍርድ ቀን ፍትሕ እንደገና እንዲሰፍን የሚያደርገው እንዴት ነው?

ከሞት የተነሱ ሰዎች በገነት ውስጥ

የመጀመሪያው ሰው አዳም ሆን ብሎ በአምላክ ላይ በማመፅ ዘሮቹ በሙሉ መከራ እንዲደርስባቸው እንዲሁም በኃጢአትና በሞት ባርነት ሥር እንዲወድቁ አድርጓል። (ሮም 5:12) ኢየሱስ ይህን የፍትሕ መዛባት ለማስተካከል ሲል በቢሊዮን የሚቆጠሩ የሞቱ ሰዎች ከሞት እንዲነሱ ማለትም ትንሣኤ እንዲያገኙ ያደርጋል። የራእይ መጽሐፍ እንደሚያሳየው ይህ የሚፈጸመው በክርስቶስ ኢየሱስ የሺህ ዓመት ግዛት ነው።—ራእይ 20:4, 11, 12ን አንብብ።

ከሞት የሚነሱት ሰዎች የሚፈረድባቸው ከመሞታቸው በፊት በፈጸሙት ነገር ሳይሆን በራእይ ምዕራፍ 20 ላይ በተገለጹት “የመጽሐፍ ጥቅልሎች” ላይ ለተጻፉት ነገሮች በሚሰጡት ምላሽ ነው። (ሮም 6:7) ሐዋርያው ጳውሎስ “ጻድቃንም ሆኑ ዓመፀኞች” ከሞት እንደሚነሱ ተናግሯል፤ እነዚህ ሰዎች ስለ አምላክ የመማር አጋጣሚ ይሰጣቸዋል።—የሐዋርያት ሥራ 24:15ን አንብብ።

3. በፍርድ ቀን የትኞቹ ነገሮች ይፈጸማሉ?

ደስተኛ ሰዎች በገነት ውስጥ

ይሖዋ አምላክን ለማወቅና ለማገልገል ምንም ዓይነት አጋጣሚ ሳያገኙ የሞቱ ሰዎች፣ ለውጥ አድርገው መልካም ነገሮችን እንዲያደርጉ ዕድል ይሰጣቸዋል። መልካም ነገር የሚሠሩ ከሆነ የሚያገኙት ትንሣኤ ‘የሕይወት ትንሣኤ’ ይሆናል። ይሁንና ከሞት ከሚነሱት መካከል አንዳንዶቹ የይሖዋን መንገዶች ለመማር ፈቃደኞች አይሆኑም። ስለዚህ የሚያገኙት ትንሣኤ ‘የፍርድ ትንሣኤ’ ይሆንባቸዋል።—ዮሐንስ 5:28, 29ን፣ ኢሳይያስ 26:10ን እና 65:20ን አንብብ።

አንድ ሺህ ዓመት ርዝማኔ ያለው የፍርድ ቀን ወደ ማብቂያው ሲቃረብ ይሖዋ ታዛዥ የሆኑ የሰው ልጆች ቀድሞ ወደነበሩበት የፍጽምና ደረጃ እንዲደርሱ ያደርጋል። (1 ቆሮንቶስ 15:24-28) ታዛዥ ለሆኑ የሰው ልጆች በሙሉ የተሰጠው ይህ ተስፋ እንዴት አስደናቂ ነው! በመጨረሻው ፈተና ወቅት አምላክ፣ ለአንድ ሺህ ዓመት ያህል በጥልቁ ውስጥ የታሰረውን ሰይጣን ዲያብሎስን ይፈታዋል። ሰይጣን ከጥልቁ ከተፈታ በኋላም ሰዎችን ከይሖዋ ለማራቅ ይሞክራል፤ ይሁንና ሰይጣንን የሚቃወሙ ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።—ኢሳይያስ 25:8ን እና ራእይ 20:7-9ን አንብብ።

4. ለሰው ዘር ጥቅም የሚያስገኘው ሌላው የፍርድ ቀን ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ይህ ሥርዓት እንዲጠፋ የሚያደርገውን ክስተት ለማመልከትም “የፍርድ ቀን” የሚለውን ሐረግ ይጠቀማል። በኖኅ ዘመን ክፉ ሰዎችን በሙሉ ጠራርጎ እንዳጠፋው የጥፋት ውኃ ሁሉ ይህ የፍርድ ቀንም የሚመጣው በድንገት ነው። ደስ የሚለው ነገር፣ “ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች” መጥፋታቸው በምድር ላይ አዲስ ሰብዓዊ ኅብረተሰብ እንዲመሠረት መንገድ ይከፍታል፤ በዚያን ጊዜ በምድር ላይ “ጽድቅ ይሰፍናል።”—2 ጴጥሮስ 3:6, 7, 13ን አንብብ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ከገጽ 213-215 ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ