መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“ብዙ ሰዎች ማንኛውንም ውሳኔ ከማድረጋቸው በፊት ስለ ኮከባቸው ለማወቅ ጥረት ያደርጋሉ። ከዋክብት በሕይወታችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ብለው ያስባሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] የሚገርመው ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ስብስብ ከዋክብት ይናገራል። [2 ነገሥት 23:5ን አንብብ።] ይህ ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል ይናገራል።” በገጽ 18 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ሰኔ 2010
“አብያተ ክርስቲያናት አብዛኛውን ጊዜ ለጥምቀት፣ ለሠርግና ለቀብር ሥነ ሥርዓቶች ክፍያ ይጠይቃሉ። ይህ ተገቢ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠውን ይህን መመሪያ ልብ ይበሉ። [ማቴዎስ 10:7, 8ለን አንብብ።] ይህ ርዕስ ለሃይማኖታዊ አገልግሎቶች ክፍያ መጠየቅን በሚመለከት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ይናገራል።” በገጽ 22 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1
“ብዙ ሰዎች ሁሉን የሚችለውን ፈጣሪ አምላክ ብለው ይጠሩታል። ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ስም እንደሚነግረን ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ዘፀአት 6:3ን በ1879 እትም አንብብ።] ይህ መጽሔት የአምላክ ስም የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ ከአንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ለምን እንደወጣና አምላክን በስሙ ማወቅ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ሐምሌ 2010
“የኢኮኖሚ ሁኔታ ብዙ ሰዎችን እያሳሰባቸው ነው። ከሥራ የተፈናቀሉ ሰዎች በጣም ይጨነቃሉ፤ እየሠሩ ያሉ ደግሞ ከሥራቸው እንዳይባረሩ ይሰጋሉ። እዚህ ጥቅስ ላይ ያለው ሐሳብ ይህን ሁኔታ ለመቋቋም ይረዳናል ብለው አስበው ያውቃሉ? [ማቴዎስ 6:34ን አንብብ፤ ከዚያም ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት ገንዘባችንን በአግባቡ መያዝ የምንችልበትን መንገድ በተመለከተ ጥሩ ሐሳቦችን ይዟል። በተጨማሪም ስሜታችንን እንዴት መቆጣጠር እንደምንችል ያብራራል።”