የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/95 ገጽ 1
  • ክርስቶስ ለወጣቶች ምሳሌ ነው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ክርስቶስ ለወጣቶች ምሳሌ ነው
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ራስህን በፈቃደኝነት ልታቀርብ ትችላለህ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ከሁሉ የተሻለ የሥራ መስክ ይሆንልህ ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • አቅኚ ሆነህ ይሖዋን ልታገለግለው ትችላለህን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • አቅኚዎች በረከትን ይሰጣሉ፤ መልሰውም በረከት ያገኛሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 6/95 ገጽ 1

ክርስቶስ ለወጣቶች ምሳሌ ነው

1 ረዥም ጊዜ ከፈጀ የመጽሐፍ ቅዱስ ውይይት በኋላ አንድ ወጣት እንዲህ በማለት ገልጾ ነበር:- “ኃይለኛ ግፊት በሚያሳድረው የኢየሱስ ክርስቶስ ባሕርይ ተነክቻለሁ። በእንዲህ ዓይነቱ መሪ ላይ እምነት ልጥል እችላለሁ።” ለፖለቲካ ሰዎች ወይም ለዝነኛ ስፖርተኞች ወይም ተዋንያን እንዲህ ሊባል አይቻልም። እውነተኛ ክርስቲያኖች ዓለማዊ የአቋም ደረጃዎችንና ክርስቲያናዊ ያልሆኑ የአኗኗር ዘይቤዎችን በግልጽ የሚደግፉ ሰዎችን ምሳሌ አድርገው አይመለከቱም።— መዝ. 146:3, 4

2 ወጣቶች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት ሲያሳዩ ራሳቸውን የአምላክ በግ አድርገው ማቅረባቸው እንደሆነና ኢየሱስ እንዳወቃቸው እርግጠኛ መሆን ይችላሉ። መልካሙ እረኛ ይንከባከባቸዋል። (ዮሐ. 10:14, 15, 27) ኢየሱስን እንደ ምሳሌያቸው አድርገው የሚከተሉ ወጣቶች የተባረኩ ናቸው።

3 በአሁኑ ጊዜ ብሩክሊን በሚገኘው ቤቴል የሚያገለግል አንድ ወንድም የስምንት ዓመት ልጅ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ ይህንን የአገልግሎት መብት ግቡ አድርጎ ነበር። የቤቴል አገልግሎት ትልቅ ሰው ሲሆን የክርስቶስን ምሳሌ የሚከተልበት ተግባራዊ መንገድ እንደሆነ አድርጎ እንዲመለከተው ማበረታቻ ተሰጥቶት ነበር። ወላጆቹና ተጓዥ የበላይ ተመልካቾች ይህንን ግብ ከፊቱ አስቀምጠውለት ነበር። ራሱን ከወዲሁ ለማዘጋጀት እንዲረዳው ቤት ውስጥ የዕለት ተዕለት ሥራዎችን በማከናወን፣ የመንግሥት አዳራሹን ለመጠገን በሚደረገው እንቅስቃሴ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያበረክትና የአገልግሎት ችሎታውን በማዳበር ልክ እንደ አንድ የቤቴል ቤተሰብ አባል በትጋት እንዲሠራ አበረታተውት ነበር። አሁን ከአያሌ ዓመታት የቤቴል አገልግሎት በኋላ በልጅነቱ የክርስቶስን ምሳሌ ለመከተል ባደረገው ጥረት ይደሰታል።

4 የሙሉ ጊዜ የመስክ አገልግሎትም መልሶ ሊክሰን ይችላል። ኢየሱስ ዓለማዊ ሥራ ከማሳደድ ይልቅ አገልግሎቱን መርጧል። አንዲት ወጣት እህት ከትምህርት ቤት በተመረቀች ጊዜ አቅኚ ለመሆን ፈልጋ የነበረ ቢሆንም አመቺ የሆነ የግማሽ ቀን ሥራ ማግኘት ስላልቻለች አቅኚነትን ለመጀመር አመነታች። ‘መጀመሪያ ሥራ ካገኘሁ በኋላ የአቅኚነትን ማመልከቻ አስገባለሁ’ እያለች ታስብ ነበር። አቅኚ እንዳትሆን ያገዳት ምንም ነገር ሳይኖር አቅኚ ሳትሆን ለረጅም ጊዜ ከቆየች የሙሉ ቀን ሥራ የተሻለ ሆኖ ሊታያት እንደሚችል አንድ ሽማግሌ አስገነዘባት። “መንፈሱ እንዲመራኝ ወደ ይሖዋ ጸለይኩ” በማለት ገልጻለች። ወዲያውኑ ረዳት አቅኚ ሆነች በኋላም የዘወትር አቅኚ ሆነች። ብዙም ሳይቆይ ከአቅኚነት ፕሮግራሟ ጋር የሚሄድ ከሁሉ የተሻለ ተስማሚ ሥራ አገኘች።

5 ኢየሱስ ለእያንዳንዱ ሰው የመንግሥቱን መልእክት በድፍረት አውጆአል። (ማቴ. 4:23) ወጣት ክርስቲያኖችም ሌሎችን ከመፍራት ይልቅ በስብከታቸው ደፋር መሆንን ከዚህ ሊማሩ ይችላሉ። አንድ የ14 ዓመት የይሖዋ ምሥክር እንዲህ በማለት ሪፖርት አድርጓል:- “በምማርበት ትምህርት ቤት ውስጥ ያሉት ሁሉ ስለ ክርስቲያናዊ አቋሜ ያውቃሉ . . . እንደምሰብክ ስለሚያውቁ አገልግሎት ላይ ሳለሁ ከአንድ የክፍል ጓደኛዬ ጋር ብገናኝ እፍረት አይሰማኝም። ጓደኞቼ በአብዛኛው ለምሥራቹ ጆሮአቸውን ይከፍታሉ፤ ብዙውን ጊዜም ጽሑፎች ይወስዳሉ።”

6 የክርስቶስን ምሳሌ መመርመሩ ወጣቶች የወደፊት ሕይወታቸውን በተመለከተ ጥበብ ያለበት ውሳኔ እንዲያደርጉ ሊረዳቸው ይችላል። ዓለማዊ ነገሮችን በማሳደድ ከመጠመድ ይልቅ በይሖዋ አገልግሎት በቅንዓት በመካፈል ‘ታላቁን ፈጣሪያቸውን ያስባሉ።’ (መክ. 12:1) ልክ እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ዓለም ከሚያቀርብልን ማንኛውም ነገር ይበልጥ ተፈላጊ በረከቶች የሚያስገኘውን “የአባት ፍቅር” ይኮተኩታሉ። ከአሮጌው ዓለም ጋር አብረው ‘ከማለፍ’ ይልቅ ‘የዘላለም ሕይወትን’ ተስፋ ማድረግ ይችላሉ።— 1 ዮሐ. 2:15–17

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ