መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“በዛሬው ጊዜ የልጆችን አስተዳደግ የተመለከቱ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ብዙ ሐሳቦች ሲሰነዘሩ ይሰማል። ሆኖም ወላጆች አስተማማኝ ምክር ማግኘት እንደሚችሉ ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም መዝሙር 32:8ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የልጆችን አስተዳደግ በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ጠቃሚ መመሪያ ያብራራል።”
ንቁ! ኅዳር 2006
“አንዳንዶች ለሁሉ ነገር ተጠያቂው አምላክ እንደሆነ ይሰማቸዋል። አንድ አሳዛኝ ሁኔታ ሲከሰት ‘አምላክ ይህን ያደረገበት በቂ ምክንያት ይኖረዋል’ ሲሉ ይደመጣሉ። እርስዎስ ምን ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ያዕቆብ 1:13ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ለሥቃይ መንስኤ የሆነው ማን እንደሆነና አምላክም ሥቃይን ለማስወገድ ምን እንደሚያደርግ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ሐሳብ ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 15
“አንዳንዶች በዓለም ላይ የተስፋፋውን ምግባረ ብልሹነት ሲመለከቱ ‘ትክክል የሆነውን ለማድረግ ይህን ያህል መድከም ለምን አስፈለገኝ?’ ብለው ይጠይቃሉ። እርስዎስ እንዲህ ተሰምትዎት ያውቃል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] የሚከተሉትን አበረታች የሆኑ ቃላት ይመልከቱ። [ምሳሌ 2:21, 22ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ትክክል የሆነውን ማድረግ አስፈላጊ የሆነበትን ዋነኛ ምክንያት ያብራራል።”
ንቁ! ታኅሣሥ 2006
“እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው ማን ነው ይላሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ብዙዎች ከሁሉም ሰዎች የሚበልጠው ታላቅ ሰው ኢየሱስ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት ገዥ እንደመሆኑ መጠን ወደፊት በምድር ላይ ምን እንደሚያከናውን እስቲ ይመልከቱ። [በገጽ 8 እና 9 ላይ የሚገኘውን ሥዕል አሳየው። እንዲሁም ጎላ ብለው ከተጻፉት ጥቅሶች መካከል አንዱን አንብብለት።] ይህ መጽሔት ኢየሱስ ይህን የሚያደርገው እንዴትና መቼ እንደሆነ ያብራራል።”