የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/04 ገጽ 3
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ጥቅም ማግኘታችሁን ቀጥሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • መጽሔቶቻችንን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙባቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 7/04 ገጽ 3

የጥያቄ ሣጥን

◼ የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች የግል ቅጂዎችን ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?

በየትኛውም ቋንቋ የተዘጋጁ የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችንም ሆነ በካሴት የተዘጋጀውን እትም በኮንትራት ማግኘት የሚቻልበት ዝግጅት ከተወሰነ ጊዜ በፊት ያቆመ በመሆኑ ሁሉም አስፋፊዎች መጽሔቶችንና ካሴቶችን ማግኘት የሚችሉት ከጉባኤያቸው ነው። በብሬይል የሚዘጋጁ መጽሔቶችንና ካሴቶችን የሚወስዱ ጽሑፎቻቸውን በፖስታ ቤት በኩል ማግኘት ይችላሉ። ጉባኤዎች በካሴት የተቀረጹ መጽሔቶችን ለማግኘት የጉባኤ ትዕዛዝ (M-202) የተባለውን ቅጽ ሞልተው መላክ እንደሚችሉ እባካችሁ አስታውሱ። በሌሎች ቋንቋዎችና በትላልቅ ፊደላት የተዘጋጁ እትሞችን ለማዘዝም በዚህ ቅጽ መጠቀም ይቻላል።

በክልላችሁ የሚገኝ አንድ ሰው መጽሔቶችን በቋሚነት ለማግኘት እንደሚፈልግ ከገለጸ ሁሉም እትም በጊዜው እንዲደርሰው እባካችሁ ጥረት አድርጉ። የተወገዱ ሰዎች መጽሔቶችን ወይም በግላቸው የሚጠቀሙባቸውን ሌሎች ጽሑፎች በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ ከሚገኘው የሥነ ጽሑፍ ክፍል መውሰድ ይችላሉ። አስፋፊዎች ለተወገዱ ሰዎች ጽሑፎች ሊያደርሱላቸው አይገባም።Rising to the Challenge

ቅርንጫፍ ቢሮው በኮንትራት መልክ ጽሑፎች እንዲደርሳቸው ዝግጅት የሚያደርገው በየጉባኤው ባሉ አስፋፊዎች አማካኝነት መጽሔቶችን ሊያገኙ ለማይችሉ ሰዎች ብቻ ነው። የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ መጽሔቶችን በሌላ በምንም መንገድ ማግኘት ለማይችል ሰው የኮንትራት ማስገቢያ ቅጽ ሞልቶ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ሲልክ ጸሐፊው ጉዳዩን የአገልግሎት ኮሚቴው ተመልክቶት ያጸደቀው መሆኑን የሚገልጽ አጠር ያለ ማስታወሻ አብሮ ይልካል።

በሌላ አባባል አስፋፊዎች ኮንትራት ለመግባት የሚያቀርቡትን ጥያቄ በግላቸው ለቅርንጫፍ ቢሮው መላክ የለባቸውም ማለት ነው። አስፋፊዎችም ሆኑ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች የሚልኳቸው እንደዚህ ያሉት ጥያቄዎች ተመልሰው ወደ ጉባኤው ይላካሉ።

◼ በወኅኒ ቤት የሚገኙ የሕግ ታራሚዎችስ እነዚህን መጽሔቶች ማግኘት የሚችሉት እንዴት ነው?

ወኅኒ ቤቱ ባለበት ክልል የሚያገለግለው ጉባኤ በዚያ ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች መጽሔቶቹን ማስገባት የሚችል ከሆነ ወደ ወኅኒ ቤቱ የሚሄዱት አስፋፊዎች መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ሊወስዱላቸው ይችላሉ። እንደዚህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ ግን የሕግ ታራሚው ራሱ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው በመጻፍ ኮንትራት ለመግባት ሊጠይቅ ይችላል። የተወገዱ የሕግ ታራሚዎችም ቢሆኑ ወደ ወኅኒ ቤት ከሚመጡት አስፋፊዎች መጽሔቶቹን ማግኘት፣ ይህ የማይቻል ከሆነ ደግሞ ኮንትራት ለመግባት ቅርንጫፍ ቢሮውን መጠየቅ ይችላሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ