የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/95 ገጽ 8
  • ፈልገህ አግኝ (ከገጽ 8 የዞረ )

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፈልገህ አግኝ (ከገጽ 8 የዞረ )
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዓላማ ያላቸው ተመላልሶ መጠየቆች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ውጤታማ ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ ቀደም ሲል ያሳዩትን ፍላጎት ገንባ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • አቀላልና ውጤታማ ተመላልሶ መጠየቆችን ማድረግ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ደፋሮች ሁኑ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 4/95 ገጽ 8

ለመማር ፈቃደኛ የሆኑትን ፈልገህ አግኝ

1 “የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም።” (ዮሐ. 6:44) ልብን የሚመረምረው ይሖዋ ለመማር ፈቃደኛ የሆኑትንና በተማሩት መሠረት የሚመላለሱትን ሰዎች ይባርካቸዋል። እነዚህ ልበ ቅን የሆኑ ሰዎች ናቸው እንጂ ለመማር ፈቃደኞች የሆኑትን ለማግኘት የምናደርገውን ሰላማዊ ፍለጋ ለማወክ ቆርጠው የተነሱ አክራሪዎች አይደሉም። (ኤር. 17:10፤ ዮሐ. 6:45) አዲስ ዓለም የሚናፍቁትን ገሮች ለማግኘት በሚደረገው ፍለጋ ከአምላክ ጋር አብሮ የመሥራት መብት አግኝተናል።— መዝ. 37:11፤ 1 ቆሮ. 3:9

2 የቤቱ ባለቤት:- “በሥላሴ ታምናላችሁ?” ብሎ ቢጠይቅ ለመማር ፈቃደኛ ለሆነ ሰው እንዲህ ብለህ ልትመልስ ትችላለህ:-

◼ “በአገራችን ያሉ አብዛኞቹ ሰዎች በሥላሴ ያምናሉ። ዛሬ እንኳን የመጣሁት ስለ ሥላሴ ለመወያየት አልነበረም ጥያቄውን ካነሱ ግን በተረጋጋና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ መወያየት የምንችል ይመስልዎታል? (መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት፤ የቤቱ ባለቤት በዚህ ርዕስ ላይ አላስፈላጊ ጭቅጭቅ የሚያስነሳ ከሆነ ሐሳብህን ለመቀጠል አትሞክር። ከዚህ ይልቅ መልካሙን ሁሉ እንደምትመኝለትና ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥ ሆኖ ስለሚያስተዳድራት ምድራዊ ገነት አንድ ቀን ለመወያየት እንደምትችል ገልጸህ መደምደሙ የተሻለ ይሆናል። ሥላሴ የተባለውን ብሮሹር ልታበረክት ተችላለህ።) ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱና ቅዱሳን ሐዋርያቱ ስለ ሥላሴ በፍጹም እንዳልተናገሩ ያውቃሉ? ስለዚህ እኛ የምናምነው እነሱ ያምኑ የነበረውን ነው።”

3 አንዳንድ የቤት ባለቤቶች:- “እኛ አንድ ጊዜ ድነዳል (ወይም የራሳችን ቤተ ክርስቲያን አለን) ወደ እኛ ለምን ትመጣላችሁ?” ይላሉ

◼ ለመማር ፈቃደኛ የሆነ ሰው ከሆነ እንዲህ ብለን ብናነጋግረው ጥሩ ሊሆን ይችላል:- “አሳቢነትዎን እናደንቃለን። በዚህ ጉዳይ ላይ ግን ኢየሱስ ራሱ እኛ አሁን ሰዎችን ሄደን እንደምናነጋግረው ዓይነት ሥራ ይሠራ እንደነበርና ተከታዮቹም ይህንኑ እንዲያደርጉ አዟቸው እንደ ነበር አንደሚያውቁ ምንም አልጠራጠርም። የኢየሱስ ስብከት ዋነኛ ርዕስ ምን እንደነበር ያውቃሉ? (ትንሽ ቆም በል) ዛሬ ወደዚህ የመጣነው ለዚህ ነው። (ሉቃስ 8:1፤ ዳን. 2:44)”

◼ ሌላው አቀራረብ እንዲህ ሊሆን ይችላል:- “እንግዲያው ኢየሱስ በማቴዎስ 24:12–14 ላይ ከተናገረው ቃላት ጋር እንደሚስማሙ ጥርጥር የለውም። ከአምላክ ጋር የቀረበ ዝምድና ያለው ሰው እንኳ በዚህ ዓመፀኛ ዓለም ውስጥ መጽናት አለበት። እንዲያውም እነዚህ የኢየሱስ ቃላት የሚፈጸሙት በእኛ ዘመን እንደሆነ ያውቃሉ? (ወይም:- የአምላክን መንግሥት አስመልክቶ የምናከናውነው ይህ የስብከት ሥራ አስቀድሞ ክርስቶስ የተናገረለት እንደሆነ ያውቃሉን?)”

4 የአንዳንዶች የተለመደ መልስ ደግሞ “ቄሶቻችን ያስተምሩናል” የሚል ነው። በደግነት ለምንሰጣቸው መልስ የሚሰጡት ምላሽ ለመማር ፈቃደኛ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ያሳያል።

◼ መልስህ እንዲህ ሊሆን ይችላል:- “እኛ ያልንዎትን በተሳሳተ መንገድ እንዳልተረዱ ተስፋ እናደርጋለን። እየጠየቅንዎት ያለነው የራሳችንን ትምህርት እንዲያዳምጡን አይደለም። ልናነብልዎት የፈለግነው በምድር ላይ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ የሚበልጠው ታላቁ አስተማሪ ኢየሱስ ራሱ ከተናገራቸው አንዳንድ ቃላት ነው። (ከዚያም ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተናገረውን አንድ ተስማሚ ሐሳብ ካነበብክ በኋላ ወደ ጀመርከው ርዕስ ሂድ።)”

5 አንዳንድ ሰዎች ደግሞ በፍጹም ቅንነት ቶሎ ብለው በመስቀል እንደምናምንና እንደማናምን ይጠይቁናል

◼ መማር ለሚፈልግ ሰው እንዲህ ልትለው ትችላለህ:- “ብዙ ሰዎች መስቀል ማለት የጌታችን ፈልገህ አግኝ (ከ 8 የዞረ) ለኢየሱስ መሥዋዕታዊ ሞት ማስታወሻ እንደሆነ አድርገው እንደሚያምኑ ተረድተናል። መሥዋዕት መሆኑ በሰማይ ንጉሣችን እንዲሆን መንገድ እነደከፈተለት ያውቃሉ? (ከዚያም ስለ መንግሥቲቱ ወይም መንግሥቲቱ ስለምታመጣቸው በረከቶች ንገረው።)”

6 የመንግሥት ዜናን የማበርከቱ ዘመቻ ከተጀመረ በኋላ ለመማር ፈቃደኛ ለሆኑ ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ በምታደርጉበት ጊዜ የመንግሥት ዜና ላልደረሳቸው ሰዎች አንድ ቅጂ ትታችሁ መሄዳችሁን አትርሱ። የመንግሥት ዜናን ካበረከታችሁ በኋላ ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ ምን ማለት እንደምትችሉ በግንቦት የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ይብራራል።

7 የአምላክ ቃል ‘ኃይል’ ስላለው መልእክታችንን ስናቀርብ ልንጠቀምበት ይገባል። ለመማር ፈቃደኛ የሆኑትን ልብ ይነካል (ዕብ. 4:12) ሰውዬው ራሱ መጽሐፍ ቅዱሱን እንዲያነብ ጋብዘው። (ከሥራ 17:11 ጋር አወዳድር።) እኛ የበኩላችንን ከተወጣን ይሖዋ ደግሞ ጥረታችንን ይባርካል።

[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል8]

(ወደ ገጽ 2 ይዞራል)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ