የሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ተመላልሶ መጠየቅ አድርጉ
1 አምላክ ‘ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና ትክክለኛውን የእውነት እውቀት እንዲያውቁ’ ይፈልጋል። (1 ጢሞ. 2:4) ሰዎችን እንዲድኑ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው? እውነትን የማስተማር ዓላማ ይዘህ ተመላልሶ መጠይቅ አድርግ። ተመልሰህ ስትሄድ ምን ብለህ ትናገራለህ? ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ሐሳቦች ሊረዱህ ይችላሉ።
2 በቀጥታ ጥናት ለማስጀመር ሞክረህ ጥሩ ምላሽ አግኝተህ ከነበረ ተመልሰህ ስትሄድ እንዲህ ማለት ትችላለህ:-
◼ “ባለፈው ጊዜ በተነጋገርንበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት የሚጠቅምባቸውን ምክንያቶች ተወያይተን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ከልብ ጥረት ማድረጋችን አምላክ ለወደፊቱ ምን እንዳዘጋጀልን እንድናስተውል ይረዳናል። [ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።] በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች አምላክ ምን ተስፋዎች እንደሰጠና እርሱን ማስደሰት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ማወቅ እንዲችሉ የረዳቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራም አለን።” እውቀት ወይም ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ አሳይተህ የምዕራፎቹን ርዕሶች ባጭሩ ካብራራህ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ የምናስጠናው እንዴት እንደሆነ ግለጽለት።
3 “የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው” የተባለውን መጽሐፍ ላበረከትክለት ሰው በሚከተለው መንገድ ተመላልሶ መጠየቅ ልታደርግለት ትችላለህ:-
◼ “በመጀመሪያ በመጣሁ ወቅት ለቤተሰብዎ የሚያሳዩትን አሳቢነት ስመለከት በጣም አድንቄአለሁ። በአሁኑ ጊዜ የምንኖረው በዚህ ክፉ ሥርዓት የመጨረሻ ቀኖች ውስጥ ስለሆነ ቤተሰቦች የወደፊቱን ጊዜ ተዘጋጅተው መጠበቃቸው በጣም አስፈላጊ ነው። ባለፈው ጊዜ ሰጥቼዎት የነበረው የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው የተባለው መጽሐፍ ቤተሰባችንን ለወደፊቱ ጊዜ ለማዘጋጀት ከፈለግን በቤት ውስጥ ቋሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ውይይት እንድናደርግ አጥብቆ ይመክረናል። [ገጽ 185-6 አንቀጽ 10 አንብብ።] ጥቂት ደቂቃዎች ወስጄ 200 በሚያክሉ አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በቤተሰብ መልክ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እንደሚያጠኑ ባሳይዎ ደስ ይለኛል።” ጊዜ በፈቀደልህ መጠን እንዴት እንደሚጠና ለማሳየት በገጽ 71 ላይ በሚገኘው ንዑስ ርዕስ ሥር ባለው ሐሳብ ተጠቀም።
4 ተመላልሶ መጠየቅ የምናደርገው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር እንደሆነ አትርሳ። በተለይ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለው አዲሱ መጽሐፍና ለዘላለም መኖር የተባለው መጽሐፍ ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ ለማስጠናት ታስበው የተዘጋጁ ናቸው። የቆዩ መጻሕፍት ላበረከትንላቸው ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ አድርገን ጥናት ስናስጀምር በእነዚህ አዳዲስ መጻሕፍት ትኩረት ማድረጋችን በጣም ጠቃሚ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን የሚያጠኑ ሰዎች ለመዳን የይሖዋን ስም መጥራት የሚችሉበትን መንገድ ሲያውቁ ከፍተኛ ደስታ እናገኛለን።— ሥራ 2:21