የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/00 ገጽ 10
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የግል የአገልግሎት ክልል አለህ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • የግል የአገልግሎት ክልል ቢኖርህ ትጠቀማለህ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • በንግድ አካባቢዎች መስበክ የሚቻለው እንዴት ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • የጉባኤያችሁ የአገልግሎት ክልል ሰፊ ነውን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 8/00 ገጽ 10

የጥያቄ ሣጥን

◼ አጠቃላዩን የጉባኤ የአገልግሎት ክልል የሚያሳየው ካርታ በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ መሰቀል ይኖርበታልን?

አዎን፣ አጠቃላዩን የጉባኤ የአገልግሎት ክልል የሚያሳየው ካርታ በፍሬም ተደርጎ በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ መሰቀል ይኖርበታል። ካርታው በማስታወቂያ ሰሌዳው ላይ መሰቀል አይኖርበትም። አጠቃላዩን የጉባኤውን የአገልግሎት ክልል ወሰንና እያንዳንዱን የአገልግሎት ክልል ከተሰጠው ቁጥር ጋር የሚያሳይ መሆን ይገባዋል። ካርታው የመንግሥት አዳራሹን በጋራ የሚጠቀሙ ጉባኤዎችን ወሰን ለይቶ ማሳየት አለበት። ይህ መሆኑ አስፋፊዎችም ሆኑ ፍላጎት ያሳዩ አዳዲስ ሰዎች በየትኛው ጉባኤ የአገልግሎት ክልል ውስጥ እንደሚኖሩ ለማወቅ ይረዳቸዋል። እንዲሁም የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት በሚደረግባቸው ቦታዎች ላይ ምልክት ከተደረገ፣ ሁሉም የተመደቡበት የመጽሐፍ ጥናት ቡድን የት እንደሚገኝ እንዲያውቁ ይረዳቸዋል። ካርታው ጊዜ ያለፈበት መሆን የለበትም።

ካርታው መሰቀሉ በተቻለ መጠን ሁሉም አስፋፊዎች የራሳቸው የአገልግሎት ክልል ቢኖራቸው ጥሩ መሆኑን እንዲያስታውሱ ይረዳቸዋል። ቤታቸው አቅራቢያ የአገልግሎት ክልል መውሰድ የሚፈልጉ አስፋፊዎች ካሉ ለመምረጥ ይረዳቸዋል። አንዳንድ ጊዜም በመስክ ስምሪት ስብሰባዎች ላይ መሪው እያንዳንዱ የአስፋፊዎች ቡድን የተመደበበትን ክልል ወዲያው ለማሳየት ስለሚረዳው ጊዜ ለመቆጠብ ያስችላል።

በተጨማሪም ካርታው ጉባኤው የመንግሥቱን መልእክት በተሰጠው የአገልግሎት ክልል ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለመስበክ የተደራጀ መሆኑን የሚያሳይ ጥሩ ማስረጃ ነው።​—⁠ሉቃስ 9:​6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ