መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“በዛሬው ጊዜ ያሉ ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት ግድ የላቸውም። እርስዎስ አንድ ሰው ሃይማኖተኛ መሆኑ ጥሩ ሰው እንዲሆን ይረዳዋል ብለው ያምናሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻው ዘመን የሚኖሩ አንዳንድ ሰዎች ከሃይማኖት ማግኘት የሚፈልጉት ምን እንደሆነ አስቀድሞ ተናግሯል። [2 ጢሞቴዎስ 4:3, 4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት እውነተኛው አምልኮ አምላክን እንዴት እንደሚያስከብርና እኛንም በምን መንገድ ሊጠቅመን እንደሚችል ያብራራል።”
ንቁ! መስከረም 2006
“ብዙ ሰዎች እንደተፈጠርን ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ በዝግመተ ለውጥ እንደመጣን ይሰማቸዋል። እርስዎስ ምን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ትክክለኛው ውሳኔ ላይ እንድንደርስ የሚረዳንን አንድ ሐሳብ እስቲ ይመልከቱ። [ኢዮብ 12:7, 8ን አንብብ።] ይህ የንቁ! መጽሔት ልዩ እትም በተፈጥሮ ውስጥ ከሚታየው ጥበብና የረቀቀ ንድፍ ምን ትምህርት እንደምናገኝ ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 15
በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች የሚያሳስብ አንድ ወቅታዊ ጉዳይ ጥቀስ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ:- “ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አሁን ያለንበትን ጊዜ በትክክል እንደሚገልጽ ይሰማዎታል? [2 ጢሞቴዎስ 3:1ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ ርዕስ በመጨረሻው ዘመን እንደምንኖር የሚያሳየውን ማስረጃ የሚያብራራ ከመሆኑም ሌላ ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለብንም ይጠቁማል።”
ንቁ! ጥቅምት 2006
“ሁሉም ሰው ማለት ይቻላል ቴሌቪዥን ማየት ያስደስተዋል። ሆኖም በቴሌቪዥን የምንመለከተውን ነገር መምረጥ እንዳለብን አይሰማዎትም? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ምሳሌ 13:20ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ቴሌቪዥን ማየት ምን ተጽዕኖ እንደሚያሳድርብንና ቴሌቪዥን የመመልከት ልማዳችንን መቆጣጠር የምንችለው እንዴት እንደሆነ የሚያብራሩ ሐሳቦችን ይዟል።”