መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“በቤተሰብ ውስጥ የሚያጋጥመው ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። የቤተሰብ አባላት በዚህ ጥቅስ ላይ የተጠቀሰውን የኢየሱስን አመለካከት ለመከተል ጥረት ቢያደርጉ በቤተሰቡ ላይ ምን ተጽዕኖ የሚያሳድር ይመስልዎታል? [ማቴዎስ 20:28ን አንብብ። ከዚያም ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ርዕሰ ትምህርት ቤተሰቦች ኢየሱስ ከተወው ምሳሌ የሚያገኟቸውን አምስት ትምህርቶች ያብራራል።” በገጽ 16 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ኅዳር 2009
“ሃይማኖት በሰዎች መካከል ፍቅርና ሰላም እንዲኖር የሚያደርግ እንደሆነ ይሰማዎታል? ወይስ ጥላቻና ዓመፅ የሚያስፋፋ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙዎች ኢየሱስ የተናገረውን ይህንን ሐሳብ በተግባር የሚያውሉ አይመስሉም። [ማቴዎስ 5:44, 45ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ጠላትን መውደድ ይቻላል? ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል።” በገጽ 10 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“አምላክ በዚህ ዓለም ላይ ያለውን መከራና ሥቃይ አንድ ቀን ያስወግደዋል ብለው አስበው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እንዲህ ብለን እንድናምን የሚያደርገንን ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ልብ ይበሉ። [በገጽ 7 ላይ ከሚገኘው ሣጥን ላይ አንድ ጥቅስ አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ መከራንና ሥቃይን በሙሉ መቼና እንዴት እንደሚያስወግድ የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ይዟል።”
ንቁ! ታኅሣሥ 2009
“አንዳንዶች ጽንፈ ዓለም ፈጣሪ እንዳለው ያምናሉ፤ ሌሎች ግን በድንገት እንደመጣና ዓላማ እንደሌለው ያምናሉ። እርስዎስ ምን ይላሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ይህን በተመለከተ ምን እንደሚል ልብ ይበሉ። [ዕብራውያን 3:4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ጽንፈ ዓለም እንዴት እንደተገኘ እንዲሁም የተፈጠረበት ዓላማ ምን እንደሆነ ምክንያታዊ የሆኑ ማስረጃዎችን ይሰጣል።”