የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/97 ገጽ 8
  • የመንግሥት ዜና ቁ. 35ን በስፋት አሰራጩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመንግሥት ዜና ቁ. 35ን በስፋት አሰራጩ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “አዲሱ ሺህ ዓመት—የወደፊቱ ጊዜ ምን ተስፋ ይዞልሃል?”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ከጥቅምት 16 እስከ ኅዳር 12 የሚደረግ ልዩ ዘመቻ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • “የጌታ ሥራ የሚበዛላችሁ ሁኑ”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • በሚያዝያ ወር ‘መልካም ሥራዎችን ለመሥራት ቀናተኞች’ ሁኑ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 10/97 ገጽ 8

የመንግሥት ዜና ቁ. 35⁠ን በስፋት አሰራጩ

1 በጥቅምትና በኅዳር ወር ሁላችንም ብዙ የምናከናውነው ሥራ ይኖረናል። በጥቅምት ወር በመጀመሪያዎቹ 11 ቀኖች የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ነጠላ ቅጂዎችን እናበረክታለን። ከዚህ በኋላ ከእሁድ ጥቅምት 12 ጀምሮ እስከ እሁድ ኅዳር 16 ድረስ በዓለም አቀፉ የመንግሥት ዜና ቁ. 35 ስርጭት ላይ ተሳትፎ እናደርጋለን። በአካባቢያችን ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ አንድ አስፈላጊ የሆነ መልእክት የማዳረስ ልዩ መብት አለን። መልእክቱ “ሰዎች ሁሉ እርስ በእርሳቸው የሚዋደዱበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?” ለሚለው ጥያቄ መልስ ይዟል። በዚህ ልዩ በሆነ የዘመቻ ወቅት በሥራ ቀኖች የመንግሥት ዜና ቁ. 35⁠ን እናሰራጫለን። ቅዳሜና እሑድ የመንግሥት ዜና ከማሰራጨታችን በተጨማሪ አዲስ የወጡ መጽሔቶችን እናበረክታለን።

2 ማን ተሳትፎ ሊያደርግ ይችላል? እንደተለመደው ሽማግሌዎች በሥራው ግንባር ቀደም ይሆናሉ። እያንዳንዱ ሰው የመንግሥት ዜና በማሰራጨት እንደሚደሰትና በአንዱ ወይም በሁለቱም የዘመቻ ወሮች ወቅት ብዙ አስፋፊዎች ረዳት አቅኚ ሆነው እንደሚመዘገቡ ምንም ጥርጥር የለውም። ሌሎች አስፋፊዎች ደግሞ በአገልግሎቱ ከወትሮው የበለጠ ሰዓት ለማሳለፍ መፈለጋቸው አይቀርም።

3 እውቀት በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት ጥናቱን ያገባደደና በቅርቡ በመስክ አገልግሎት ለመካፈል ብቁ ሊሆን የሚችል የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ አለህ? የመንግሥት ዜና በማሰራጨቱ ዘመቻ መሳተፍ እንዲችል ዘመቻው ከመጀመሩ በፊት ያልተጠመቀ አስፋፊ ለመሆን ይችል ይሆናል። ትራክቱን ለማስተዋወቅ የሚያስፈልገው ቀላል አቀራረብ ብቻ ነው። ለምሳሌ ያህል አንድ ሰው እንዲህ ለማለት ይችላል:- “ይህ መልእክት እጅግ አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ በዚህ ወር በ169 ቋንቋዎች በዓለም ዙሪያ እየተሰራጨ ነው። እርስዎም የግል ቅጂዎች ቢወስዱ ደስ ይለኛል።” ትንንሽ ልጆችም እንኳ ሳይቀር በዚህ አስደሳች ሥራ ጥሩ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይችላሉ።

4 የመጽሐፍ ጥናት መሪዎች እያንዳንዱ የቡድኑ አባል የመንግሥት ዜና ቁ. 35⁠ን በማሰራጨት ረገድ ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርግ ማበረታታት ይኖርባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ አስፈላጊውን ማበረታቻ ካገኙ እንደገና በአገልግሎቱ ንቁ ተሳትፎ ሊያደርጉ የሚችሉ አገልግሎት አቁመው የነበሩ አስፋፊዎች ይኖሩ ይሆናል። ተሞክሮ ካላቸው አስፋፊዎች ጋር አብረው በመሆን በዚህ ዘመቻ መሳተፍ እንዲችሉ ለመርዳት ምን ማድረግ እንደሚቻል ለማወቅ ከዘመቻው ቀደም ብለው ሽማግሌዎች በግለሰብ ደረጃ መጎብኘት ይኖርባቸዋል።

5 የአገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎቹ መቼ ቢደረጉ ይሻላል? ይህ ሁሉ እንቅስቃሴ በቡድን ለመመስከር የሚያስችል ምቹና ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ዝግጅት ማድረግ ይጠይቃል። ለምሳሌ ያህል አራት አስፋፊዎች በቡድን ሆነው በአንድ ክልል ውስጥ አብረው እንዲሠሩ ሊመደቡ ይችላሉ። ይህንንም ሲያደርጉ ማስተዋል መጠቀም አለባቸው። በሁለት ጥንድ በመቀናጀት በክልሉ የተለያየ ክፍሎች ሊያገለግሉ ይችላሉ። በዚህ መንገድ አጭር በሆነ ጊዜ ውስጥ ብዙ ክልሎች ሊሸፈኑ ይችላሉ። በተቻለ መጠን በሳምንቱ ውስጥ በእያንዳንዱ የሥራ ቀን፣ ቅዳሜና እሑድ እንዲሁም ምሽት ላይ የመስክ አገልግሎት ስብሰባዎች መዘጋጀት አለባቸው። ስብሰባዎቹ መደረግ ያለባቸው አስፋፊዎችና አቅኚዎች ለአገልግሎት የወጡበትን ሰዓት ሙሉ በሙሉ መጠቀም በሚችሉባቸው ጊዜያት መሆን አለባቸው። ተማሪዎች፣ የፈረቃ ሠራተኞችና ሌሎችም እንዲጠቀሙ አመሻሹ ላይ የስምሪት ስብሰባ እንዲኖር ዝግጅት ማድረግ ይቻል ይሆናል። እያንዳንዱ አስፋፊ በዚህ ዘመቻ የተሟላ ተሳትፎ ለማድረግ እንዲችል ከቤት ወደ ቤትም ሆነ በንግድ አካባቢ ለማገልገል የሚያስችል በቂ ክልል መኖሩን የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ማረጋገጥ አለበት።

6 ቤታቸው ካልተገኙ ምን ማድረግ እንችላለን? የመንግሥት ዜና ቁ. 35⁠ን ማንበብ ያለባቸው ለምን እንደሆነ ለማብራራት የቤቱን ባለቤቶች በግንባር ቀርበን ማነጋገር እንፈልጋለን። ስለዚህ ቤታቸው በሄድክበት ወቅት ማንንም ሰው ካላገኘህ አድራሻውን ጻፍና በሌላ ቀንና ሰዓት ተመልሰህ ሂድ። በዘመቻው የመጨረሻ ሳምንትም ተመልሰህ ሄደህ ልታገኛቸው ሞክረህ ካልተሳካልህ በዚያ የሚያልፍ መንገደኛ እንዳያየው አድርገህ የመንግሥት ዜና አንድ ቅጂ በሩ ላይ ትተህ መሄድ ትችላለህ። በመኖሪያ አካባቢዎች በመንገድ ላይ በእግራቸው ለሚሄዱ ሰዎች የመንግሥት ዜና ለማበርከት ንቁ ሁን። ሆኖም ሁሉም አስፋፊዎች ወደ ክልላቸው በሚሄዱበት ጊዜ በአንድ ጎዳና ላይ በእግር ለሚጓዙ ሰዎች ትራክቱን ለማበርከት ቢሞክሩ የሚኖረውን ድግግሞሽ ማስተዋል ትችላለህ? ከዚህ ይልቅ ቶሎ ክልልህ ውስጥ ገብተህ ለተለያዩ ብዙ ሰዎች ትራክቱን ለመስጠት መሞከር የተሻለ አይሆንምን? እንዲህ ማድረግህ ክልልህ ውስጥ ብዙ ሰዓት እንድታሳልፍና ብዙ ቤቶች እንድትሸፍን ያስችልሃል። የገጠር ክልሎች በሚሸፈኑበት ጊዜ ወይም ደግሞ መሸፈን ያለበት ሌላ ክልል በሚኖርበት ወቅት ቤታቸው ላላገኘናቸው ሰዎች በዚያው መጀመሪያ በሄድንበት ጊዜ አንድ ቅጂ የመንግሥት ዜና ልንተውላቸው እንችላለን።

7 ዓላማችን ምንድን ነው? በኅዳር 16 ዘመቻው ከማብቃቱ በፊት ጉባኤዎች የደረሳቸውን የመንግሥት ዜና ባጠቃላይ በማሰራጨት ክልላቸውን በሙሉ ለመሸፈን መጣር አለባቸው። የተሰጠህ የጉባኤው የአገልግሎት ክልል በጣም ሰፊ ከሆነና የአገልግሎት ጓደኛ ሳይኖርህ ብትሠራ የማያሰጋ ከሆነ እንዲህ ማድረጉን የተሻለ ሆኖ ታገኘው ይሆናል። ይህም በተቻለህ መጠን ምሥራቹን ለሚገባቸው ብዙ ሰዎች ለማዳረስ ያስችልሃል። (ማቴ. 10: 11) የአገልግሎት ቦርሳ ከመያዝ ይልቅ በእጅህ ጥቂት ትራክቶች ይዘህ መጽሐፍ ቅዱስህን ደግሞ ኪስህ ወይም በትንሽ ቦርሳ መያዝ የተሻለ ሊሆን ይችላል። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ስታገኝ ጥሩ ማስታወሻ መያዝህን አረጋግጥ።

8 በዘመቻው ለመሳተፍ ተዘጋጅተሃልን? ጉባኤው ምን ያህል ተጨማሪ መጽሔቶች እንደሚያስፈልገው ሽማግሌዎች አስቀድመው መወሰንና በዚያ መሠረት ትእዛዝ መላክ ይኖርባቸዋል። ለእያንዳንዱ ጉባኤ አስቀድሞ የተመደበ የመንግሥት ዜና ቁ. 35 ስለሚላክ ማዘዝ አያስፈልግም። ልዩ፣ የዘወትርና ረዳት አቅኚዎች እያንዳንዳቸው የሚያሰራጩት 250 ቅጂዎች ሲኖራቸው የጉባኤ አስፋፊዎች ደግሞ እያንዳንዳቸው 50 ቅጂዎች ተመድቦላቸዋል። ለእያንዳንዳችን የሚሆን የሥራ ድርሻ ተመድቧል። በዚህ አስደሳች በሆነ ሥራ ለመሳተፍ ጓጉተሃል? እንደጓጓህ ምንም አያጠራጥርም። የመንግሥት ዜና ቁ. 35 የያዘውን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ጠቃሚ መልእክት አቅማችን በፈቀደ መጠን በሰፊው እንዲሰራጭ እናድርግ!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ