መጽሔቶቻችንን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“አብዛኞቻችን ከሌሎች ጋር በሰላም መኖር እንፈልጋለን። ይሁን እንጂ እንዲህ ማድረግ የመናገሩን ያህል ቀላል አይደለም ቢባል ሳይስማሙ አይቀሩም። [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ ይህ የሆነበትን ምክንያት ይናገራል። [ያዕቆብ 3:2ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ይቅርታ መጠየቅ እርቅን በመፍጠርና ሰላምን በማስፈን ረገድ የሚጫወተውን ቁልፍ ሚና ያሳያል።”
ንቁ! ኅዳር 2002
“የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ማንም ሰው ‘ታምሜአለሁ’ የማይልበት ጊዜ እንደሚመጣ ይናገራል። [ኢሳይያስ 33:24ን አንብብ።] ያ ጊዜ በጣም አስደሳች የሚሆን አይመስልዎትም? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] በአሁኑ ወቅት ግን የሰው ዘር ኤድስን ጨምሮ በበርካታ በሽታዎች እየተጠቃ ነው። ይህ የንቁ! እትም ኤድስ የሚገታበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል።”
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 15
“አንዳንዶች አምላክን ለማምለክ ቤተ ክርስቲያኖችና ቤተ መቅደሶች ያስፈልጉናልን? ብለው ይጠይቃሉ። እርስዎ ምን ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰጠውን ሐሳብ ይመልከቱ። [ሥራ 17:24ን አንብብ።] እንዲህ ከሆነ ታዲያ የአምልኮ ቦታዎች የሚያስፈልጉት ለምንድን ነው? ይህ መጽሔት ቅዱሳን ጽሑፎች ለዚህ ጥያቄ የሚሰጡትን መልስ ይዟል።”
Nov. 22
“ወደፊት ሳይንስ ሕመምንና በሽታን ያስቀራል ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ የንቁ! እትም በሳይንስ መስክ የተገኙትን አንዳንድ እድገቶች ይመረምራል። እንዲሁም ሕመምንና ሞትን ለማስቀረት ኃይል ያለው ፈጣሪ ብቻ የሆነው ለምን እንደሆነ ያሳያል።” መዝሙር 146:3-5ን አንብብና መጽሔቱን አበርክት።