ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ትክክለኛ እውቀት ለሌሎች አካፍል
1 በሰኔ የመስክ አገልግሎታችን ወቅት እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ እናበረክታለን። ወቅታዊ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ውይይት ለመጀመር ምን ትላለህ? ይህንንስ በጣም ግሩም የሆነ መጽሐፍ እንዴት ታስተዋውቃለህ?
2 አዲሶቹን ትራክቶቻችንን መጠቀም፦ አንዳንድ አስፋፊዎች ለሌሎች ጽሑፎችን ከመስጠታቸው በፊት እንኳ የሰውየውን ፍላጎት ለማስተዋል በትራክቶች በመጠቀም የተሳካ ውጤት አግኝተዋል። ይህን ለማከናወን እርዳታ ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው? ይህ ዓለም ከመጥፋት ይተርፍ ይሆን? የተባለውን ትራክት በማበርከት ነው።
ተገቢውን ሰላምታ ካቀረብክ በኋላ እንዲህ ለማለት ትችል ይሆናል፦
◼ “እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቁ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመሆኑ ይስማሙ እንደሆነ ሰዎችን እየጠየቅናቸው ነው። [መልስ እንዲሰጥ ጊዜ ፍቀድለት።] በእርግጥ ብዙ ሰዎች በሰው ዘር የሕይወት አቅጣጫ ላይ ተፅዕኖ አሳድረዋል፤ አንዳንዶችም ለሰው ዘር መሻሻል አስተዋፅዖ አድርገዋል፤ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሌሎቹ ሁሉ ለየት የሚያደርገው ምን እንደሆነ ልብ ይበሉ። [ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።] ሌላ ማንም ለሰው ዘር የዘላለም ሕይወት ለመስጠት ኃይል የለውም። [ትራክቱን ገጽ 3 ላይ አውጣ።] ኢየሱስ እዚህ ምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ከዓለም መጨረሻ በፊት የሚፈጸሙትን ክንውኖች ገልጿል። ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱንም ደስ እንዲላቸው አበረቷቷቸዋል፤ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች መዳን እንደቀረበ የሚያሳዩ ናቸው።” ስለ ክርስቶስ መገኘት አንዳንድ ገጽታዎችን በአጭሩ ከተወያያችሁ በኋላ ትኩረቱን በመንግሥቱ ግዛት ስለሚመጡት በረከቶች ወደሚያሳየው የመጨረሻው ገጽ አዙረው።
3 ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት:- ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ መኖር ለአንተ ምን ትርጉም ይኖረዋል? አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ግርማ ስላላቸው ወንዞች፣ ጸጥታ ስላለው ሸለቆ፣ ውብ የሆኑ እንስሳት እርስ በእርሳቸው በሰላም ስለሚኖሩበት አስደሳች ቦታ ያስባሉ። አሁን ባለው የዓለም ሁኔታ የሚጨነቁ ሰዎች ሰላም የሰፈነበትን የአዲስ ዓለም ተስፋ ፈጽሞ አእምሮን የሚያድስ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ።
4 ለጎረቤቶችህ፣ አብረውህ ለሚሠሩት እና ከቤት ወደ ቤት ለምታገኛቸው አንድ አእምሮን የሚያድስ እና አስደሳች ነገር ለመስጠት ተዘጋጅተሃልን?
“ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት” የተባለውን ትራክት በመጠቀም ከዚህ በታች ካለው ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነገር ልትናገር ትችላለህ፦
◼ “በዚህች ትንሽ ጽሑፍ [ትራክት] ሽፋን ላይ እንደሚታየው ሰዎች በሰላም ለመኖር ይችላሉ ብለው ያስባሉን? [የቤቱ ባለቤት መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] በገጽ 2 ላይ ባለው የመጀመሪያ አንቀጽ ውስጥ ያለውን የመጨረሻ ጥያቄ እስቲ ይመልከቱት። እንዲህ በማለት ይጠይቃል:- ‘ይሁን እንጂ ይህ ዓይነቱ ሁኔታ በምድር ላይ አንድ ቀን ይመጣል ብሎ ማሰብ ሕልም ወይም ቅዠት ነውን?’ [ከዚያም በትራክቱ ውስጥ ቀጥሎ ያለውን አንቀጽ አንብብ።] ይህ ስለ አዲስ ሰማያት እና አዲስ ምድር የተጠቀሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው። በ2 ጴጥሮስ 3:13 ላይ ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስዎን ማምጣት የሚችሉ ከሆነ ስለ ምድር የወደፊት ሁኔታ የበለጠ ለማወቅ መዝሙር 104:5ን ልናነብ እንችላለን።” ወይም ጥቅሱን ከራስህም መጽሐፍ ቅዱስ ልታነበው ትችላለህ። ግለሰቡ ፍላጎት ካሳየ ውይይቱን ታላቁ ሰው ወደ ተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 133 ምራው።
5 የተተከለውን ዘር ‘ለማጠጣት’ ተጨማሪ ተመላልሶ መጠየቆችን ማድረግ ያስፈልጋል። (1 ቆሮ. 3:6, 7) ከዚህ በታች ያለው ርዕስ ታላቁ ሰው በተባለው መጽሐፍ በመጀመሪያ ጉብኝት ጊዜ ወይም በተመላልሶ መጠየቅ ጊዜ እንዴት ጥናት መጀመር እንደሚቻል ሐሳብ ይሰጣል።