መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“ብዙዎች ‘ብሉይ ኪዳን’ ጠቃሚ ታሪካዊ መረጃዎችን እንደያዘ ይሰማቸዋል። ይሁንና በውስጡ የሚገኙት መመሪያዎች በዛሬው ጊዜም የሚሠሩ መሆን አለመሆናቸውን በተመለከተ ጥያቄ ያነሳሉ። እርስዎ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አመለካከት አለዎት? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ሮሜ 15:4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ ‘ብሉይ ኪዳን’ ለዕለታዊ ኑሮ የሚጠቅም ምክርና አስተማማኝ የሆነ የወደፊት ተስፋ እንደያዘ ያብራራል።”
ንቁ! መስከረም 2007
“የተፈጥሮ አደጋዎችን የሚያመጣው አምላክ እንደሆነ ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ዘዳግም 32:4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ የተፈጥሮ አደጋዎች እንዲደርሱ ለምን እንደፈቀደ ያብራራል። ቤተሰብዎን እንዲህ ካሉት አደጋዎች እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ የሚገልጽ ሐሳብም አለው።”
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 15
“በዚህ ጥቅስ ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በተመለከተ ምን አመለካከት እንዳለዎት ባውቅ ደስ ይለኛል። [ዘዳግም 32:4ን አንብብ።] አምላክ ሁሉን ቻይና ፍትሐዊ ከሆነ በዓለም ላይ ሥቃይና ክፋት ይህን ያህል የበዛው ለምን እንደሆነ ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት አምላክ፣ ክፋትን እስከ አሁን ድረስ ያላስወገደው ለምን እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ጥቅምት 2007
“ያለንበት ጊዜ ከድሮው የበለጠ ለልጆች አደገኛ እንደሆነ ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ብዙዎች የምንኖረው እዚህ ጥቅስ ላይ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ይስማማሉ። [2 ጢሞቴዎስ 3:1-5ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ወላጆች፣ ልጆቻቸውን በጾታ ከሚያስነውሩ ግለሰቦች መጠበቅ የሚችሉባቸውን መንገዶች በተመለከተ አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦችን ይሰጣል።”