የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/08 ገጽ 4
  • ሙሉ በሙሉ እየተጠቀምክበት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሙሉ በሙሉ እየተጠቀምክበት ነው?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አዲስ አምድ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • ለመጠበቂያ ግንብ አንባቢያን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ለአገልግሎታችን የሚጠቅም ዓምድ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • በመጠበቂያ ግንብ ላይ የተደረጉ አስደሳች ለውጦች!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 8/08 ገጽ 4

ሙሉ በሙሉ እየተጠቀምክበት ነው?

1 “በአገልግሎት ላይ እስክጠቀምበት ቸኩያለሁ!” ይህ ሐሳብ፣ አንዲት እህት የጥር 1, 2008 መጠበቂያ ግንብን ካነበበች በኋላ የጻፈችው ነው። በሚበረከተው የመጠበቂያ ግንብ እትም ላይ በቋሚነት የሚወጡትን ዓምዶች በሚገባ አንብበሃቸዋል? በመስክ አገልግሎት ላይ እንዴት ልትጠቀምባቸው እንደምትችልስ አስበህበታል?

2 “ከኢየሱስ ምን እንማራለን?”:- ይህን ዓምድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጠቃሚ ሆኖ አግኝተኸው ሊሆን ይችላል። እስካሁን ጥናት ለማስጀመር ተጠቅመህበት የማታውቅ ከሆነ ርዕሱን ለቤቱ ባለቤት አንብብለትና ኢየሱስ ጉዳዩን በሚመለከት የተናገረውን ሐሳብ ከመጀመሪያው አንቀጽ ላይ አሳየው። ግለሰቡ ፍላጎት ካሳየ በጥያቄ መልክ የቀረቡትን ስሜት ቀስቃሽ ንዑስ ርዕሶች በመጠቀም ውይይቱ እንዲቀጥል ለማድረግ ጣር። ለመጀመሪያው ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ ጋብዘው። ከዚያም ከአንቀጹ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ሥዕሎች በአጭሩ አብራራለትና ወደሚቀጥለው አንቀጽ እለፍ። በመጀመሪያው ዕለት ግማሹን ከተወያያችሁበት በኋላ የቀረውን ደግሞ በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት ልትሸፍኑት ትችላላችሁ። ጥናቱን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተሰኘው መጽሐፍ ለመቀጠል ዝግጅት አድርግ።

3 “ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?”:- በየሦስት ወሩ የሚወጣው ይህ ዓምድ ባሎች፣ ሚስቶችና ወላጆች የቤተሰባቸውን ሰላም የሚያናጉ ችግሮች በሚያጋጥሟቸው ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችሉ ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በተጨማሪም በዚህ ዓምድ ሥር የሚወጡትን ርዕሶች የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኘውን ጥበብ እንዲያስተውሉ ለመርዳት ልትጠቀምባቸው ትችላለህ።—2 ጢሞ. 3:16, 17

4 ለወጣቶች የተዘጋጁ ዓምዶች:- “ለወጣት አንባቢያን” የተሰኘው ዓምድ አንባቢው ስለ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ቆም ብሎ እንዲያስብና ምርምር እንዲያደርግ አጋጣሚ ይከፍትለታል። ይህን ዓምድ በመስክ አገልግሎት የምታገኛቸው ወጣቶች የአምላክን ቃል ማጥናት ያለውን ጠቀሜታ እንዲገነዘቡ ለመርዳት ልትጠቀምበት ትችላለህ። (መዝ. 119:9, 105) ወላጆችን ስታነጋግር ደግሞ በየሁለት ወሩ የሚወጣውን “ልጆቻችሁን አስተምሩ” የሚለውን ዓምድ መጠቀም ትችላለህ። በዚህ ዓምድ ሥር የሚወጡት ርዕሶች ልጆች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተጠቀሱ ሰዎች ጠቃሚ ትምህርት እንዲያገኙ ይረዷቸዋል። እነዚህን ርዕሶች ከልጆችህ ጋር አንብበሃቸው ታውቃለህ?

5 ሌሎች ዓምዶች:- “አንባቢያን የሚያነሱት ጥያቄ” የሚለው ወርኃዊ ዓምድ የይሖዋ ምሥክሮች ያልሆኑ ሰዎች ሊያነሷቸው ለሚችሏቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። ከቤት ወደ ቤት በምታገለግልበት ጊዜ መጽሔቱን ለማበርከት ይህን ዓምድ መጠቀም ትችላለህ። “ከ . . . የተላከ ደብዳቤ” የተሰኘው ዓምድ ሚስዮናውያንና ሌሎች የይሖዋ ምሥክሮች አገልግሎታቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ያጋጠሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች በተመለከተ የላኳቸውን ሪፖርቶች ይዞ ይወጣል። እነዚህ ርዕሶች፣ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ምሥራቹ ስለ ክርስቶስ መገኘት በተነገረው ትንቢት ፍጻሜ መሠረት በዓለም ዙሪያ እየተሰበከ መሆኑን እንዲገነዘቡ ያስችሏቸዋል።—ማቴ. 24:3, 14

6 በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ላይ የተመሠረተውና በየወሩ የሚወጣው “ወደ አምላክ ቅረብ” የተባለው ዓምድ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ስለ ይሖዋ ይበልጥ እንዲማሩ ሊያነሳሳቸው ይችላል። “በእምነታቸው ምሰሏቸው” የሚለው ዓምድ ደግሞ በሦስት ወር አንዴ የሚዘጋጅ ሲሆን ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪኮች በዓይነ ሕሊናቸው ለመሳል እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህ ዓምድ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱ ሰዎች ያደረጓቸውን ምርጫዎች፣ ያጋጠሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎችና ያሳዩትን እምነት ሕያው በሆነ መንገድ በማቅረብ አንባቢዎች ታሪኮቹ ሕያው እንዲሆኑላቸው ያደርጋል።

7 በመስክ አገልግሎት ላይ እንድንጠቀምበት ታስቦ የተዘጋጀ ሙሉ የመጠበቂያ ግንብ እትም በየወሩ ማግኘታችን እንዴት የሚያስደስት ነው! የዚህን እትም ይዘት በሚገባ ለማወቅና በአገልግሎታችን ላይ ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም የቻልነውን ሁሉ እናድርግ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ