የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/99 ገጽ 1
  • “ታገሡ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ታገሡ”
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በአገልግሎታችን ትዕግሥተኛ መሆን ይገባናል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • ትዕግሥት ማሳየታችሁን ቀጥሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ይሖዋና ኢየሱስ ካሳዩት ትዕግሥት ትምህርት ማግኘት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • መታገስ ትችላለህን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 1/99 ገጽ 1

“ታገሡ”

1 የሰይጣን አሮጌ ሥርዓት ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ወደ ፍጻሜው እየቀረበ መምጣቱን ስናይ የይሖዋን የማዳን ቀን በመጠባበቅ ‘መታገሣችን’ የግድ አስፈላጊ ነው። በተለይ ሥርዓቱ ወደ ማብቂያው በተቃረበበት በአሁኑ ጊዜ ክፉ የጠላት ኃይሎች የይሖዋን ሉዓላዊነት ከሚመለከተው አንገብጋቢ ጉዳይ ትኩረታችንን ለመስረቅ ቆርጠው የተነሱ ከመሆናቸውም በላይ ስፍር ቁጥር በሌላቸው የግል ጉዳዮቻችን አቅጣጫችንን ለማስለወጥ ይሞክራሉ። በዚህ መንገድ ሰይጣን በመንግሥቱ የስብከት ሥራ የምናደርገውን ተሳትፎ እንድናቆም ወይም እንድንቀንስ በማድረግ ያሞኘናል። (ያዕ. 5:7, 8፤ ማቴ. 24:13, 14) ተፈላጊውን ትዕግሥት ማሳየት የምንችለው በምን መንገዶች ነው?

2 ቻይ በመሆን፦ በአገልግሎታችን ግዴለሽነት ወይም ተቃውሞ ሲያጋጥመን ችለን ማሳለፋችን በስብከት እንድንጸና ይረዳናል። የምናገኛቸው ሰዎች ያልጠበቅነውን ምላሽ ቢሰጡን ወይም ክፉ ሆነው ብናገኛቸው በቀላሉ የምንደናገጥ ወይም የምንናደድ አንሆንም። (1 ጴጥ. 2:23) ይህ ውስጣዊ ጥንካሬ ለሥራችን ግዴለሽነት ወይም ጥላቻ ስለሚያሳዩት በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ ስላሉ ሰዎች አፍራሽ ነገር ከመናገር ሊገታን ይችላል። እንዲህ የምናደርገው ይህ ዓይነቱ ወሬ እኛንም ሆነ ከኛ ጋር በአገልግሎት የሚካፈሉትን ተስፋ እንደሚያስቆርጥ ስለምንገነዘብ ነው።

3 በትዕግሥት መጽናት፦ በአገልግሎታችን ፍላጎት ያለው ሰው አግኝተን ጥሩ ውይይት ካደረግን በኋላ ተመልሰን ቤቱ ስንሄድ ሰውየውን ማጣታችን ትዕግሥታችንን ሊፈታተን ይችላል። በተመሳሳይ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ የምናስጠናቸው ሰዎች እድገት ለማድረግ ወይም ከእውነት ጎን ለመቆም የሚያዘግሙ ከሆኑ ትዕግሥታችን ይፈተናል። ሆኖም በትዕግሥት መጽናት አብዛኛውን ጊዜ ጥሩ ውጤት ያስገኛል። (ገላ. 6:9) አንዲት እህት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከማስጀመሯ በፊት ለአንዲት ወጣት በተደጋጋሚ ተመላልሶ መጠየቅ አደረገችላት። በመጀመሪያዎቹ አምስት ተመላልሶ መጠየቆች ወቅት ወጣቷ በሌሎች ሥራዎች ተጠምዳ ነበር። እህት ለስድስተኛ ጊዜ ስትሞክር በከባድ ዝናብ እየተደበደበች ብትሄድም ቤት ውስጥ ሰው አልነበረም። የሆነ ሆኖ እህት ለወጣቷ አንድ የመጨረሻ እድል ለመስጠት ወስና በድጋሚ ስትሄድ ለማጥናት ዝግጁ ሆና አገኘቻት። ከዚያ በኋላ ተማሪዋ ቀጣይ እድገት በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሕይወቷን ለይሖዋ ወሰነች።

4 የይሖዋ ቀን እንደማይዘገይ እናውቃለን። በመሆኑም መለኮታዊ ትዕግሥት ጥሩ ፍሬ እንደሚያስገኝ በመገንዘብ ይሖዋ የሚያደርገውን እንጠባበቃለን። (ዕን. 2:3፤ 2 ጴጥ. 3:9–15) እንደ ይሖዋ ትዕግሥት ማሳየትና በአገልግሎት መጽናት አለብን። ትጋት ለተሞላበት ሥራችሁ ብድራት እንዲከፍላችሁ ይሖዋን “በእምነትና በትዕግሥት” ተጠባበቁ።—ዕብ. 6:10–12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ