መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“በጥንት ዘመን የተጻፈው ይህ ሕግ እንደሚያመለክተው በአንድ ወቅት አረጋውያን በአብዛኞቹ ባሕሎች ውስጥ አክብሮት ይሰጣቸው ነበር። [ዘሌዋውያን 19:32ን አንብብ።] እንዲህ ዓይነቱ አክብሮት ዛሬም ያለ ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት አምላክ አረጋውያንን እንዴት እንደሚንከባከብና እኛም በዚህ ረገድ ምን ማድረግ እንደምንችል ያብራራል።”
ንቁ! ሰኔ 2006
“ሽብርተኝነት አዲስ ነገር ባይሆንም በዛሬው ጊዜ የእያንዳንዱን ሰው ሕይወት የሚነካ ዓለም አቀፋዊ ክስተት ሆኗል ለማለት ይቻላል። ይህ የሆነው ለምን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ የንቁ! መጽሔት ሽብርተኝነት መቼ እንደሚያከትም እንዲሁም አምላክ በምድር ላይ እውነተኛ ሰላም እንዴት እንደሚያመጣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሐሳብ ያሳያል።” ሚክያስ 4:4ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 15
“ችግሮች እያሉብንም እንኳ ደስተኛ መሆን የሚቻል ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት የሕይወትን ውጣ ውረዶች በተሳካ መንገድ እንድንወጣቸው የሚያስችለንን መመሪያ ከየት ማግኘት እንደምንችል ይናገራል። በተጨማሪም እውነተኛ ተስፋ ምን ያህል የማጽናናት ኃይል እንዳለው ያብራራል።” ራእይ 21:3, 4ን አንብብ።
ንቁ! ሰኔ 2006
“በቅርብ ጊዜ የተከሰቱት የተፈጥሮ አደጋዎች፣ ማስጠንቀቂያ ሰምቶ እርምጃ የመውሰድን አስፈላጊነት ያጎላሉ ቢባል አይስማሙም? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ካትሪና ከተባለችው ዓውሎ ነፋስ የተረፉት ሰዎች ምን ትምህርት እንዳገኙ ያብራራል። ከዚህም በላይ በዚህ ዘመን የምንኖር ሁሉ በትኩረት ልንሰማው ስለሚገባን አንድ ማስጠንቀቂያ ይናገራል።” በገጽ 14 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።