የሚበዙትን የሚያነሳሳ ቅንዓት
በቆሮንቶስ የሚገኙት ክርስቲያኖች መልካም ሥራ ለመሥራት ያላቸው ቅንዓት ‘የሚበዙትን አነሳስቶ’ ስለነበር ሐዋርያው ጳውሎስ አመስግኗቸዋል። (2 ቆሮ. 9:2) አብዛኛውን ጊዜ አንድ ግለሰብ፣ አንድ ቤተሰብ፣ አንድ የመጽሐፍ ጥናት ቡድን ወይም ጠቅላላው ጉባኤ በወንጌላዊነቱ ሥራ በቅንዓት በመካፈል ተመሳሳይ ውጤት ሊያገኝ ይችላል። በአገልግሎቱ ቅንዓት እንድታሳዩ ሊረዷችሁ የሚችሉ አንዳንድ ነጥቦች ከዚህ በታች ቀርበዋል።
◼ ቅዳሜ ቅዳሜ የመጽሔት ቀን እንቅስቃሴ ለማድረግ ጊዜ መድቡ።
◼ እሁድ በመስክ አገልግሎት ተካፈ
this is part of last word on previous lineፈሉ።
◼ ልዩ ምሥክርነት ለመስጠት ዝግጅት በተደረገባቸው ቀናት በአገልግሎት ተካፈሉ።
◼ ሥራ ወይም ትምህርት የማይኖርባቸውን የበዓል ቀናት ለአገልግሎት ተጠቀሙባቸው።
◼ የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉባኤውን በሚጎበኝበት ሳምንት የሚደረገውን የመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴ ደግፉ።
◼ በዓመት ውስጥ ለአንድ ወይም ከዚያ ለሚበልጡ ወራት በረዳት አቅኚነት አገልግሎት ተካፈሉ።
◼ ከተቻለም ሁኔታዎቻችሁን አስተካክላችሁ የዘወትር አቅኚ ሁኑ።
የ2000 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ከገጽ 17-19 ተመልከቱ።