የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/97 ገጽ 3-5
  • 1,000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 1,000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 11 በተግባር እንደታየው በጉባኤ ውስጥ ብዙዎቹ ረዳት አቅኚ ሆነው ሲያገለግሉ የአገልግሎት ክልሎች ተጣርተው ይሸፈናሉ። ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ አለን። የአገልግሎት ክልል የሚያድሉ ወንድሞች ተጨማሪ ዕቅድ ለማውጣት ደስተኞች እንደሚሆኑና ብዙ ያልተሠራባቸው አካባቢዎችን ለመሸፈን የረዳት አቅኚዎችን እርዳታ ሊጠይቁ እንደሚችሉ አያጠራጥርም። ምሳ ይዞ ሙሉ ቀን በአገልግሎት ላይ መካፈል በአገልግሎት ክልሉ ውስጥ ራቅ ወዳሉ አካባቢዎች ሄዶ ለመሥራት ያስችላል። እንዲሁም ተጨማሪ የመጽሔት ቀናት ፕሮግራም ለማውጣትና የተከማቹ መጽሔቶችን ለማሰራጨት ጥረት ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል። (ጥቅምት 23, 1996 ለጉባኤዎች በሙሉ የተጻፈውን ደብዳቤ አንቀጽ 5ን እባክህ ተመልከት።)
  • 12 ሽማግሌዎች ቅድመ ዝግጅት ያደርጋሉ:- በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ብዙ አስፋፊዎች በአገልግሎት ላይ መሳተፍ ይችሉ ዘንድ የከሰዓት በኋላውንና አመሻሹን ወቅት ጨምሮ በሳምንቱ ውስጥ በተለያየ ሰዓት የተለያየ ዓይነት የምሥክርነት እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮግራም መውጣት ይኖርበታል። የአገልግሎት እንቅስቃሴው ከቤት ወደ ቤት የሚደረገውን አገልግሎት ጨምሮ የመንገድ ላይ ምሥክርነት፣ በንግድ ቦታዎች የሚሰጠውን ምሥክርነትና እቤታቸው ያልተገኙ ሰዎችን ማነጋገርንም የሚጨምር መሆን ይኖርበታል። ሽማግሌዎች እንዲህ ያለውን ዝግጅት ማድረጋቸው ይበልጥ ተግባራዊና አመቺ በሆነ መንገድ አቅኚዎች ከጉባኤው ጋር ተባብረው እንዲያገለግሉ ያስችላቸዋል። የመስክ አገልግሎትን አስመልክቶ የተደረጉ ዝግጅቶች በሙሉ ለጉባኤው መገለጽ ይኖርባቸዋል። ለአገልግሎት የሚደረጉት ስብሰባዎች በደንብ የተደራጁ መሆን ይገባቸዋል። በተጨማሪም የተሟላ የአገልግሎት ክልል ማዘጋጀትና በቂ መጠን ያላቸው መጽሔቶችና ጽሑፎች በፍጥነት መታዘዝ ይኖርባቸዋል።
  • 13 የግል የአገልግሎት ፕሮግራም አውጡ:- ቀደም ሲል ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል ይፈራ የነበረ አንድ ወንድም “ከጠበኩት በላይ ቀላል ነበር። ጥሩ ፕሮግራም ማውጣት ብቻ ነው የሚጠይቀው” ብሏል። በዚህ አባሪ ጽሑፍ የመጨረሻ ገጽ ላይ ከሰፈሩት የረዳት አቅኚነት ፕሮግራም ናሙና መካከል ለአንተ ይበልጥ ተስማሚ የሆነው የትኛው ነው? በእያንዳንዱ ሳምንት አሥራ አምስት ሰዓት ለአገልግሎት መመደብ ረዳት አቅኚዎች የሚፈለግባቸው የሰዓት ግብ ላይ እንዲደርሱ ያስችላቸዋል።
  • 14 የቤት እመቤቶችና የከሰዓት በኋላ ሽፍት ሠራተኞች ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል የጠዋቱን ጊዜ ለመስክ አገልግሎት ሊመድቡ ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ ተማሪዎችና የሌሊት ሽፍት ሠራተኞች የከሰዓት በኋላውን ጊዜ ለስብከቱ ሥራ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። የሙሉ ቀን ሥራ ያላቸው ደግሞ በምሽት አገልግሎት እየተካፈሉ በሳምንቱ መካከል አንድ ቀን እረፍት ሊወስዱ አለዚያም ቅዳሜና እሑድ ሙሉ ቀን በአገልግሎት መሳተፍ የተሻለ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ። ከቅዳሜና ከእሑድ ሌላ በመስክ አገልግሎት መካፈል የማይችሉ ደግሞ አምስት ቅዳሜና እሑድ ያላቸውን ወሮች ለአገልግሎት ይመርጣሉ። በዚህ ዓመት መጋቢት፣ ነሐሴ ወይም ኅዳር አምስት ቅዳሜና እሑድ ስላላቸው በእነዚህ ወራት ረዳት አቅኚ መሆን ይችላሉ። ገጽ 10 ላይ ለመምሪያነት እንዲያገለግል ባዶ የተተወውን ሰንጠረዥ በመጠቀም በጥንቃቄና በጸሎት አስባችሁበት ለግል ሁኔታችሁ ይበልጥ ተስማሚ የሆነ የግል የአገልግሎት ፕሮግራም ልታወጡ ትችላለህ።
  • 15 የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ዝግጅት ያለው አንዱ ጥቅም እንደ ልብ ሊለዋወጥ የሚችል መሆኑ ነው። አቅኚ ሆናችሁ ልታገለግሉ የምትችሉበትን ወር ራሳችሁ ልትመርጡ ትችላላችሁ። እንዲሁም የፈለጋችሁትን ያህል ወር አቅኚ መሆን ትችላላችሁ። ላልተወሰነ ጊዜ ረዳት አቅኚ ሆናችሁ ማገልገል ፈልጋችሁ ግን ሁኔታችሁ ባይፈቅድላችሁ አልፎ አልፎ ረዳት አቅኚ ሆናችሁ ማገልገል ትችላላችሁ? በሌላው በኩል ደግሞ አንዳንዶች ለተወሰኑ ወራት በተከታታይ ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ችለዋል።
  • 16 ለሙሉ ጊዜ አቅኚነት የሚደረግ ዝግጅት:- የአቅኚነት መንፈስ ያላቸው ብዙ ወንድሞች የዘወትር አቅኚ ሆነው ለማገልገል ይፈልጋሉ። ይሁን እንጂ አቅኚ ለመሆን የሚያስችል ጊዜ፣ አመቺ ሁኔታና ብርታት አይኖረኝ ይሆናል የሚል ስጋት አላቸው። በአሁኑ ጊዜ የዘወትር አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉ አብዛኞቹ አቅኚዎች ወደ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት ከመግባታቸው በፊት ረዳት አቅኚ ሆነው እንዳገለገሉ የተረጋገጠ ነው። አንድ ሰው በረዳት አቅኚነቱ ፕሮግራም ላይ በእያንዳንዱ ቀን አንድ ሰዓት ብቻ እያከለ ቢያገለግል ወይም በእያንዳንዱ ሳምንት አንድ ተጨማሪ ቀን በአገልግሎት ላይ ቢያሳልፍ የዘወትር አቅኚነት የሰዓት ግብ ላይ ሊደርስ ይችላል። ይህ ለአንተ ተስማሚ መሆኑን ለማረጋገጥ ረዳት አቅኚ ሆነህ አንድ ወይም ሁለት ወር 90 ሰዓት ለማገልገል ለምን አትሞክርም? በዚያውም ብዙ ተመላልሶ መጠየቆችና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች የማግኘት አጋጣሚ ይከፈትልሃል፤ ይህም ሚዛኑን የጠበቀ የአቅኚነት አገልግሎት እንድታከናውን ያስችልሃል።
  • 17 አንዲት እህት ሳታቋርጥ ለስድስት ወራት ረዳት አቅኚ ሆና አገልግላለች። በዚህ ጊዜ የዘወትር አቅኚ ሆና የማገልገል ግብ ነበራት። ይህን ዓላማ ይዛ የዘወትር አቅኚዎች የሚያሟሉትን 90 ሰዓት ለመመለስ የሚያስችላት ጊዜ ለማግኘት አራት የተለያዩ ሰብዓዊ ሥራዎችን ሞከረች። በየወሩ አቅኚ መሆን የምትችል መሆኗን ለማረጋገጥ አንድ ወይም ሁለት ፕሮግራም ታወጣ ነበር። በዚህ መንገድ ሁሉን ከሞከረች በኋላ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት መካፈል እንደማትችል ሆኖ ተሰማት። ሆኖም መመሪያ እንዲሰጣት ይሖዋን መጠየቋን አላቋረጠችም። አንድ ቀን ለአገልግሎት ስብሰባ በምትዘጋጅበት ወቅት በመስከረም 1991 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣ:- “በሰዓቱ ግብ ላይ ከመጠን በላይ ከመጨነቅ ይልቅ በመሰብሰቡ ሥራ ላይ ለመሳተፍ በተገኘው ተጨማሪ አጋጣሚ ላይ ለምን አታተኩሩም? (ዮሐ. 4:​35, 36)” የሚል ሐሳብ አነበበች። እንዲህ ትላለች:- “ይህን ዓረፍተ ነገር አምስት ወይም ስድስት ጊዜ አነበብኩት። ከይሖዋ የመጣ መልስ እንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩ። በዚያች ቅጽበት የዘወትር አቅኚ ሆኜ ለማገልገል ወሰንኩ።” ምንም እንኳ ያገኘችው የትርፍ ጊዜ ሥራ ፕሮግራም ለአቅኚነት የማያመች ቢሆንም የዘወትር አቅኚ ለመሆን ማመልከቻ አስገባች። ከአንድ ሳምንት በኋላ የሥራ ፕሮግራሟ ተለወጠ። ለእርሷ ተስማሚ የሆነ የሥራ ሰዓት አገኘች። “ይህ ነገር የይሖዋ እጅ አለበት ወይስ የለበትም?” አለች። ጨምራም “መመሪያ እንዲሰጣችሁ ይሖዋን ጠይቃችሁ መልስ ካገኛችሁ በኋላ ሳታንገራግሩ ተቀበሉት።” የዘወትር አቅኚ ለመሆን ከፍተኛ ምኞት ካለህ ምናልባት በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ረዳት አቅኚ ሆነህ ካገለገልክ በኋላ አንተም በሙሉ ጊዜ አገልግሎት የተሳካልህ መሆን እንደምትችል ልትተማመን ትችላለህ።
  • 18 በእነዚህ ልዩ እንቅስቃሴ በሚደረግባቸው ወራት ይህን የመዳን ምሥራች ለማስፋፋት ሕዝቡ የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚደግፍና ቅንዓታችሁን እንደሚባርክ እርግጠኞች ነን። (ኢሳ. 52:​7፤ ሮሜ 10:​15) በመጋቢት፣ በሚያዝያ ወይም በግንቦት ወራት ረዳት አቅኚ ሆነህ በማገልገል 1, 000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ ለሚለው ጥሪ አዎንታዊ መልስ ትሰጣለህን?
  • ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት ልታወጣው የምትችለው ጠቃሚ ግብ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ዘንድሮም ጥሪውን ትቀበላላችሁን?—ለረዳት አቅኚነት በድጋሚ የቀረበ ጥሪ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • የይሖዋን ግርማ በሰፊው አውጁ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 2/97 ገጽ 3-5

1, 000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ

በመጋቢት፣ በሚያዝያ ወይም በግንቦት ረዳት አቅኚ መሆን ትችላለህን?

1 በሚያዝያ 1881 የታተመው መጠበቂያ ግንብ እትም “1, 000 ሰባኪዎች ይፈለጋሉ” የሚል ርዕስ ይዞ ወጥቶ ነበር። መጽሔቱ ራሳቸውን ለአምላክ የወሰኑና “ከጌታ የእውነትን እውቀት የተቀበሉ” ወንዶችና ሴቶች የሚችሉትን ያህል የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በሰፊው ለማሰራጨት ጊዜያቸውን እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርቦ ነበር። ካላቸው ጊዜ መካከል ግማሹን ወይም ከዚያ የበለጠውን ለጌታ ሥራ ሙሉ በሙሉ ለማዋል የሚችሉ ሁሉ ኮልፖልተር ወንጌላውያን ሆነው በፈቃደኛነት እንዲያገለግሉ ማበረታቻ ተሰጥቷቸው ነበር። እነዚህ ወንጌላውያን ለዛሬዎቹ አቅኚዎች መንገድ ጠራጊ ሆነዋል።

2 አሁን ያለንበት ጊዜ ከ1800ዎቹ ዓመታት የተለየ ቢሆንም እንኳን አንድ ነገር ግን እውነት ነው። ራሳቸውን ለአምላክ የወሰኑ የአምላክ አገልጋዮች የሚችሉትን ያህል ጊዜያቸውን ምሥራቹን ማሰራጨታቸውን ለመቀጠል ሊጠቀሙበት ይፈልጋሉ። ረዳት አቅኚ ሆኖ ማገልገል የጉባኤ አስፋፊዎች በመንግሥቱ አገልግሎት ላይ ረዥም ሰዓት እንዲሳተፉ ስለሚያስችላቸው ውጤታማነታቸውን እንዲያሻሽሉ ይረዳቸዋል።​— ቆላ. 4:​17፤ 2 ጢ⁠ሞ. 4:​5

3 የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወንድሞችና እህቶች ረዳት አቅኚ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ለዚህ የአገልግሎት ዘርፍ ያለው አድናቆት ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉ ሰዎች ቁጥር በጣም አድጎ በ1992 ሚያዝያ ወር ላይ 950 ደርሶ ነበር! በአሁኑ ጊዜ ከአምስት ዓመት በፊት በነበረው ላይ 2, 000 አስፋፊዎች በመጨመራቸው በዚህ ዓመት በመጋቢት ከ1, 000 በላይ አስፋፊዎች ረዳት አቅኚዎች ሊሆኑና ቀጥሎ ባሉት ወራቶች ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ሰዎች በዚሁ አገልግሎት ሊካፈሉ እንደሚችሉ የተረጋገጠ ነው።

4 ከመጋቢት፣ ከሚያዝያና ከግንቦት ወራት በአንዱ ወይም ከዚያ በላይ ረዳት አቅኚ ሆናችሁ ለማገልገል ግብ እንድታወጡ እናበረታታችኋለን። የመጋቢት ወር የተጨመረው ለምንድን ነው? ምክንያቱም የዚህ ዓመት የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ የሚከበረው እሑድ መጋቢት 23 ስለሆነ ነው። በዓሉ ከሚከበርበት ቀን ቀደም ባሉት ሳምንታት ጌታችንና አዳኛችን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ባቋቋመው የመንግሥቱ የስብከት ሥራ በቅንዓት ከመካፈል የበለጠ ምንም ነገር ልንሠራ አንችልም። በመጋቢት ከፍተኛ መጠን ያለው ምስክርነት በሚሰጥበት ጊዜ ብዙ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ አብረውን እንዲገኙ ልንጋብዝ እንችላለን። በተጨማሪም የመጋቢት ወር አምስት ቅዳሜና አምስት እሑዶች ስላሉት በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ባሉት ቀኖች በመስክ አገልግሎት ረዥም ሰዓት ልናሳልፍ እንችላለን። እርግጥ በሚያዝያና በግንቦት ወራት በአገልግሎት ተመሳሳይ ቅንዓት ማሳየታችን ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተከታትለን ለመርዳትና አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? በተሰኘው ብሮሹር ተጠቅመን አዲስ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር ያስችለናል። በተጨማሪም አዳዲስ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት እትሞችን በመጠቀም በተለይ ቅዳሜና እሑድ የአገልግሎት ክልላችንን አጣርተን እንሸፍናለን።

5 ረዳት አቅኚ ለመሆን ብቁ የሚሆኑት እነማን ናቸው?:- አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት የተሰኘው መጽሐፍ ገጽ 113 ላይ እንዲህ ይላል:- “የግል ሁኔታህ የቱንም ዓይነት ይሁን፣ የተጠመቅህ ከሆንክ፣ ጥሩ ሥነ ምግባራዊ አቋም ካለህ፣ በወሩ ውስጥ በመስክ አገልግሎት የሚፈለግብህን 60 ሰዓት ማምጣት የምትችል ከሆነና ለአንድ ወር ወይም ከዚያ በላይ ረዳት አቅኚ ሆነህ ለማገልገል እንደምትችል የምታምን ከሆነ የጉባኤው ሽማግሌዎች ለዚህ የአገልግሎት መብት ያቀረብከውን ማመልከቻ በደስታ ይቀበሉታል።” ሁኔታዎችህን አስተካክለህ በመጋቢት፣ በሚያዝያ ወይም በግንቦት በዚህ መብት መካፈል ትችላለህ? እንግዲያውስ የሚያስፈልግህ ነገር ቢኖር ቅጽ መጠየቅ ብቻ ነው።

6 የሽማግሌዎች አካል የሚያሳየው ይሆናል የሚል ዝንባሌና የቀሩት የጉባኤው አስፋፊዎች የሚያሳዩት ልባዊ ድጋፍ 1, 000 ረዳት አቅኚዎች ያስፈልጋሉ ለሚለው ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ ሊያስገኝ ይገባል። (ዕብ. 13:​7) በሚመጡት አንድ ወይም ሁለት ወራት ምን ያህል የቤተሰባቸው አባል ረዳት አቅኚ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል የቤተሰብ ራሶች እንዲያረጋግጡ ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል።​— መዝ. 148:​12, 13፤ ከሥራ 21:​8, 9 ጋር አወዳድር።

7 የሙሉ ቀን ሰብዓዊ ሥራ ስላለህ፣ ተማሪ ስለሆንህ፣ የቤተሰብ ኃላፊነት ወይም ሌላ ቅዱስ ጽሑፋዊ ግዴታ ስላለብህ ብቻ ረዳት አቅኚ ሆኜ ማገልገል አልችልም ብለህ ለመደምደም አትቸኩል። ረዳት አቅኚ ሆኖ ማገልገል ለአንዳንድ አስፋፊዎች ቀላል ላይሆን ይችላል፤ ሆኖም በጥሩ ሁኔታ በመደራጀትና በይሖዋ እርዳታ ሊሳካላቸው ይችላል። (መዝ. 37:​5፤ ምሳሌ 16:​3) በአቅኚነት አገልገሎት ለመካፈል ያለህ ምኞት ሁኔታዎችህን እንዲቆጣጠረው እንጂ ሁኔታዎችህ አቅኚ ለመሆን ያለህን ምኞት እንዲቆጣጠሩት አትፍቀድ። (ምሳሌ 13:​19) ብዙዎች ለይሖዋና ለሰው ያላቸው ጠንካራ ፍቅር በሳምንቱ ውስጥ ለኑሮ የሚያደርጉትን ሩጫ አስተካክለው በወር ውስጥ የሚያከናውኑትን የአገልግሎት መጠን ለማስፋት ችለዋል። (ሉቃስ 10:​27, 28) በመንግሥቱ አገልግሎት ለመካፈል ከፍተኛ ጥረት የሚያደርጉ ሁሉ ብዙ በረከቶች ያገኛሉ።​— 1 ጢ⁠ሞ. 4:​10

8 ረዳት አቅኚነት የሚያስገኛቸው ጥቅሞች:- በሺህ የሚቆጠሩ የአምላክ አገልጋዮች በሙሉ ነፍስ ተነሳስተው በረዳት አቅኚነት ሲያገለግሉ ለይሖዋ ከፍተኛ የውዳሴ ድምፅ ያሰማሉ። እነዚህ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ለብዙ ሰዎች ምስራቹን ለማድረስ በጣሩ መጠን መንፈሱንና በረከቱን ለማግኘት በእርሱ ላይ የበለጠ ስለሚደገፉ በግላቸው ከይሖዋ ጋር ይቀራረባሉ።

9 ረዳት፣ የዘወትርና ልዩ አቅኚዎች በመካከላችን መኖራቸው በጉባኤው ውስጥ የመነቃቃት መንፈስ ያስገኛል። በመስክ አገልግሎት ያጋጠሟቸውን ተሞክሮዎች በሚናገሩበት ጊዜ ግለታቸው ወደ ሌሎች ይጋባል። ይህም ሌሎች በጣም አስፈላጊ በሆነው የአገልግሎት ሥራ ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ መጨመር እንዲችሉ ቅድሚያ የሚሰጡትን ነገርና ችሎታቸውን መለስ ብለው እንዲመረምሩ ያነሳሳቸዋል። በ70 ዓመት ዕድሜያቸው የተጠመቁ አንዲት እህት ወዲያውኑ ላልተወሰነ ጊዜ ረዳት አቅኚ ሆነው ማገልገል ጀመሩ። ከጥቂት ዓመታት በኋላ በዚህ ዕድሜያቸው በየወሩ ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ከፍተኛ ጥረት የሚያደርጉት ለምን እንደሆነ በተጠየቁ ጊዜ የዕድሜያቸው የመጀመሪያዎቹ 70 ዓመታት እንዲሁ እንደባከኑ እንደተሰማቸውና የቀረውን የሕይወት ዘመናቸውን ግን ማባከን እንደማይፈልጉ ተናግረዋል!

10 በረዳት አቅኚነት አገልግሎት የሚካፈል እያንዳንዱ ግለሰብ የአገልግሎት ችሎታውን ያሻሽላል። አንድ ወጣት ምሥክር እንዲህ በማለት አምኗል:- ‘ገና ትንሽ ልጅ ሳለሁ ወላጆቼ በስብከቱ ሥራ በሚካፈሉበት ጊዜ ይዘውኝ ይሄዱ ነበር። መስክ አገልግሎት ለእኔ የጨዋታ ያህል ነበር። ይሁን እንጂ ትምህርት ቤት ስገባ ከሌሎች ተማሪዎች የተለየሁ እንደሆንኩ ይሰማኝ ጀመር። አብረውኝ ለሚማሩ ተማሪዎች ስለ እውነት መናገር ያሳፍረኝ ጀመር። ከቤት ወደ ቤት በምሰብክበት ጊዜ በትምህርት ቤት የማውቀው አንድ ሰው ያጋጥመኝ ይሆን እያልኩ መፍራት ጀመርኩ። ችግሬ ሰውን መፍራት ሳይሆን አይቀርም። [ምሳሌ 29:​25] ትምህርቴን ጨርሼ ከወጣሁ በኋላ ለጊዜው አቅኚ ሆኜ ለማገልገል ወሰንኩ። በዚህም ምክንያት ስብከት ከመቼውም ጊዜ በላይ ያስደስተኝ ጀመር። ከዚህ ቀደም አስብ እንደነበረው ስብከትን እንደ ጨዋታ ወይም ከባድ ሸክም አድርጌ መመልከቴን አቆምኩ። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቼ በእውነት ውስጥ እድገት ሲያደርጉ ስመለከት ይሖዋ አምላክ በማደርጋቸው ጥረቶች እየደገፈኝ እንዳለ በመገንዘቤ የጠለቀ እርካታ ተሰማኝ።’ ይህ ወጣት የዘወትር አቅኚ ሆኖ ማገልገሉን ቀጥሏል።

11 በተግባር እንደታየው በጉባኤ ውስጥ ብዙዎቹ ረዳት አቅኚ ሆነው ሲያገለግሉ የአገልግሎት ክልሎች ተጣርተው ይሸፈናሉ። ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ አለን። የአገልግሎት ክልል የሚያድሉ ወንድሞች ተጨማሪ ዕቅድ ለማውጣት ደስተኞች እንደሚሆኑና ብዙ ያልተሠራባቸው አካባቢዎችን ለመሸፈን የረዳት አቅኚዎችን እርዳታ ሊጠይቁ እንደሚችሉ አያጠራጥርም። ምሳ ይዞ ሙሉ ቀን በአገልግሎት ላይ መካፈል በአገልግሎት ክልሉ ውስጥ ራቅ ወዳሉ አካባቢዎች ሄዶ ለመሥራት ያስችላል። እንዲሁም ተጨማሪ የመጽሔት ቀናት ፕሮግራም ለማውጣትና የተከማቹ መጽሔቶችን ለማሰራጨት ጥረት ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል። (ጥቅምት 23, 1996 ለጉባኤዎች በሙሉ የተጻፈውን ደብዳቤ አንቀጽ 5ን እባክህ ተመልከት።)

12 ሽማግሌዎች ቅድመ ዝግጅት ያደርጋሉ:- በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ብዙ አስፋፊዎች በአገልግሎት ላይ መሳተፍ ይችሉ ዘንድ የከሰዓት በኋላውንና አመሻሹን ወቅት ጨምሮ በሳምንቱ ውስጥ በተለያየ ሰዓት የተለያየ ዓይነት የምሥክርነት እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮግራም መውጣት ይኖርበታል። የአገልግሎት እንቅስቃሴው ከቤት ወደ ቤት የሚደረገውን አገልግሎት ጨምሮ የመንገድ ላይ ምሥክርነት፣ በንግድ ቦታዎች የሚሰጠውን ምሥክርነትና እቤታቸው ያልተገኙ ሰዎችን ማነጋገርንም የሚጨምር መሆን ይኖርበታል። ሽማግሌዎች እንዲህ ያለውን ዝግጅት ማድረጋቸው ይበልጥ ተግባራዊና አመቺ በሆነ መንገድ አቅኚዎች ከጉባኤው ጋር ተባብረው እንዲያገለግሉ ያስችላቸዋል። የመስክ አገልግሎትን አስመልክቶ የተደረጉ ዝግጅቶች በሙሉ ለጉባኤው መገለጽ ይኖርባቸዋል። ለአገልግሎት የሚደረጉት ስብሰባዎች በደንብ የተደራጁ መሆን ይገባቸዋል። በተጨማሪም የተሟላ የአገልግሎት ክልል ማዘጋጀትና በቂ መጠን ያላቸው መጽሔቶችና ጽሑፎች በፍጥነት መታዘዝ ይኖርባቸዋል።

13 የግል የአገልግሎት ፕሮግራም አውጡ:- ቀደም ሲል ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል ይፈራ የነበረ አንድ ወንድም “ከጠበኩት በላይ ቀላል ነበር። ጥሩ ፕሮግራም ማውጣት ብቻ ነው የሚጠይቀው” ብሏል። በዚህ አባሪ ጽሑፍ የመጨረሻ ገጽ ላይ ከሰፈሩት የረዳት አቅኚነት ፕሮግራም ናሙና መካከል ለአንተ ይበልጥ ተስማሚ የሆነው የትኛው ነው? በእያንዳንዱ ሳምንት አሥራ አምስት ሰዓት ለአገልግሎት መመደብ ረዳት አቅኚዎች የሚፈለግባቸው የሰዓት ግብ ላይ እንዲደርሱ ያስችላቸዋል።

14 የቤት እመቤቶችና የከሰዓት በኋላ ሽፍት ሠራተኞች ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል የጠዋቱን ጊዜ ለመስክ አገልግሎት ሊመድቡ ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ ተማሪዎችና የሌሊት ሽፍት ሠራተኞች የከሰዓት በኋላውን ጊዜ ለስብከቱ ሥራ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። የሙሉ ቀን ሥራ ያላቸው ደግሞ በምሽት አገልግሎት እየተካፈሉ በሳምንቱ መካከል አንድ ቀን እረፍት ሊወስዱ አለዚያም ቅዳሜና እሑድ ሙሉ ቀን በአገልግሎት መሳተፍ የተሻለ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ። ከቅዳሜና ከእሑድ ሌላ በመስክ አገልግሎት መካፈል የማይችሉ ደግሞ አምስት ቅዳሜና እሑድ ያላቸውን ወሮች ለአገልግሎት ይመርጣሉ። በዚህ ዓመት መጋቢት፣ ነሐሴ ወይም ኅዳር አምስት ቅዳሜና እሑድ ስላላቸው በእነዚህ ወራት ረዳት አቅኚ መሆን ይችላሉ። ገጽ 10 ላይ ለመምሪያነት እንዲያገለግል ባዶ የተተወውን ሰንጠረዥ በመጠቀም በጥንቃቄና በጸሎት አስባችሁበት ለግል ሁኔታችሁ ይበልጥ ተስማሚ የሆነ የግል የአገልግሎት ፕሮግራም ልታወጡ ትችላለህ።

15 የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ዝግጅት ያለው አንዱ ጥቅም እንደ ልብ ሊለዋወጥ የሚችል መሆኑ ነው። አቅኚ ሆናችሁ ልታገለግሉ የምትችሉበትን ወር ራሳችሁ ልትመርጡ ትችላላችሁ። እንዲሁም የፈለጋችሁትን ያህል ወር አቅኚ መሆን ትችላላችሁ። ላልተወሰነ ጊዜ ረዳት አቅኚ ሆናችሁ ማገልገል ፈልጋችሁ ግን ሁኔታችሁ ባይፈቅድላችሁ አልፎ አልፎ ረዳት አቅኚ ሆናችሁ ማገልገል ትችላላችሁ? በሌላው በኩል ደግሞ አንዳንዶች ለተወሰኑ ወራት በተከታታይ ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ችለዋል።

16 ለሙሉ ጊዜ አቅኚነት የሚደረግ ዝግጅት:- የአቅኚነት መንፈስ ያላቸው ብዙ ወንድሞች የዘወትር አቅኚ ሆነው ለማገልገል ይፈልጋሉ። ይሁን እንጂ አቅኚ ለመሆን የሚያስችል ጊዜ፣ አመቺ ሁኔታና ብርታት አይኖረኝ ይሆናል የሚል ስጋት አላቸው። በአሁኑ ጊዜ የዘወትር አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉ አብዛኞቹ አቅኚዎች ወደ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት ከመግባታቸው በፊት ረዳት አቅኚ ሆነው እንዳገለገሉ የተረጋገጠ ነው። አንድ ሰው በረዳት አቅኚነቱ ፕሮግራም ላይ በእያንዳንዱ ቀን አንድ ሰዓት ብቻ እያከለ ቢያገለግል ወይም በእያንዳንዱ ሳምንት አንድ ተጨማሪ ቀን በአገልግሎት ላይ ቢያሳልፍ የዘወትር አቅኚነት የሰዓት ግብ ላይ ሊደርስ ይችላል። ይህ ለአንተ ተስማሚ መሆኑን ለማረጋገጥ ረዳት አቅኚ ሆነህ አንድ ወይም ሁለት ወር 90 ሰዓት ለማገልገል ለምን አትሞክርም? በዚያውም ብዙ ተመላልሶ መጠየቆችና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች የማግኘት አጋጣሚ ይከፈትልሃል፤ ይህም ሚዛኑን የጠበቀ የአቅኚነት አገልግሎት እንድታከናውን ያስችልሃል።

17 አንዲት እህት ሳታቋርጥ ለስድስት ወራት ረዳት አቅኚ ሆና አገልግላለች። በዚህ ጊዜ የዘወትር አቅኚ ሆና የማገልገል ግብ ነበራት። ይህን ዓላማ ይዛ የዘወትር አቅኚዎች የሚያሟሉትን 90 ሰዓት ለመመለስ የሚያስችላት ጊዜ ለማግኘት አራት የተለያዩ ሰብዓዊ ሥራዎችን ሞከረች። በየወሩ አቅኚ መሆን የምትችል መሆኗን ለማረጋገጥ አንድ ወይም ሁለት ፕሮግራም ታወጣ ነበር። በዚህ መንገድ ሁሉን ከሞከረች በኋላ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት መካፈል እንደማትችል ሆኖ ተሰማት። ሆኖም መመሪያ እንዲሰጣት ይሖዋን መጠየቋን አላቋረጠችም። አንድ ቀን ለአገልግሎት ስብሰባ በምትዘጋጅበት ወቅት በመስከረም 1991 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣ:- “በሰዓቱ ግብ ላይ ከመጠን በላይ ከመጨነቅ ይልቅ በመሰብሰቡ ሥራ ላይ ለመሳተፍ በተገኘው ተጨማሪ አጋጣሚ ላይ ለምን አታተኩሩም? (ዮሐ. 4:​35, 36)” የሚል ሐሳብ አነበበች። እንዲህ ትላለች:- “ይህን ዓረፍተ ነገር አምስት ወይም ስድስት ጊዜ አነበብኩት። ከይሖዋ የመጣ መልስ እንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩ። በዚያች ቅጽበት የዘወትር አቅኚ ሆኜ ለማገልገል ወሰንኩ።” ምንም እንኳ ያገኘችው የትርፍ ጊዜ ሥራ ፕሮግራም ለአቅኚነት የማያመች ቢሆንም የዘወትር አቅኚ ለመሆን ማመልከቻ አስገባች። ከአንድ ሳምንት በኋላ የሥራ ፕሮግራሟ ተለወጠ። ለእርሷ ተስማሚ የሆነ የሥራ ሰዓት አገኘች። “ይህ ነገር የይሖዋ እጅ አለበት ወይስ የለበትም?” አለች። ጨምራም “መመሪያ እንዲሰጣችሁ ይሖዋን ጠይቃችሁ መልስ ካገኛችሁ በኋላ ሳታንገራግሩ ተቀበሉት።” የዘወትር አቅኚ ለመሆን ከፍተኛ ምኞት ካለህ ምናልባት በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ረዳት አቅኚ ሆነህ ካገለገልክ በኋላ አንተም በሙሉ ጊዜ አገልግሎት የተሳካልህ መሆን እንደምትችል ልትተማመን ትችላለህ።

18 በእነዚህ ልዩ እንቅስቃሴ በሚደረግባቸው ወራት ይህን የመዳን ምሥራች ለማስፋፋት ሕዝቡ የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚደግፍና ቅንዓታችሁን እንደሚባርክ እርግጠኞች ነን። (ኢሳ. 52:​7፤ ሮሜ 10:​15) በመጋቢት፣ በሚያዝያ ወይም በግንቦት ወራት ረዳት አቅኚ ሆነህ በማገልገል 1, 000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ ለሚለው ጥሪ አዎንታዊ መልስ ትሰጣለህን?

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

በረዳት አቅኚነት አገልግሎት የተሳካ ውጤት ማግኘት የሚቻልባቸው መንገዶች

■ እንደሚሳካልህ እርግጠኛ ሁን

■ ጥረትህን እንዲባርክልህ ወደ ይሖዋ ጸልይ

■ ከአንተ ጋር አቅኚ እንዲሆን ሌላ አስፋፊ ጋብዝ

■ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል የአገልግሎት ፕሮግራም አውጣ

■ በቂ መጠን ያለው መጽሔት እዘዝ

■ ጉባኤው ለአገልግሎት ላወጣው ፕሮግራም እገዛ አድርግ

■ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመስከር የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ፈልግ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ