ሐምሌ 12 የሚጀምር ሳምንት
ሐምሌ 12 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 9-11
ቁ. 1፦ 1 ነገሥት 9:10-23
ቁ. 2፦ መጽሐፍ ቅዱስ ቁሳዊ ሀብት ስለማሳደድና አልኮል ያለልክ ስለመጠጣት ምን ምክር ይሰጣል? (rs ገጽ 188 አን. 4 እስከ ገጽ 189 አን. 1)
ቁ. 3፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች ከላይ የሆነውን ጥበብ ማንጸባረቅ የሚችሉት እንዴት ነው? (ያዕ. 3:17)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ ሞክራችሁታል? ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በቅርቡ በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በወጡት በሚከተሉት ርዕሶች ውስጥ የተሰጡትን ሐሳቦች በአጭሩ ከልስ፦ “ለወንዶች ለመመሥከር ጥረት አድርጉ” (8/09)፣ “በማንኛውም ጊዜ የይሖዋ ምሥክሮች ነን” (11/09) እና “ከቤት ወደ ቤት ስታገለግሉ ጥሩ ረዳት ሁኑ” (3/10)። አድማጮች በእነዚህ ርዕሶች ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች እንዴት በተግባር ላይ እንዳዋሉና ምን ጥቅሞች እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
15 ደቂቃ፦ “ቅድሚያ ልንሰጠው የሚገባ ነገር።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።