በመላው ዓለም የሚሰራጭ ወቅታዊ የመንግሥት ምሥራ
1 እሑድ ሚያዝያ 23 “የሐሰት ሃይማኖት ጥፋት ቀርቧል” በሚል ትኩረት የሚስብ ርዕስ ልዩ የሕዝብ ንግግር ይቀርባል። በዚያን ቀን በሚደረገው ስብሰባ መደምደሚያ ላይ አራት ገጾች ያሉት አእምሮን የሚያመራምር የመንግሥት ምሥራች (ትራክት) ይወጣል። ትራክቱ የያዘው ወቅታዊ መልእክት ከሚያዝያ 24 እስከ ግንቦት 14 ባሉት የሦስት ሳምንታት ጊዜያት ውስጥ በመላው ዓለም ይሰራጫል።
2 በሁሉም የምድር ክፍል የሚኖሩ ሰዎች ግራ ተጋብተዋል። በየትኛውም ቦታ የሚኖሩ ሰዎች በተለያዩ ችግሮች እየተሠቃዩ ነው። የመንግሥት ምሥራች ለሰው ልጆች የትክክለኛ መመሪያ ምንጭ ወደ ሆነው ወደ አምላክ ቃል ስለሚመራቸው እየተከሰተ ያለው ነገር ከልብ ለሚያሳስባቸው ሰዎች በጣም ያስደስታቸዋል። (መዝ. 119:105) የመንግሥት ምሥራች ሚያዝያ 23 ሲወጣ ለማግኘት ሁላችንም እንጓጓለን። እስከዚያ ለዚህ ከፍተኛ የሦስት ሳምንት ዘመቻ ለመዘጋጀት ብዙ የምንሠራው ሥራ ይኖረናል።
3 ሁሉም በቅንዓት እንዲሳተፉ አበረታቷቸው፦ በዚህ ሥራ እነማን ሊሳተፉ ይችላሉ? አስፋፊ የሆነ ሁሉ እንዲህ ለማድረግ እንደሚጓጓ የተረጋገጠ ነው። ዘወትር በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ የሚገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችስ? አንዳንዶች ለተወሰነ ጊዜ ከእኛ ጋር የተሰበሰቡ ሲሆን እያደር እድገት እያደረጉ ናቸው። ቅዱስ ጽሑፋዊ ከሆኑ መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር ሕይወታቸውን አስማምተው ከሆነ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ተደርገው ለመቆጠር ብቃት የላቸውምን? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱን የሚመራው አስፋፊ ጉዳዩን ከተማሪው ጋር ሊወያይና ተማሪው በመስክ አገልግሎት ለመሳተፍ የሚፈልግ ከሆነ ሁለት ሽማግሌዎች አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት የተባለው መጽሐፍ በገጽ 98 እና 99 ላይ ያለውን ትምህርት ከእሱ ጋር ሊከልሱ ይችላሉ። ይህም ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ለመሆን የሚበቁት በዚህ ዘመቻ የተሟላ ተሳትፎ ለማድረግ እንዲችሉ በተቻለ ፍጥነት መደረግ አለበት። ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ለመሆን ያልበቁት የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችም ቢሆኑ ይህን ወቅታዊ ትራክት ለሚያውቋቸው ሰዎች ወይም ለቤተሰቦቻቸው እንዲያበረክቱ ማበረታቻ ሊሰጣቸው ይችላል።— በተጨማሪም መጠበቂያ ግንብ 22–109 ገጽ 16, 17 አንቀጽ 8 ተመልከት።
4 ይህ ሥራ ከባድ አይደለም፤ ማንኛውም ሰው በዚህ ሥራ ሊሳተፍ ይችላል። ወላጆች የሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታቸው ክፍል በማድረግ ሁሉም የቤተሰቡ አባል ይህን የመንግሥት ምሥራች ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አግልግሎት ለማበርከት በደንብ የተዘጋጀ እንዲሆን የመለማመጃ ፕሮግራሞችን ሊያክሉ ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ ቀላል አቀራረብ የተሻለ ውጤት ያስገኛል። አጭር መግቢያ ከተጠቀምክ በኋላ ለምታነጋግረው ሰው የመንግሥት ምሥራች አበርክትለትና እንዲያነበው አበረታታው። ሰውዬው ፍላጎት እንዳለው ካሳየ የሰውዬውን ፍላጎት ለመኮትኮት ተመልሰህ ለመሄድ እንድትችል ማስታወሻ ያዝ። (1 ቆሮ. 3:6, 7) የተሳካ ውጤት ለማግኘት ቁልፉ ቀላል የሆነና ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት አቀራረብ መጠቀም ነው።
5 በሚያዝያና በግንቦት ወራት ‘ብዙ የሚሠራ ሥራ’ ይኖረናል። በሚቀጥለው ወር የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ላይ “የጌታ ሥራ የሚበዛላችሁ ሁኑ” የሚል ርዕስ ባለው የመጽሔቱ አባሪ ላይ ተጨማሪ ትምህርት ይቀርባል።— 1 ቆሮ. 15:58